ሰማዕታትን አንረሳቸውም

ከሰማኒያ አመታት በፊት ኢትዮጵያዊያን ዘማቾች አይተው የማያውቁትን የአውሮፕላን ድብደባ የገለፁበት ግጥም እንዲህ ይላል። ‹‹በትግራይ ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በጎንደር ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በሸዋ ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በጎጃም ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በሰማይ ላይ መጣ በማናውቀው አገር….›› ጣልያኖች በማናውቀውማንበብ ይቀጥሉ…

የእቴጌ እና የሂትለር ፎቶ

ባየኋቸው ቁጥር ግርርም ከሚሉኝ ታሪካዊ ፎቶዎች አንዱን ላካፍልዎት፡፡ በ1935 የተነሣው ይህ ፎቶው የተገኘው ባሶሼትድ ፕሬስ መዝገብ ውስጥ ነው፡፡ በፎቶው ላይ ለጊዜው ስሙን ያልደረስኩበት ሠዓሊ የግርማዊት እቴጌ መነን እና የአዶልፍ ሂትለርን ሥዕል ሲሸጥ ይታያል፡፡ በፎቶው ጀርባ ላይ እንደ ተገለጸው ከሆነ፤የጀርመኑ አምባገነንማንበብ ይቀጥሉ…

ሀገሬ

‹‹ሀገሬ…›› (መነሻ ሀሳብ ፤ ‹‹ ዘ ሬቬናንት›› ፊልም) በከባድ ንፋስና ዝናብ ሰአት ትልልቅ ዛፎችን አይታችሁ ታውቃላችሁ? የቅጠሎቹን ሳያቋርጡ መርገፍገፍ፣ የቅርንጫፎቹን መንቀጥቀጥ ስታዩ ‹‹ይሄ ዛፍ ካሁን ካሁን ወደቀ፣ ካሁን ካሁን ተገነደሰ ››ብላችሁ ሰግታችሁ ይሆናል፡፡ ቅርንጫፎቹ ቅንጥስ እያሉ ቢወድቁም፣ ቅጠሎቹ ባንድነት ቢረግፉም፣ ግንዱንማንበብ ይቀጥሉ…

ዶ/ር ኣበራ ሞላ

ዶ/ር ኣበራ ሞላ መጋቢት ፳፬ ቀን ፲፱፻፵ ዓ.ም. ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ ኣውራጃ፣ በረህ ወረዳ፣ ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱ ሲሆን በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን መጠቀም እንዲቻል ያደረጉ ምሁር ናቸው። ይሀንንም ያደረጉት የዓማርኛውን የጽሕፈት መሣሪያ (ታይፕራይተር) ለሚያውቁት ቀላል እንዲሆን በ“a”፣ “b”፣ “c”፣ “d”ማንበብ ይቀጥሉ…

አለቃ ገብረ ሐና

አለቃ ገብረ ሐና በብዙ ሰዎች ዘንድ በቀልደኝነታቸው ይታወቁ እንጂ በቤተክርስቲያን ታሪክ ወደር ከማይገኝላቸው ሊቃውንት አንዱ አንደነበሩ ያውቃሉ ? የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በድሮው የደብረታቦር አውራጃ ፎገራ ወረዳ፤ ናብጋ ጊዮርጊስ በተባለው ቦታ በ1814 ዓ.ም. ነው። የመጀመርያ ትምህርታቸውን በአካባቢው ከቀሰሙ በኋላማንበብ ይቀጥሉ…

ባለ መሰንቆውና ባለ ወለሎው

“ሮድ ደሴት” በተባለ አገር ውስጥ እንደ እንደምኖር የነገርኩት ጓደኛየ “እና ባሣ አጥማጅነት ነው የምትተዳደረው?” ብሎኛል፡፡ ሮድ ደሴት አበሻ እጥረት ክፉኛ ከሚያጠቃቸው ክልሎች አንዱ ነው ፡፡ አሁን ምድሩም ሰማዩም ሰውም ነጭ ነው፡፡ ያገር ሰው በጣም ይናፍቀኛል፡፡ የሆነ ያበሻ ዓይነ ውሃ ያለው አልፎማንበብ ይቀጥሉ…

የመጀመሪያው ፎቶግራፍ እና ክሊኒክ ኣጀማመር በኢትዮጵያ

ዳግማዊ ምኒልክ ከዘመናዊነት ጋር ተያይዘው ከሚነሱባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ፎቶግራፍ ይገኝበታል፡፡ ፎቶግራፍና ኢትዮጵያ የተዋወቁት በርሳቸው ዘመን እንደሆነ ይወሳል፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው ፎቶግራፍ አንሺ ከካሜራው ጋር ኢትዮጵያ የገባው በ1875 ዓ.ም. ነው፡፡ በወቅቱ የነበሩት ኣማካሪዎች አንደዘገቡት አና ቡሃላም በ በጳውሎስ ኞኞ ተተርጉሞ አንደቀረበውማንበብ ይቀጥሉ…

የመጀመሪያዎቹ ሚኒስትሮች

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ሚኒስትሮች ፲፱፻ (1900) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ሚኒስትሮች የተሾሙት በጥቅምት ፲፬ (14) ቀን ፲፱፻ (1900) ዓ/ም ነው። በዚያን ጊዜም በዳግማዊ አጤ ምኒልክ የተሾሙት የመጀመርያዎቹ ሰባት ሚኒስትሮች የሚከተለት ናቸው። ፩ኛ/ አፈንጉስ ነሲቡ መስቀሉ — የዳኝነት ሚኒስትርማንበብ ይቀጥሉ…

የአውሮፕላን ታሪክ በኢትዮጵያ 

የመጀመሪያው አውሮፕላን በ1921 ዓ.ም. አዲስ አበባ መድረስ ለኢትዮጵያውን ከውጭው ዓለም ጋር ለመገናኘት አዲስ ምዕራፍ የተከፈተበት ቀን መሆኑ አስደስቷቸዋል፡፡ ለፈረንሳዮቹ ደግሞ በኢትዮጵያ አቪዬሽን ታሪክ ከሌሎች አገሮች በተለይ ዝግጅቱን አጠናቆ ከነበረው ጀርመን መቅደማቸው አስፈንድቋቸዋል፡፡ ለአብዛኛው ኢትዮጵያ ግን የአውሮፕላን መምጣት ግርምትና ትዕንግርት ፈጥሮበታል፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…

የኢትዮጲያውያን ገና በአል

የገና (ልደት) በዓል በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ ዐብይ በአላት ውስጥ አንዱ በአል ነው። እለቱ በትንቢተ ነቢያት የተነገረለት የሰውን ልጆች በጥንተ ተፈጥሮ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ አሁን ደግሞ በሐዳስ ተፈጥሮ ለመፍጠር ማለት ሰውን ለማዳን ሰው ሆኖ የተወለደበት እለት ነው። የልደት በዐልማንበብ ይቀጥሉ…

የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ

አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ በዘፈን አንደኛ ሙሉቀን መለሰ (እስከመቸ ድረስ ጥላሁን ገሰሰ) የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ? Lol የህዳሴውን ግድብ ወደ “ህዳሴው ገደል” ያሸጋገረውን ስምምነት የፈረመው ሰውየ“ እጁን ለቁርጥማት፤ ደረቱን ለውጋት“ እንዲዳርገው በመመረቅ ወደ ሰላምታየ እገባለሁ፡፡ እንዴት ናችሁ፤ ያልታደላችሁ? እኔ በህይወቴማንበብ ይቀጥሉ…

ስለችጋር

ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ ‹‹እየበሉ›› በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ ችጋር የሚያጠቃው ማንንማንበብ ይቀጥሉ…

“ገጽታ ግንባታ?”

ባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…

ገፅታ ሳይኖር፣ ለገፅታ መጨነቅ ውጤት የለውም!

“በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው ችጋር መጀመሪያ ነው፤ በመስከረምና በጥቅምት የዝናብ ወቅቱን ተከትሎ የሚመጣ ችጋር ገና መንገድ ላይ ነው፤ በአብዛኛዎቹ ገበሬዎች ላይ የሚደርሰው በመጋቢትና በሚያዝያ ነው፤ በድንቁርና ንግግርና በመመጻደቅ አይቆምም፤ አሁን የተከሰተውን ምልክት ለመቀበልና ዋናውን ችጋር ለመከላከል የሚያስፈልገውን እርምጃ በጊዜው መውሰድ ካልተቻለማንበብ ይቀጥሉ…

“ከጥላቻ ማህፀን የሚወለድ ሰላም የለም”

Bertrand Russell በ ‘The Proposed Road to Freedom’ ፣ የማርክስን “የኮሚኒስት ማኒፌስቶ” ሃሳብ (የዓለም ሰራተኞች ተባበሩ የሚለውን) ሲተች የሚከተለውን ይላል… ‘ There is no Alchemy by which a universal harmony can be produced out of hatred’ በአጭሩ…ከጥላቻ የሚገነባ ሁሉ ዓቀፋዊማንበብ ይቀጥሉ…

ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ

ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ- የመጀመሪያው ሙዚቃን በሸክላ ያስቀረፁ እና ህጋዊ መንጃ ፍቃድ በመያዝ (ከጀርመን ሀገር) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መኪና አሽከርካሪ /ሹፌር/ እና የመጀመሪያው መካኒክ በ1900ዓ.ም ሙሴ ሆልስ የተባሉ ጀርመናዊ በኢትዮጵያ ለብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ አፄ ምኒልክን በተሰናበቱበት ጊዜ ጀርመንማንበብ ይቀጥሉ…

የተቸካዮች ምክር ቤት

ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን ዘና ለማረግማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹አላውቅም›› ማለት ነውር የሆነበት አገር እየገነባን ነው ?

አገራችን ላይ ትልቁ ችግር የሚመስለኝ ….ታላላቆች በሁሉም ነገር ትልቅ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብና ‹ታናናሾች › በሁሉም ነገር ትንሽ እንደሆኑ አድርጎ ማናናቅ ነው …ለምሳሌ ሰፈራችን ውስጥ ያለን ታዋቂ አርቲስት …ህግም ፣ፍልስፍናም፣ መሃንዲስነትም ፣ የተበላሸ ቧንቧ ጥገናም ፣ ፖለቲካም ፣ስፖርትም ከሱ በላይ አዋቂማንበብ ይቀጥሉ…

ሄሊ እና የመንዝ ወርቅ

በዚያ ሰሞን ለአጭር ጊዜ ስራ የተቀጠርኩበት አንድ ቢሮ ፈረንጅ አለቃዬን ልተዋወቃት ቢሮዋ ሄድኩ፡፡ ‹‹ኦው!አዲሷ ኮንሰልታንት! ማነው ስምሽ?›› አለችኝ አየት አድርጋኝ፡፡ ‹‹ሕይወት እምሻው›› እኔን ሳይሆን የምታገላብጠውን የወረቀት ክምር አያየች ‹‹ኦህ…አጠር አድርጊውና ንገሪኝ ›› አለችኝ ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ‹‹ይቅርታ ምን አልሽኝ?›› አልኳትማንበብ ይቀጥሉ…

እህል ወይስ አረም ?

አሁን ባለንበት ዘመን ያለን የኢትዮጵያ ትውልድ የሀገራችንን ታሪክ፣ የሕዝቦች የእርስ በርስ ግንኙነትና የመሪዎቻችንን ሁኔታ ስንነጋገርና ስንጽፍ በአብዛኛው አሉታዊውን ነገር ይበልጥ ጎልቶ እንዲወጣ፣ ጥላቻ እንዲበቅል፣ ቂም እድሜ እንዲያገኝ፣ ልዩነት እንዲሰፋ፣ ጠብም ሥር እንዲሰድ በማድረግ ላይ የተመሠረተ ሆኖ ይታያል፡፡ ርግጥ ነው በሰውማንበብ ይቀጥሉ…

የ”ባቡር መጣ!?” ሁለት ጽንፎች !

‹‹…100 ዓመት የኋሊት… እስኪ አንዴ እንንደርደር በሸገር ጎዳና በለገሀር መንደር ባቡር አዲስ ነበር ? … አይደለም አይደለም ባቡርማ ነበር በምኒልክ ቀዬ በጣይቱ ዓለም አሁን ስለመጣ… ዘመናት ዘግይቶ የምን ግርግር ነው የምን እንቶፈንቶ? ይሄ ሁል ፍንጠዛ ይሄ ሁል ፍርጠጣ ‹ከባድ ባቡርማንበብ ይቀጥሉ…

እልፍ አእላፍ እኛ!

ቅዳሴው ሰማዩን ሰንጥቆት አረገ …. በደስታው ከበሮ ልብ አረገረገ መሬት አደይ ሞላች ውሽንፍሩ አባራ የቢራቢሮ አክናፍ እልፍ ቀለም ዘራ የፀሃይ ብርሃን በመንደሩ በራ….. እንዲህ ከጎረቤት እልልታ ያጀበው የዶሮ ወጥ ሽታ የነጭ ልብስ ወጋገን የሰዎች ቱማታ እንዲህ ወደማጀት የተከፋች እናት አይኗማንበብ ይቀጥሉ…

ዮዲት ጉዲት (Yodit Gudit) ማን ናት?

ከክርስቶስ ልደት በኋላ ፡ በአንደኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በንግሥት ህንደኬ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የጥምቀት ዜና በአራት ኛው ክፍለ ዘመን በኦብርሃና አጽብሐ ዘመነ መንግሥት በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ስብከት ተስፋፍቶ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስብከተ ወንጌልን አምኖ ጥምቀትንና ክርስትናን ተቀበለ፡፡ እጅግማንበብ ይቀጥሉ…

መጥተናል መጥተናል…. ቀጠሮ አክብረናል!

የቡሄ ጭፈራ እጅግ በጣም ‹‹አስገራሚ ››ከሚሆንባቸው ቦታወች አንዱ ኮንዶሚኒየም ህንፃወች ላይ ይመስለኛል !! ህፃናቱ በዱላወቻቸው አራተኛ ፎቅ ላይ ወለሉን እየደቁ ሲጨፍሩ ..ጠቅላላ ብሎኩ ይነቃነቃል ይንጋጋል …ህንፃው ከቆርቆሮ የተሰራ ነው የሚመስላችሁ ! በዛ ላይ ሰወች ኮንዶሚኒየም ቤት ሲኖሩ ከኢትዮጲያ ውጭ (ኧረማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ቡሔ(ቡሄ!)

“መጣና ባመቱ አረ እንደምን ሰነበቱ ክፈትልኝ በሩን የጌታዬን ሆያ-ሆዬ-ሆ…” ቡሄ! ወይንም ደብረ ታቦር በመላው ሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዓቢይ (ዋና) በዓላት አንዱ ነው። የዚህ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረማንበብ ይቀጥሉ…

ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን (1928-1998)

ጸጋዬ ገብረ መድህን (1928-1998) ባዳ ተብላ በምትታውቅ አምቦ ካተማ አካባቢ በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት ቀኃሥ ትምህርት ቤት ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ ትምህርታችውን ከገፉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952 እንደማንበብ ይቀጥሉ…

የመጀመሪያው የአማርኛ ልቦለድ

በ1908 ዓ.ም. በሮም ባሳተሟት ልቦለድ ታሪክ የፈጠራ ሥራቸው-በኢትዮዽያ የአማርኛ ዘመናዊ ሥነጽሑፍ መሥራች ካሰኛቸው ማእረግ ባሻገር በአፍሪካ ቋንቋዎችም ታሪክ- በሀገርኛ ቋንቋ በመጻፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ የሚል ምስክርነት አግኝተዋል። ደራሲው ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ሲሆኑ የልብወለድ ድረሰታቸው ‘ጦቢያ’ ትባላለች። አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በ1860 ዓ.ምማንበብ ይቀጥሉ…

ከአዳም ረታ ቃለ መጠይቅ

. . . አብዮት ሲመጣ (እንዲመጣ ሲደረግ) ልብ ወለድ መጽሃፍት ቢረባም ባይረባም በፓምፍሌት ተተኩ፡፡ ለመጀመሪያ ሰሞን ደስ የሚል ነገር ነበረው፡፡ ምክኒያቱም አዲስ ነው፡፡ (እዚህ ዘመን ላይ ቦታ ስለማይበቃን ልዝለለው እንጂ በሰፊው የምለው ኑዛዜያዊ ግለ ሂስ ነበር) ብዙ ሳልቆይ ሲጀመር መሰላቸቴንማንበብ ይቀጥሉ…

ኦባማ ኢትዮጲያ ሲመጡ የእራት ላይ ወጋቸው ምናባዊ ቅኝት

ኦባማ ኢትዮጲያ ሲመጡ . . . 40 ታዋቂ ሰዎችን ያናግራሉ (የእራት ላይ ወጋቸው ምናባዊ ቅኝት…እነሆ ) ‹‹እኛ ባቀናነው በሰራነው መንገድ የማንም ቀዠላ ተወላገደበት›› ቻይና …ትላለች ብለን ያሰብነው፡) አለም እንደሸንኮራ ተሰንጥቆ ወላ በካርቱን ወላ በአሽሙር የኦባማን ጉብኝት መተቸቱን ተያይዞታል ! ግማሹማንበብ ይቀጥሉ…

መቶ ብር ከየት ወዴት?

ትናንት ኣመሻሽ ላይ፤ ከYohanes Molla ጋር ተቀጣጥረን ተገናኘን ፡፡ካልዲስ ገብተን እኔ ኣንድ ፍንጃል ቡና ሳዝዝ ፤ ዮሀንስ ሲያቀብጠው ኣንድ ቡና እና የባራክ ኦባማን ጆሮ የሚያህል ቦምቦሊኖ ኣዘዘ፡፡ በመጨረሻ ኣስተናጋጂቱ የእዳችንን ደረሰኝ ኣምጥታ ጠረጴዛው መሀል ላይ ኣኖረችው ፡፡እሱ እኔ እስክከፍል ሲጠብቅማንበብ ይቀጥሉ…

የበላይ ዘለቀ እና የፋሺስት ኢጣሊያ ድርድር ታሪከ

በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ከባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አስኔ በወሎ ክፍለ ሐገር በቦረና ሳይንት አውራጃ በጫቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሩ ጉጣ ከተባለው ቀበሌ በ1904 ዓ.ም ተወለዱ። ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ሲወር በላይ ዘለቀ የ24 ዓመት ወጣት ነበር።ማንበብ ይቀጥሉ…

የዋለልኝ መኰንን አጭር የትግል ታሪክ

ዋለልኝ መኰንን በድሮው አጠራር በወሎ ጠቅላይ ግዛት በደብረሲና ወረዳ ከአባቱ ከአቶ መኰንን ካሣና ከእናቱ ከወይዘሮ ዘነበች ግዛው መጋቢት 11 ቀን 1938 ዓመተ ምህረት ተወለደ። ዋለልኝ መኰንንም በደሴ ከተማ በሚገኘው የንጉሥ ሚካኤል ተምህርት ቤት አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ከዚህም በመቀጠልማንበብ ይቀጥሉ…

ግርግር – አንድ

አውላቸው እባላለሁ … ተወልጀ ያደኩት እዚሁ ሰፈር ነው (ሌላ ምን መሄጃ አለኝ) ሰዎች ታሪክህን ንገረን ይሉኛል … ለማንም ታሪኬን ተናግሬ አላውቅም … እኔ,ኮ የሚገርመኝ እስቲ አሁን ማን ይሙት ይሄ ህዝብ ታሪክ ብርቅ ሁኖበት ነው የኔን ታሪክ ለመስማት የሚጓጓው ? …ማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ባፍሪካ የመጀመርያው የሳቅ ትምርት ቤት››

ባለፈው፣በቤተ-መንግስት መውጫ፣ በሸራተን መውረጃ መንገድ ላይ የተሰቀለ ፖስተር አየሁ፡፡ ‹‹ባፍሪካ የመጀመርያው የሳቅ ትምርት ቤት››ይላል፡፡የዘመኑን መንፈስ ከሚያሳዩ ተቋሞች ዋናው መሆን አለበት ብየ አሰብኩ፡፡በዘመኑ ዝም ብሎ መሳቅ ከባድ ነው፡፡እንድያውም በዘመኑ ከልቡ የሚስቅ ሰው ከተገኘ እንደ ስድስት ኪሎ አንበሳ በቅጽር ከልለን ልንጎበኘውና ልናስጎበኘውማንበብ ይቀጥሉ…

ዶሮ ብቻ ያልሆነው የዶሮ ወጥ

የዛሬ አመት አካባቢ ኬንያ ለስራ በቆየሁበት ወቅት የአመት በአላችን ንኡስ ምግብ፣ የገበታችን ንግስት ዶሮ ፤ከ ‹‹ማዘር ቤት›› እስከ አምስት ኮከብ ሆቴል አንዴ በሩዝ፣ አንዴ በኡጋሊ እየታጀበች፤ ከቀን ላብ አደር እስከ ቁንጮ ፖለቲከኛ አፍ እንደዋዛ በየእለቱ ስትገባ ገርሞኝ ነበር፡፡ ይሄን አይቼማንበብ ይቀጥሉ…

የገብረ ሕይወት ያለህ!

(Peace be up on him) “An economist should have cool mind and warm heart”! Professor Eshetu Chole በዘመኑ የምሁራን ልሂቃን ስብዕና፣ የንቃት ደረጃና ለሕዝባቸው ባላቸው ቁርጠኝነት (መስዋዕትነት እስከመክፈል ድረስ) ደካማነት የተበሳጨ ኢትጵያዊ ወጣት ፅሁፍ፡፡ ከላይ ለመግቢያነት የተጠቀምኩበትን የፕ/ር እሸቱ ጮሌንማንበብ ይቀጥሉ…

መንግስቱ ንዋይ – የሞት ፍርድ ከተወሰነባቸው በኋላ የተናገሩት ንግግር

መንግስቱ ንዋይ : መጋቢት 19 ፣ 1953 ዓ.ም የሞት ፍርድ ከተወሰነባቸው በኋላ የተናገሩት ንግግር እናንት ዳኞች የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለ ይግባኝ ተቀብያለሁ፡፡ ይግባኝ ብየ ጉዳየን የሚመለከትልኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈለግሁ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እንደማይሆን አውቃለውና በይግባኝማንበብ ይቀጥሉ…

ዝቋላ ሀገሩ የት ነው?

የዚህች ሀገር ባለቤቶች ሁላችንም ካልሆንን በቀር በተናጠል ማንም ባለ ግዛት ሊሆን አይችልም፡፡ ሉሲ አማራ ትሁን ኦሮሞ፣ አፋር ትሁን ሶማሌ፣ ጉሙዝ ትሆን ትግሬ፣ ወላይታ ትሁን ጋሞ የሚያውቅ የለም፡፡ በአኩስምና አካባቢው በተገኙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ነገሥታቱ የሚገዙትን ሀገር ሕዝቦች ስም ይዘረዝራሉ፡፡ እጅግማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...