Tidarfelagi.com

“lucifer”

በራሴ ጉዳይ ተንበርክኬ የፀለይኩበት ቀን በጣም እሩቅ ነው። እውነት ለማውራት ከጠየቅኩት በላይ የማይገባኝ ሁላ የተሰጠኝ ሰው ነኝና ብዙም ጥያቄ የለኝም! ከፍቶኝ ፊቱ የቀረብኩባቸውንም ቀናት formal ፀሎት የፀለይኩባቸው ቀናት በጣም ድሮ ናቸው። አጠገቤ ሆኖ እንደሚሰማኝ እነጫነጫለሁ።
«ከዚህ በላይ መሸከም እንደማልችል አታውቅም? እኔ ታውቃለህ ለሆነው ላልሆነው አላስቸግርህም! ይሄንንማ ስማኝ! ደሞ ታውቃለህ ፅድቄን ተማምኜ አይደለም ስምህን መጥራቴ፣ ከንቱ እንደሆንኩ አውቃለሁ ታውቃለህ! ምህረትህን ተማምኜ ነው በድፍረት የምጠይቅህ! ዝምታህ አልበዛም? ከዚህ በላይ አትፈትነኝ! አሳምረህ ታውቀኛለህ ወድቃለሁ ……… » እንዲህ ያለ ወሬም ፀሎትም አይሉት ነገር ነው የምነጫነጭበት። ሲመልስልኝ እና እጄን በአፌ ሲያስጭነኝ እንኳን እኔ በዙሪያዬ ያሉ ይገረማሉ!

አርብ እለት የኔ የምላት ሰው ትንሽ ከበድ ያለ ነገር ውስጥ ገባችብኝ እና ለተወሰነ ሰዓታት ልቤን ሁላ የምተፋው መስሎኝ ነበር ከጭንቀቴ የተነሳ። everyone prays in the end እንዳለው ሳም ስሚዝ ልፀልይ አልተንበረከኩም? ከዛ ምን ብዬ እንደምፀልይ ሁላ ግራ አልገባኝም? እግዜር ራሱ ተገርሞ እነገብርኤልን «ኸረ ኑ እዩልኝ? » ያለ ነው የሚመስለኝ። በስርዓቱ «እግዚአብሄር አምላክ ሆይ እባክህ ፀሎቴን ስማኝ ……. » ብዬ ጀምሬ ድንገት ደግሞ በኔ ከንቱነት ፀሎቴ ቢዘገይስ ብዬ መሰለኝ «እሺ በቃ እኔን ተወኝ ስለእሷ የዋህ ልብና ባንተ ስለጣለችው እምነት ስትል ክፉ አይንካት! እኔን ተወኝ!» ብዬ እንደለመድኩት ኢንፎርማሊ ጸልዬ ጨረስኩ። የሆነው ሆኖ ያ ሰዓት አለፈ እና መልካም ከሆነ በኋላ የሆንኩትን አስቤ በራሴ ሙድ ስይዝ lucifer የሚለው ፊልም ትዝ አለኝ…….. everyone prayes in the end, even lucifer
ፊልሙ ሉሲፈር ሲኦል ውስጥ የሚቀጡ ነፍሶችን ከሚያስተዳድርበት ቫኬሽን ልውሰድ ብሎ ሎሳንጅለስ መጥቶ ነው። እማጅኑልኝ 😂😜 ለሁሉም ነገር እግዚአብሄርን ነው ተጠያቂ አድርጎ የሚወቅሰው። የሆነኛው ሲዝን ላይ የወደዳት ቺክ ልትሞትበት ሲሆን «father …. » ብሎ ፀሎቱን ጀመረኣ 😆😅

ካላያችሁ ልጠቁማችሁ! ፊልሙ በታሪክ ፍሰት ረገድ ዋው የሚባልለት አይደለም! ፍልስፍናዎቹ በጣም ተመችቶኝ ነው ያየሁት። በተለይ መፅሃፍ ቅዱስን አንብቦ ላደገ ሰው። አትመራመሩ ተብለን የዘለልናትን ምዕራፍ እያነሳ ምናልባትም ባላሰብነው መንገድ ያሳየናል። ሲጀመር ሉሲፈር ነጭ ፈረንጅ። አብ እግዚአብሄር እና ሚካኤል ጥቁር ሆነው ነው ፊልሙ ላይ የሚሰሩት እነገብርኤል ነጭ ናቸው። 😀 ሁሉንም ነገር 666 እና የጥልቁ ሴራ እያላችሁ የምትተነትኑ ሰዎች ባታዩት አጥብቆ ይመከራል። 🤣🤣🤣
ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝማ❤️❤️❤️❤️❤️

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም