ሁሉም ችግር ያወራል። ሁሉም ወቃሽ ነው። ሁሉም ተጠቅቻለሁ ባይ – ሁሉም በደል ቆጣሪ ነው። እነከሌ ይራገማሉ። እነከሌም ያሳቅላሉ። ሁሉም ነገድ የተገፊነት ተረክ አለው። ሁሉም ጠላት እና ጨቋኝ አለው፤ ሁሉም በጋራ ይከሳል.. ሁሉም በጅምላ ይከሰሳል፤ ‘ጸረ ሰላም፣ ጨቋኝ፣ ሴረኛ፣ ለውጥ አደናቃፊ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ጥሪት – ጥረት – ጥምረት
ቤተሰብ ውስጥ ምስቅልቅል የሚፈጠረው ወላጆች በተፈጥሮ ሞት ኑረትን ሲሰናበቱ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ልጆች በእናት አባት ሕላዌ ወቅት ያልታያቸው የሃብት ክፍፍል ትዝ የሚላቸው ያን ጊዜ በመሆኑ ነው። ብዙ ጊዜ የሃብት ቅርምት ቤተሰብን ባላንጣ ያደርጋል። ከአንድ አብራክ ተከፍለው ከአንድ ማሕጸን በቅለው ክፉማንበብ ይቀጥሉ…
ማን ይቀስቅሰን?
“አጥር መስራት የውሻ ተግባር ነው” ~ የገዳ ስርዓት — እንደ ማሕበረሰብ አንቀላፍተናል… ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነን… ለሞት የቀረበ እንቅልፍ… ችግሩ ማንቀላፋታችንን አናውቅም… ማንቀላፋታችንን ስላላወቅን የተኛንበትንም አናውቅም… ማንቀላፋታችን ደግሞ በሌባ አስደፍሮናል… ችግሩ መሰረቃችንን አናውቅም… ወይም ግድ የለንም… የተዘረፍነው ግን አማናዊነት ነው…ማንበብ ይቀጥሉ…
የመደመር ነገር…
፩ – Solid vs Stranded ___ ስለ ኤሌክትሪክ ስናወራ በጭራሽ የማንዘለው አንድ ነገር Wire (Conductor) ነው.. ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ (ሽቦ) እንለዋለን… ዋየር በሚሰራበት ቁስ በርካታ በአዘገጃጀት ደግሞ ሁለት መልክ አለው… Solid (አንድ ‘ነጠላ’ ሽቦ) እና Stranded (የቀጫጭን ብዙ ሽቦ እጅብ)… እንደምንሰራውማንበብ ይቀጥሉ…
የልደት ቀን ማስታወሻ
“And in the end it’s not the years in your life that count; it’s the life in your years.” ~ Abraham Lincoln ___ የብዙዎቻችን ምኞት ረጅም ዓመት መኖር ነው… ብዙ ዕድሜ ማስቆጠር… ትልቁ ምርቃታችን ‘ዕድሜ ይስጥህ’ አይደል?… ‘ዋናው ጤና’ ስንልምማንበብ ይቀጥሉ…
ከእንቅልፍ መልስ…
[ዳንሱን ከዳንሰኛው መነጠል ይቻላልን?] ___ ስለ ማንነት ሲነሳ በመስታወት ውስጥ ‘ፊቱን’ እያየ የሚመሰጥ ሰው ነው በዓይነ ሕሊናዬ የሚታየኝ… የናርሲስ ቢጤ … ናርሲስ በግሪክ ሚቲዮሎጂ ገጾች በውሃ ውስጥ የሚያየውን ምስል ለማምለክ ጥቂት የቀረው ሰው ሆኖ ተስሏል… በማንነት ጉዳይ ሁላችንም ናርሲስት ነን…ማንበብ ይቀጥሉ…
March 8 – ሴቶች የሚነቆሩበት ቀን
አንድ አድራጎት አስደማሚ የሚሆነው አድራጎቱ በዓለም ላይ “የመጀመሪያ” ሲሆን አልያም የአድራጊው ድርጊቱን መፈጸም ከአዕምሮ በላይ ሲሆን ነው… የኖረና የነበረን ጉዳይ እጹብ ድንቅ አድርጎ መሸላለም ግን አንድም ለአድራጊው የተሰጠን ዝቅተኛ ግምት አልያም ድርጊቱን ለማመናፈስ የተደረገን ጥረት ያሳያል… ___ አውሮፕላን በሴቶች ሲበርማንበብ ይቀጥሉ…
Connecting the dots
ልጅ እያለሁ ነጥቦችን በማዋደድ ጨዋታ እዝናና ነበር… በአንዳንድ ጋዜጣና መጽሔቶች የጀርባ ገጽ ላይ በተንተን ያሉ ጥቂት ነጠብጣቦች ይቀመጡና አንባቢያን በነጠላ መስመር ሲያገናኟቸው አንዳች ትርጉም ያለው ቅርጽ እንዲሰጡ ሆነው ይታተማሉ… ነገሩ መዝናኛ ቢሆንም አስተውሎ ላየው አንዳች እውነት ሹክ ማለቱ አይቀርም… ትላልቅማንበብ ይቀጥሉ…
እኛ _ ሙዚቃ _ ኑረት
ሙዚቃ የየሰው የኑረት እውነት፣ የመስተጋብራችን ቀና ትርክት፣ የጉድለታችን ሙላት፣ የስህተታችን ጥቁምት… ይልቁንም የስክነታችን አብነት ሲሆን የነፍስን ጆሮ ያነቃል – የሥጋን ትፍስህት ያመጥቃል… አንዳንድ ሙዚቃዎች በጆሮ ከመደመጥም በላይ ለዓይን የውበት ቁንጮ፣ ለምላስ የጣዕም ልኬት፣ ለአፍንጫ መልካም መዓዛ የሚፈጥሩ ሆነው አድማጭን ያስደምማሉ…ማንበብ ይቀጥሉ…
Butterfly Effect
ተተንባይ ኑረት የሌላቸውን ሁነቶች የሚተነትነው ሒሳባዊ ንድፈ-ሃሳብ Chaos Theory ይባላል… ትወራው በዚህ ስም ከመጠራቱ በፊት መገለጫ ባሕሪያቱን ለመተንተን የመጀመሪያ ነው የሚባልለት የሒሳብ ሊቅ Henri Poincaré ይባላል… ፈረንሳዊ ነው… “It may happen that small differences in the initial conditions produce veryማንበብ ይቀጥሉ…
ነፃ ነፃነት
“ነፃ ሆነን ብንፈጠርም በየሄድንበት እንደታሰርን ነው” ይላል ሩሶ… “Man is born free, and everywhere he is in chains. One man thinks himself the master of others, but remains more of a slave than they are.” ~ Jean Jacques Rousseau …ማንበብ ይቀጥሉ…
የአብሲት ተራ ወጎች
ልጅነቴ ከተጓዘባቸው ፈለጎች አንዱ ‘እንጀራ መሸጥ’ ነው። ቡታጅራ ውስጥ ‘ሶርሴ ተራ’ በምትባል የገበያ ቦታ የእማማን ለምለም እንጀራ ከፈላጊው ጋር አገናኝ ነበር። አንድ ሰው ለብቻው የማይጨርሰውን ‘ግብዳ’ እንጀራ [ውሻ በቁልቁለት የማይስበው የሚባልለትን] የብር አምስትና አራት ሽጬያለሁ። 5ቱ ሁለት ብር ሲገባም በዚያማንበብ ይቀጥሉ…
ላንችይቱ
[Come out of the circle of time and into the circle of love. ~ Rumi] ~ ምንኛ ነው ግን… ‘የነገን ማወቅ ፈለግሁኝ’ ብሎ ምኞት… ዛሬ ላይ ሳይቆሙ ወደ ነግ መጎተት… የሚያውቁትን ጥለው በማያውቁት መሳብ… ምንኛ ነው ‘ነገን ላየው እጓጓለሁ’ ማለት…ማንበብ ይቀጥሉ…
ድልድዮቹን ተውልን
እመሃል ላይ ተገምሰው ማዶ ለማዶ የሚያተያዩን ሰባራ ድልድዮች እየበዙ ነው… አንዳንዶቹን ሆን ብለን ሰብረናቸዋል… አንዳንዶቹ በሌሎች ሰንኮፎቻችን ዳፋ ተሰብረዋል… ሌሎቹን ግን መሰበራቸውን እንኳ አልተረዳንም… ~ አንዳንዶች የሚሰብሩትን ድልድይ ፋይዳ በወቅት ስሜታቸው ትኩሳት ውስጥ ብቻ ስለሚመዝኑ የሰባሪነት ወኔ እንጂ የአስተዋይነት ስክነትማንበብ ይቀጥሉ…
Nothingness!!
መስመር መስራት ስትጀምር ወዲህና ወዲያን ትፈጥራለህ… አጥር መገንባት ስትጀምር ውስጥና ውጭ ትፈጥራለህ… ፍርድ መስጠት ስትጀምር ክፉና ደግ ትፈጥራለህ… በመስመር – አጥርና ፍርድህ ምክንያት የልዩነት ዜማ ሰርክ ይቀነቀናል… እንዲህ ‘የሆኑ’ እና እንዲያ ‘ያልሆኑ’ ክልል ይበጃል… ‘የኛ’ እና ‘የእነርሱ’ ምድብ ይሰራል። ሕይወትማንበብ ይቀጥሉ…
ልጅነቴን አፋልጉኝ
ማደግ በመሰለኝ ረግረግ ውስጥ የጠፋች ልጅነቴን አፋልጉኝ – ማወቅ በመሰለኝ ጥልቅ ውስጥ የተደበቀች ልጅነቴን አፋልጉኝ – ከድቅድቅ ጽልመት ውስጥ የዘነጋሁዋትን እውነት አፋልጉኝ… ~ ዕድሜ የሥጋ ኑረት መስፈሪያ እንጂ የውዷ ሕይወት መግለጫ አይደለም… ሕይወቴ ልጅነቴ ነው… ዕድሜ ደግሞ የልጅነቴን ንጽሕና የነጠቀኝማንበብ ይቀጥሉ…
ጠፍታ አገኘችኝ
የደመናው ጽልማሞት በዝናብ ፍርሃትና በቀጠሮ አለማክበር ስጋት መሃል አዕምሮዬን እያላጋብኝ ወደ ታክሲ መያዣው የማደርገውን ግስጋሴ ትቼ ቅርቤ ወዳለ ካፌ ዘለቅሁ… ፒያሳ ነኝ… ከመቀመጤ ሸገር እሪ ብላ አነባች… በጣም ከባድ ዝናብ መውረድ ጀመረ… “ሸበሌ እንገናኝ” ነበር ያለችኝ… ፍቅረኛዬ ናት… ‘ጥብቅ ጉዳይ’ማንበብ ይቀጥሉ…
ተ ላ ቀ ቅ
ከሕላዌው ጽንፍ አልባ እውነት ራስን የመነጠል ግብግብ። ከሆኑት መሆን ሌላ መሆንታን መሻት። ከአማናዊው እውነት ተናጥሎ በሃሳብ ደሴት መገለል። የኔ/ኛ፣ የእነርሱ፣ የነዚያ ባይነት ፍረጃ። ነኝነት ከሌላው የተለየ መሆንን ሲሰብክ መሆን /Being/ ቅዠት ውስጥ ይቧችራል። ነኝነት ጥግ ሲያሻትት የመሆን ቀለም ይደበዝዛል። የሆንከውንማንበብ ይቀጥሉ…
የሱፍ አበባ ነኝ
የብርሃን ጥገኛ ነኝ… እኔዬ ከብርሃን ውጭ ውበት የላትም… ብርሃን ሳጣ ይጨንቀኛል… ቅጠሎቼ ይጠነዝላሉ… ቅርንጫፎቼ ይኮሰምናሉ… የሱፍ አበባ ነኝ… በሕላዌ ገመድ ለተንጠለጠለችው ኑረት ጨለማና ብርሃን የማይዘለሉ ሃቆች ቢሆኑም እኔ ግን በብርሃን ፍቅር እንደተለከፍኩ አለሁ… ልክፍቱ “..መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ ስላልኩ የሚለቅማንበብ ይቀጥሉ…