ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦31)

ምነው ፍጣሪዬ በህልም የመሰለኝን እራሱን ህልም አርገህልይ ያየሁት ነገር እውን በሆነልይ አልሁና ደግሜ ታስበው ግን ህልም ባይሆን ሻንቆ ሊጨርሰን እንደነበር ውል ትላለብይ እንኳንም ህልም ሆነ ፈጣሪዬ ይቅር በለይ ብዬ ተመልሼ ተጠቅልዬ ተኛሁ፣ ጥዋት ተንቅልፌ የነቃሁት ተረፈደ ነበር።ብድግ አልሁና ድምጥ ለመስማትማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦30)

ጋደም እንዳለሁ ሸለብ አረገይ ወድያው ተሁለት አንዳቸው ለሽንት ቲወጡ ሰማሁ ብድግ አልሁና የክፍሌን በር በመጠኑ ከፍቼ ትመለከት የሽንት ቤቱ መብራት በርቷል።ትጠባባቅ ሻንቆ በውስጥ ሙታንታ ተሽንት ቤት ወጣ። እንዳየሁት በሁለት እግሩ የሚሄድ ትልቅ በሬ እንዢ ሰውም አልመስልሽ አለይ። ወደ እትዬ መኝታማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦29)

ቁልቁል እየተመለከቱ ሽቅብ ቲወጡ የልቤ ትርቷ ተመቅፅበት እጥፍ ሆነይ። ተጦሎት ቤት ወጥተው ወደ ምኝታ ክፍላቸው እስቲገቡ ቸኮልሁ።እትዬ ተዛ ድብቅ ዋሻ ወጥተው እንዳበቁ የጠሎት ቤቱን ድብቅ የወለል በር ዘግተው ተመሄድ ይልቅ አፋፉ ላይ ተገትረው ቁልቁል ቲመለከቱ ይህቺ መሰሪ ሰትዬ ምን ሆናማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦28)

ተሽጉጡ መሀል አንድ በቁመቷ ዘለግ ያለችውን መረጥሁ። አይኔ ሽጉጦቹ ታሉበት መሳቢያ ውስጥ ጥግ ላይ እተቀመጡት ነገሮይ ላይ አረፈ። ትዝ ይለኛል የዛሬ ሶስት አመት አከባቢ ታይሆን አይቀርም። ቡና እያፈላሁ ነበር ጋሼ እትዬን እንዲህ አላቸው ” ሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ጥሩ ትላልሆነማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦27)

እህን ግዜ እራሴን መቆጣጠር ተስኖይ ጩሂ ጩሂ ትላለኝ አፌን በሁለት እጄ ግጥም አድርጌ ያዝሁት። አጣብቆ ተያዛት ግድግዳ ላይ ትንፋሽ አጥሯት አይኗ እስቲገለበጥ አቆያትና ተላይ አንገቷን ባንድ እጁ እንዳነቃት ተስር ሁለት እግራን ባንድ እጅ ጠርንፎ ሽቅብ በማንሳት እትከሻው ላይ ቲሸከማት እሷንምማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦26)

ዘንዶው መስኮት የሚያህል አፉን ከፍቶ የተወረወረለትን ሰውዬ መሬት ታይነካ ቀለበው።ተመቅፅበት እስተወገቡ በመዋጥ ሰውየው ነብስ ይዞት ቲታገለው ተግራ ወደ ቀኝ ተቀኝ ወደ ግራ እያላተመ ወደ ውስጥ ያስገባው ዥመር። ልጅቱ እትዬ ላይ እያፈጠጠይ ጨካኛይ ናችሁ አረመኔዋይ ናችሁ ፈጣሪዬ ለምን ዝም አልህ እባክህማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦25)

እኝህ ሴትዬ መጥተው ተምድረ ገፅ ታይሰውሩኝ በፊት የማመልጥበት መላ ቢከሰትልይ ብዬ ታወጣ ታወርድ ቆየሁ። ትለ ባለቤቶ መፈታት ቲያወሩ ውስጤን ደስ ብሎት ትለነበር ይሆናል ታይታወቀይ ያመለጠኝ ልበላቸው አይ ይህም አይሆንም አንድ ግዜ አላልሁም ብያለለሁ አላልሁም በቃ በዚሁ ተመድረቅ ውጪ ሌላ ማምለጫምማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦24)

አረ ምንም አላልሁም እትዬ ምን እላለሁ ብለው ነው። “ቆይ..ቆይ ቆይ ቆይ … እሄን ሁሉ አመት ሰናይት ብለው ሲጠሩሽ አቤት ሲያዙሽ እሺ ከማለት ውጪ ድምፅሽ የማይሰማ ልጁ ዛሬ እንደማይረባ ከሰል እላዬ ላይ የምትንጣጭብኝ ምንድን ነው ሚስጥሩ ለመሆኑ? እ ንዴ: ማን ነውማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦23)

ቀማምሰው እንደመጡ የአይናቸው መቅላትና የድምጣቸው መቀየር ያስታውቃል።መደንገጤ እንዳይታወቅብይ ጥረት እያረግሁ የለለይን ምራቅ ሁለቴ ዋጥሁና …. እንዴ እትዬ መጡ እንዴ ቆዩ ምነው? ብቻዬን ትለተቀመጥሁ ነው መሰል ተሌቪዥኑን ታናጠፋው በፊት ትናይ የነበረው የሀገራችን ክፉ ነገር በሙሉ ፊቴ ድቅን ቢልብይ ሀገሬ አሳዘነችይ።ተዛ ምንማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦22)

ም…ን…አልክ..በልሁ? “ምን ላርግ ሰንዬ …” በል ዝም በል አልሁና አፉን ያዝሁት።የሰይጣን ጆሮ አይስማው በልሁ እንዳትደግመው። አልሁት። እንኳን እቤቱ ተቀምጠን በየሄድንበትም እየተከተለ አላስቀምጥ ያለን ሰይጣን በልሁ ያለውን ተኔ ቀድሞ እንደሰማው እያሰብሁ።እሄን ተማረግ ሞቴን እመርጣለሁ!። ጭራሽ በጄ እንዳጠፋህ ጠየከኝ በልሁ! ደግመህ እንዳታስበው።ደሞማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦21)

“ሀብታቸውን ተጠቅመው እዚህ ላደረሰቻቸው ሀገር ትምህርት ቤት እና ሆስፒታል ተመገንባት ይልቅ በየጉራንጉሩ እስርቤት እየገነቡ ለዘመናት የፍዳ ቀንበር መሸከም ያመረረውን ትውልድ በሸክም ላይ ሸክም በችግር ላይ ችግር እየጨመሩ ተዘመን ዘመን በጦርነት ተወልዶ በጭቆና አድጎ በጭቆና እንዲሞት ያደርጉታል። ሰንዬ ተድህነት ባያወጡን እንኳማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦20)

…ሳጥናኤል ወ አጋንንት አስርቱ ትዛዛት.. ትእዛዝ ሶስት፦ እሄ ጦሙን እያደረ ፈጣሪውን ጥዋት ተነስቶ የሚያመሰግን ህዝብ ወደኔ ለማምጣት ብልሀተኛች ሁኑ። ነፃ እናወጣችኋለን እያላችሁ ነፃ ሆነው እንዳይኖሩና ዘወትር ያልታሰሩበትን ገመድ ለመፍታት እረፍት አልባ ሂወት እንዲገፉ በማድረግ እረፍት ያገኙ ዘንድ ምግባረ እርኩሰትን እንዲፈፅሙማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦19)

ቄራ ነው”። አለይ። እቤቱ ግድግዳ ላይ ተትንሿ ቢላ ዥምሮ እስከ ላይኛው ግዥራ ፣ተትንሿ መቀስ ዥምሮ እስተ ትልቁ የጥድ ማኸርከሚያው መቀስ ፣ ማዋለጃ የሚመስል ባለ ጎማ አልጋ፣ተበልሁ ጀርባ በስተቀኝ 2 ተከፋች የቀብር ሀውልቶይ ቲኖሩ በስተግራ ደሞ አንዱ ጥቁር መጋረዣና አንድ ቀይማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦18)

እትዬ ተጣጥበው እና ተኳኩለው እንደጨረሱ ተላይኛው ክፍሎች ባንዱ ውስጥ ገቡ። ወድያው አንድ የመሂና ታርጋና መፍቻ ይዘው በመውጣት መሂናቸው ላይ የነበረውን ታርጋ ፈተው ቀየሩት። ተዛ የቀየሩትን ወደ ቤት አስገብተው የጎንዬሽ ገርመም አርገውይ ነይ የውጭውን በር ክፈች አሉይ። የከፈትሁበትን ቁልፍ ተቀብለውይ ተውጪማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦17)

እሳቸው ቲጮሁ እኔ እንደፈዘዝሁ በልሁ ጋር ትለረሳሁት ሰሀን ታስብ መላሽ ትላልሰጠኊቸው በሽቀው… ወደ እኔ ይበልጡን በመጠጋት “ያን ሁሉ ሳንኳኳ ምን ስትሰሪ ነበር እያልኩሽ እኮ ነው ብለው ቲያፈጡብኝ ተሄድኩበት ሀሳብ ባነንሁና የባለፈውን እንደመብረቅ ልብ የሚያቀዘቅዝ ጥፊያቸውን ታያልሱኝ በፊት… ወደ ላይም ወደማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦16 )

የሞት ሞቴን ይቅር ይበሉይ እትዬ ታለወትሮዬ ዛሬ የታሸገ ውሃ አምሮት ውል ቲልብይ ግዜ ነው ትለተኙ ታላስፈቅዶት የወሰድሁት አልሁና በድንጋጤ ምን እንደምሰራም ታይታወቀይ ውሃውንም አፌንም ከፈትሁና አንቆረቆርኩት። ታሁን ታሁን እትዬ ዘለው አናቴ ላይ የሚከመሩብይ ትለመሰለይ አይኔን ታልነቅል ትመለከታቸው ..ቃል ታፋቸው ታይወጣማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦15)

እኔም አሁን አንድ ነገር ታፌ ቢወጣ እትዬ ተነስተው ተነጨርቄ ተመዋጥ አይመለሱም። “ተእብድ አጠገብ ፥ ድንጋይ አይወረወርም” አለች ያቺ ያገር ቤቷ ሚስኪን ጎረቤቴ። እዚህ እማ ምን ኮረቤት አለ። ሰው ሁሉ ደም የተቃባ ይመስል ተሸሽጎ ነው የሚኖረው። ተቸገርኩ ቢባል ለጋሽ፣ ኡኡ ቢሉማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦14)

ብጋደምም  እንቅልፍ  ተየት ይመጣል ። ፈጣሪዬ እባክህ ክፉውን እርቅለት። እንደው በልሁ ምንም ታይሆን በፊት አንዴ   ባወራሁት እና  ምን  እንደሚለኝ  በሰማሁ። እሄን አርጊ ታለኝ ምንም ይሁን ምን ተማረግ አልመለስም !። ተዳንም ባንድ ላይ! ተሞትንም ባንድ ላይ! እዚህ ቤት ውስጥ  ምን አለውማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦13)

ደምስሮቼ ሁሉ ስራቸውን አቁመው ማን እንደነካኝ ለማየት  አንገቴን ወደ ጀርባዬ ማዞር  ተሳነኝ። የሞትኩ ያህል ትንፋሽና ድምጤን አጥፍቼ  በፍርሀት ተውጬ ትጠባበቅ  ተውሃላ የነካኝ ነገር እዛው እነካኝ ቦታ እንደተጫነኝ አልንቀሳቀስ ቲል  የሞት ሜቴን ዘወር ብዬ ታይ። ተደነገጥኩት ባልተናነሰ ባስደነገጠኝ ነገር በሸቅሁ። “ፍርሀትማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦12)

“በቀላሉ እማ ገድዬ አልቀብርህም  በቁምህ አስቃይቼ እሄን እልህክን አበርድልሀለሁ። “አሉና ሽጉጡን ታፉ ውስጥ ቲያወጡት መርፌ ወግተው ወደ ሰውነቱ ያንቆረቆሩት ፈሳሽ ምን እንደሆን እንጃ  ታፉ ውስጥ የሚዝለገለግ ነጭ ፈሳሽ እየወጣ እንደቅድሙ ለመጮህ ተሳነው መሰል በለሆሳስ  እያቃሰተ ” ግደይኝ አንቺ አረመኔ ሴትዬማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 11)

እንዳልፈጠፈጥ ፈራሁ ቀና ብዬ እራሴን ለማረጋጋት  ሞከርሁ። ጥጉን ይዤ  እምዬ እሄን ጉዴን አላየሽ  እስተዛሬ ታውሬ ጋር አብሬ  ነው የኖርኩት አልሁ ለራሴ።  ትንሽ ተቀመጥሁና  ትንፋሽ ወስጄ መልሼ በሆዴ  ተኝቼ ቁልቁል ትመለከት  የበልሁ ሁኔታ አንጀቴን አላወሰው። እትዬ የ ባእድ  የአምልኮ ጠሎታቸውን ጨርሰውማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 10)

ሻወር ቤት ውስጥ ሆኜ ያለሁበት ክፍል ውስጥ ዘው ብለው ቲገቡ እኔኑ የተከተሉኝ መስሎኝ  ወደ ውስጥም ወደ ደጅም ትንፋሽ ማውጣት ተስኖኝ ፀጥ አልሁ። እሳቸው ግን እክፍሉ እንደገቡ ግድግዳዉ ላይ የተሰቀለውን  ትልቅ ስእል  ተግድግዳው ላይ አወረዱ። ደሞ ቀጠሉና ቀለሙ ተግድግዳው ጋር የሚመሳሰልማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 9)

ቀጥታ ወደ ክፍሌ ገባሁ የሰውየው አስተያየት እና አስፈሪ ገፅታ ተፊቴ አልጠፋ አለኝ።ትናንት ያንን ምስኪን ደሀ በልሁን አስሬ እስሩ እየሄድኩ ተፖሊሶቹ ጋር  ታልሄዱኩ እያልሁ ትጨቀጭቀው ሰውየው አይቶን ታይሆን አይቀርም እትዬ  በልሁ ሚስጥር ያወጣ መስሏቸው የጨከኑበት። አይ እትዬ ምን አይነት ጨኳኝ ሰውማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 8)

ሰሚ የለለው ጩኸት ምን ያህል ውስጥን እንደሚያቆስል የደረሰበት ብቻ ታልሆነ ማን ይረዳዋል?።ባይወጣልኝም እስቲደክመኝ እለቀስሁ አልጋዬ ላይ በደረቴ እንደተደፋሁ በልሁን ተከፋ ጉዳት እንዲጠብቀው አምላኬን እየለመንሁና እየተማፀንሁ ቆየሁና ምናልባት ተኔ በፊት እዚህ ቤት የቤት ሰራተኛ ተነበሩት ውስጥ ምናልባት ምናልባት እክፍሉ ውስጥ የደበቁትማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦7)

አድፍጬ  ትጠባበቅ የትዬ ቤት አንፖል ታይጠፋ  እኩለ ሊሊት ሆነ።ተትዬ ባህሪ የማውቀው መብራት ታይጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸው ነው።ግራ ገባኝ እስታሁን አልተኙም ወይስ ታያጠፉ እንቅልፍ ጥሏቸው ይሆን ?ጨነቀኝ። በጭንቀት ትወዛወዝ  ገርበብ ያለው የትዬ ምኝታ ቤት ቲከፈት ሰማሁ።ቆሌዬ ተላዬ ላይ ረገፈ። ተተቀመጥኩበት  ተበሩ ስርማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 6)

እራሴን መሆን ተስኖኝ ተዝለፍልፌ መሬት እንደደረስኩ እትዬ “አንቺ ምን ሆነሻል”  አሉና  አምባረቁብኝ ።  ተንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ሰመመን ውስጥ  ሆኜ ምድር ምድሪቱን ትመለከት በልሁ ተወደ ጀርባዬ እየሮጠ መጣና …”እይይ እቺ ሚስኪን ልጅ  እንዲሁ እትዬ ክፉ እንዳይገጥማቸው ብላ ትትጨነቅ ነው የዋለችው አይዞሽማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 5)

እሄን ግዜ በልሁ “እዚህ ቤት ሰራተኛች ሲገቡ እንጂ ሲወጡ  አይቼ አላውቅም” ያለኝ ነገር  ተትዬ መሰወር ጋር ተገናኝቶ በመላ ሰውነቴ ትኩሳት ከፍርሀት ጋር ለቀቀብኝ። ፓሊሶቹ ስራቸውን አገባደው ለምሄድ ሲሰናዱ አየሁና እየተጣደፍኩ ወደ በልሁ ጋር ሄጄ እኔ ይችን ቀን እዚህ ቤት ከማድርማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 4)

በልሁ ፈራ ተባ እያለ በሩን ቲከፍተው አንድ አማላይ ግርማ ሞገስ የተላበሰሰ ፓሊስ “ጤና ይስጥልኝ” አለና ወደ ውስጥ ዘለቀ ሶስት አምሳያዋቹ ተከተሉት ሁለት አምሳያዋቹ ደሞ ሳይገቡ እዛው ደጅ ላይ ቆመው ሰፈሩን መቃኘት ጀመሩ። “የቤቱ ባለቤት ይኖራሉ?” ማንም የለም ጌታዬ አልኩኝ ቀድሜማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር … (ክፍል፦3)

ሀሎ…ሀሎ…ሀሎ ማን ልበል…  ድምጥ የለም። እትዬ በጭንቀት  ጆሮዬ  ላይ ወደ  ለጠፍኩት  ስልክ  ጠጋ አሉና የደዋዩን  ድምጥ ለመስማት ሞከሩ …ሀሎ …..ማን ልበል ሀሎ….  አሁንም  ድምጥ  የለም  እትዬ ተፊቴ ቆመው  እንድዘጋው በምልክት አዘዙኝ ። እንደዘገሁት ስልኩን በሁለት እጃቸው ወደ ላይ አነሱና ተመሬትማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር … (ክፍል፦2)

ጋሼ  ከታሰሩ ቡሀላ የትዬ ነገረስራ ሁሉ  ያስፈራል  ያስጨንቃል አሁን ለታ ለስንት አመት ግድግዳው ላይ የተሰቀለው ሰአት የለመደውን ቆጠራ  ቀጥሏል  ቃ….ቃ……ቃ…. ቃ  ይላል  ወድያው እትየ ተፈዘዙበት አለም ተመለሱና  ” እሄ የግድግዳ ሰአት ድምፁ ሊያሳብደኝ ነው አውርጄ ሳልከሰክሰው  አውርጂና አጥፊልኝ!  አሉኝ የጆሮዬማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር ያለው ድብቅ መቃብር ቤት (ክፍል፦1)

ሰናይት እባላለሁይ ትውልዴ እዚሁ ሸዋ አንድ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። እትዬ ቤት በቤት ሰራተይነት ከተቀጠርኩ  5 አመት አልፎያል   ነገር  ግን አንድም ቀን ቤተሰቦቼየን እንድጠይቅም ከግቢ እንድወጣም ተፈቅዶልይ አያውቅም። የመጀመሪያ ቀን አንድ  ደላላ ወደ እትዬ ቤት ሲያመጣይ ወደ ውጪም ወደ ሹፌሩምማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...