የእቴጌ እና የሂትለር ፎቶ

ባየኋቸው ቁጥር ግርርም ከሚሉኝ ታሪካዊ ፎቶዎች አንዱን ላካፍልዎት፡፡ በ1935 የተነሣው ይህ ፎቶው የተገኘው ባሶሼትድ ፕሬስ መዝገብ ውስጥ ነው፡፡ በፎቶው ላይ ለጊዜው ስሙን ያልደረስኩበት ሠዓሊ የግርማዊት እቴጌ መነን እና የአዶልፍ ሂትለርን ሥዕል ሲሸጥ ይታያል፡፡ በፎቶው ጀርባ ላይ እንደ ተገለጸው ከሆነ፤የጀርመኑ አምባገነንማንበብ ይቀጥሉ…

ባለ መሰንቆውና ባለ ወለሎው

“ሮድ ደሴት” በተባለ አገር ውስጥ እንደ እንደምኖር የነገርኩት ጓደኛየ “እና ባሣ አጥማጅነት ነው የምትተዳደረው?” ብሎኛል፡፡ ሮድ ደሴት አበሻ እጥረት ክፉኛ ከሚያጠቃቸው ክልሎች አንዱ ነው ፡፡ አሁን ምድሩም ሰማዩም ሰውም ነጭ ነው፡፡ ያገር ሰው በጣም ይናፍቀኛል፡፡ የሆነ ያበሻ ዓይነ ውሃ ያለው አልፎማንበብ ይቀጥሉ…

ነጋ

የግዜር ስውር መዳፍ፣ ልክ እንደ ፓፒረስ፣እንደ ግብጦች መጣፍ ወይም እንደ ጥንቱ፤ ያባ ጅፋር ምንጣፍ ጨለማውን ስቦ፤ በወግ ሸበለለ ሰማይ፣የጠፈር ዓይን፤ ብርሃን ተኳለ ከዶሮ ጨኸት ውስጥ፤ አዲስ ጎህ ተወልዶ ፍጥረቱ በሞላ፤ ማርያም ማርያም አለ፤ ነጋ አልጋየን ሰብሬ አንሶላ ተርትሬ ባዲሱ ጉልበቴማንበብ ይቀጥሉ…

የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ

አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ በዘፈን አንደኛ ሙሉቀን መለሰ (እስከመቸ ድረስ ጥላሁን ገሰሰ) የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ? Lol የህዳሴውን ግድብ ወደ “ህዳሴው ገደል” ያሸጋገረውን ስምምነት የፈረመው ሰውየ“ እጁን ለቁርጥማት፤ ደረቱን ለውጋት“ እንዲዳርገው በመመረቅ ወደ ሰላምታየ እገባለሁ፡፡ እንዴት ናችሁ፤ ያልታደላችሁ? እኔ በህይወቴማንበብ ይቀጥሉ…

“ገጽታ ግንባታ?”

ባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…

የተቸካዮች ምክር ቤት

ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን ዘና ለማረግማንበብ ይቀጥሉ…

ነፍስ ይማር!!

በፍቅር ሰበብ; ሴት ስለሚገድሉ ወንዶች የሚወጡ ዜናዎችን እንሰማለን፡፡ በወጣትነታቸው የተቀጠፉ ጽጌሬዳዎች ያሳዝናሉ፡፡ ነፍስ ይማር!! በፍቅር ሰበብ መግደል በተለይ የወንዶች ችግር ይመስለኛል ፡፡ ሴቶች በወደዱት ሰው መገፋትን በእንባቸው ያጥቡታል፡፡ ለወንድ ግን ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም፡፡ ለብዙ ወንዶች ከሴት ጋር የሚደረግ ግኑኝነትማንበብ ይቀጥሉ…

መቶ ብር ከየት ወዴት?

ትናንት ኣመሻሽ ላይ፤ ከYohanes Molla ጋር ተቀጣጥረን ተገናኘን ፡፡ካልዲስ ገብተን እኔ ኣንድ ፍንጃል ቡና ሳዝዝ ፤ ዮሀንስ ሲያቀብጠው ኣንድ ቡና እና የባራክ ኦባማን ጆሮ የሚያህል ቦምቦሊኖ ኣዘዘ፡፡ በመጨረሻ ኣስተናጋጂቱ የእዳችንን ደረሰኝ ኣምጥታ ጠረጴዛው መሀል ላይ ኣኖረችው ፡፡እሱ እኔ እስክከፍል ሲጠብቅማንበብ ይቀጥሉ…

”በሥጋና በግብረስጋ ቀልድ የለም”

ዜና እናሰማለን፤ ዜናውን ከማሰማታችን በፊት ኣካባቢውን በስጋት ዞር ዞር ብለን እናያለን! ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሚያደርጉት ጉብኝት ጥንቃቄ ሲባል የቦሌና ያካባቢው ነዋሪዎች ሽሮሜዳ እንዲሰፍሩ ተደረገ፡፡ President Barak Obama, welcome to the land of fair and free erection! ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሸገርማንበብ ይቀጥሉ…

ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህጻን

በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶችማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ስንኞች

ከጥቂት ኣመታት በፊት የሆኑ ሸበቶ ሽማግሌ እኔንና ኣብሮኣደጌን ኣንተነህ ይግዛውን ኣፈላልገው ኣገኙንና ለጠቅላይ ሚኒስተር መለስ የሚላክ ኣቤቱታ እንድንጽፍላቸው ማለዱን፡፡የሆነ ጉልቤ በድሏቸዋል፡፡ምሬት ኣባርሮት ወደዚህ ገጽ የመጣውን ኣንባቢ ተጨማሪ ምሬት ላለማካፈል የሰውየውን በደል ኣልጽፈውም፡፡ ተገናኝተን ስንጨዋወት ስለግጥም ተነሳና ኣንድ ግጥም በቃሌ እንድወጣላቸውማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ተድላ

የጥንቲቱ ፋርስ ካፈራቻቸው ባለቅኔዎች መካከል ኣንዱ ኦመር ካያም ነው፡፡ ፈላስፋ ሳይንቲስት እና የተዋጣለት የሂሳብ ሊቅ ነው፡፡ሩባኣያት የሚል የግጥም ዘይቤ ፈልስፏል፡፡ሩባያት ኣራት መሥመር ያለው ሲሆን ከሦስተኛው መሥመር በቀር ሌሎች ቤት ይመታሉ ፡፡ ኦመር ካያም መናፍቅ ነበር፡፡ ትንሳኤ ሙታን መኖሩን ይጠራጠራል፡፡ህይወት ከስንዝሮማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ባፍሪካ የመጀመርያው የሳቅ ትምርት ቤት››

ባለፈው፣በቤተ-መንግስት መውጫ፣ በሸራተን መውረጃ መንገድ ላይ የተሰቀለ ፖስተር አየሁ፡፡ ‹‹ባፍሪካ የመጀመርያው የሳቅ ትምርት ቤት››ይላል፡፡የዘመኑን መንፈስ ከሚያሳዩ ተቋሞች ዋናው መሆን አለበት ብየ አሰብኩ፡፡በዘመኑ ዝም ብሎ መሳቅ ከባድ ነው፡፡እንድያውም በዘመኑ ከልቡ የሚስቅ ሰው ከተገኘ እንደ ስድስት ኪሎ አንበሳ በቅጽር ከልለን ልንጎበኘውና ልናስጎበኘውማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...