ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ብቻ ሳይሆን ባለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ በግሉ በነጻነት አስቦ በአገር ጉዳይ ቁምነገሮች ላይ እንደዓቢይ አዲስ ነገርና የአስተሳሰብ እንከን የሌለበት ነገር ሲናገሩ አልሰማሁም፤ እኔ የሰማኋቸው ቅጭብጭቦች የዓቢይ ንግግሮች በሙሉ ሰውዬው የማሰብ ችሎታው የጠራ እንደሆነ ያረገጋግጡልኛል፤ በኢትዮጵያ ውስጥማንበብ ይቀጥሉ…
ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ሥልጣን
ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በፈቃዱ ከባለሥልጣንነት ተሰናበተ፤ ብዙ ሰዎች አስተ አስተያየታቸውን በቴሌቪዥን ሲገልጹ እንደሰማሁት ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በፈቃዱ ለመሰናበት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው ይላሉ፤ ይህ የማስታወስ ችሎታችንን ዝቅተኛነትን ያመለክታል፤ ጸሐፌ ትእዘዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድን ረስተናል! (ስለዚህ ጉዳይ በእንዘጭ! እምቦጭ! የኢትዮጵያ ጉዞ ላይ ዘርዘርማንበብ ይቀጥሉ…
ተጠየቅ መስከረም
አዲሱ ዓመት በእውነት አዲስ ይሁንላችሁ! ለሁላችንም የነጻነት፣የሰላም፣ የፍቅር፣ የሥራና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን ተጠየቅ መስከረም! ተጠየቅ መስከረም፤ ዛሬስ ዋዛ የለም አንተን ለመቀበል እንቁጣጣሽ እያልን፤ ከርስ እንሞላለን፤ እንሳከራለን፤ እንጨፍራለን፡፡ አልገባኝም እኔን አንተ መወደድህ፤ ስትገባ ስትወጣ ድግስ መቀበልህ፤ ዶሮው፤ በጉ፤ ሰንጋው ይታረድልሃል፤ ርጥብማንበብ ይቀጥሉ…
“ወልቃይት የማን ነው?” የማይረባ ጥያቄ
አንድ በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገውማንበብ ይቀጥሉ…
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰውማንበብ ይቀጥሉ…
ስለችጋር
ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ ‹‹እየበሉ›› በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ ችጋር የሚያጠቃው ማንንማንበብ ይቀጥሉ…