ትናንት በለጠፍኩት አንድ ጽሑፍ ግንቦት 19/1983 በለንደን ስለተከፈተው ኮንፈረንስ ተናግሬ ነበር። እስቲ አሁን ደግሞ የለንደን ኮንፈረንስ ቀጥተኛ ውጤት ስለነበረው የያኔው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እናውጋ። ከግንቦት 19-20/1983 በተካሄደው የለንደን ኮንፈረንስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ የነበሩት አዲስ አበባን ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረውማንበብ ይቀጥሉ…
EPDA – በመጨረሻው ሰዓት የተገኘ አደገኛ ድርጅት
የደርግ መንግሥትን ለመደምሰስ ሲታገሉ የነበሩ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች ነበሩ። ኢህአዴግ፣ ኦነግ እና ኢህአፓን የመሳሰሉት የታጠቀ ሰራዊት አስከትተው ሲዋጉ ነበር። አንዳንዶቹ ግን ሰራዊት ሳይኖራቸው በደርግ መንግሥት ላይ አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎችንና ስውር የውስጥ ጥቃቶችን ሲያካሂዱ ነበር። ከነዚህም ውስጥ በብዙዎች ዘንድ ልዩ ትዝታንማንበብ ይቀጥሉ…
የሼኽ ሙኽታር ምክር
በገለምሶ ዋናው መስጂድ ከ60 ዓመታት በላይ በኢማምነት ስላገለገሉት ሼኽ ሙኽታር ዐሊዪ ብዙ ጊዜ ጽፌአለሁ። ለዛሬ ደግሞ እሳቸው ያጫወቱን አንድ ግሩም ተረት ላካፍላችሁ። ተረቱ የሰው ልጅ ልኩን አውቆ እንዲኖር እና አላህ በሰጠው ኒዕማ አመሰጋኝ እንዲሆን የሚያስተምር ነው። በአንዲት መንደር የሚኖር አንድማንበብ ይቀጥሉ…
ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ ሲተረጎም (1961)
ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ እንዲተረጎም ትዕዛዝ ያስተላለፉት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ነበሩ። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ትእዛዙን ያስተላለፉት ሐምሌ 18/1958 በተጻፈ ደብዳቤ ነበር። የንጉሡን ደብዳቤ በመንተራሰስ ስራው እንዲጀመር ያደረጉት ደግሞ በወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌ ናቸው። ዶ/ር ምናሴ በተርጓሚነት የመረጡት ከአል-አዝሃርማንበብ ይቀጥሉ…
የየመኒዎች ጨዋታ
በዚህ ወቅት የቅርብ ጓደኛዬ የመኒው ኮሎኔል ሙሐመድ አል ሐይደሪ ነው። ረመዳንን በአብዛኛው አንድ ቤት ነበር ያሳለፍነው። አሁንም አብረን ነው የምንውለው። በተለይ ከሰዓት አብረን ስንጫወት ነው የምናሳልፈው። በርካታ ቁም ነገሮችንም ከእርሱ እየተማርኩ ነው። —- ጦርነትን ሸሽቶ ከሀገሩ የወጣው ሙሐመድ አል ሐይደሪማንበብ ይቀጥሉ…
ዐምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ” (ክፍል ሁለት)
የጥንት ግብጻዊያን አንድ ልማድ ነበራቸው። በየዓመቱ ቆንጆ ልጃገረድ ይመርጡና ለአባይ ወንዝ (ኒል/ናይል) ይሰውለት ነበረ። እነዚያ ግብጻዊያን ናይል በየዓመቱ መስዋዕቱን ካላገኘ ውሃውን ይቋጥርብናል የሚል እምነት ነበራቸው። አምር ኢብን ኣስ ሀገሪቱን በያዘ በጥቂት ወራት ውስጥም ግብጻዊያኑ ለወንዙ መስዋእቱን ለማቅረብ እንደሚፈልጉ ነገሩት። አምርማንበብ ይቀጥሉ…
አምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ”
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ለአፍሪቃ አህጉር የመጀመሪያ የሆነውን መስጊድ ነው። ይህ መስጊድ የተሰራው በ641 ሲሆን የሚገኘውም በግብፅ መዲና ካይሮ ውስጥ ነው። መስጊዱ የሚጠራው በመስራቹ በ“አምር ኢብን ኣስ” ስም ነው። ይሁንና አምር እና ጓዶቹ መስጊዱን የሰሩት በአል-ፉስጣጥ እንጂ በካይሮ አልነበረም። ታዲያ መስጊዱንማንበብ ይቀጥሉ…
ክርስቲያኗ ፍቅረኛዬ ናፈቀችኝ!
ረመዳን ሲመጣ ከማስታውሳቸው ሰዎች አንዷ ናት። በእድሜዋ ከኔ በሁለት ዓመት ታንሳለች። ከ1996-2004 በነበረው ዘመን የኔ ምርጥ ጓደኛ እርሷ ነበረች። ሌላ ሴት የመጋበዝ ባህል አልነበረኝም። እርሷን ግን ከፒያሳው ኡመር ኻያም ጀምሮ እስከ ውድ ሬስቶራንቶች ድረስ እየወሰድኳት እጋብዛት ነበር። እርሷም አጸፋዋን በመክፈሉማንበብ ይቀጥሉ…
“ለይለቱል በድር” እና “በርቲ በርቲ” በሀረር
ረመዳንን የሚጾም ሰው ስለ“ለይለቱል ቀድር” ማንነት በሚገባ ያውቃል ብዬ እገምታለሁ። “ለይቱል በድር”ን ግን ብዙዎቻችሁ ላታውቁት ትችላላችሁ። ስለዚህ በዛሬው የረመዳን ወጋችን “ሀረር ጌይ” በተሰኘው መጽሐፌ ስለ “ለይለቱል በድር” የጻፍኩትን አጋራችኋሁ። ***** “በድሪ” እና “በድሪያ” እኔ በተወለድኩበት አካባቢ በጣም ከሚታወቁት ስሞች መካከልማንበብ ይቀጥሉ…
ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል እብሪት ግን ለውድቀት ይዳርጋል
ጎሽ! ጎሽ! እሰይ —- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን በየእለቱ እየወደድኩት ነው። ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ያለኝ አድናቆትም እየናረብኝ ነው። ታዲያ አቶ ኢሳያስ ዛሬ ያደረገውን አስገራሚ ነገር ልብ ብላችኋልን? ፊርማውን ሲፈርም እኮ የባድመ ጉዳይ ከቁም ነገር ተቆጥሮ አልተነሳም። ድሮስ? ድሮማ “ባድመን ካላስረከባችሁን ድርድርማንበብ ይቀጥሉ…
በባድመ እና የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዙሪያ
የኢትዮጵያ ኤርትራ የድንበር ግጭት የተከሰተበት ፍጥነት በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን ጭሮ እንደነበረ ይታወሳል። ጥቂት የማይባለው የህብረተሰብ ክፍልም “የድንበር ግጭቱ ለማስመሰል የቀረበ ነው፣ የግጭቱ መንስኤ ሻዕቢያ ከኢትዮጵያ ሲያገኘው በነበረው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ በሩ መዘጋቱ ነው” የሚል እምነት አዳብሮ እንደነበረ ይታወቃል። ኢኮኖሚውን አስታክከውማንበብ ይቀጥሉ…
ትዝታ ዘ-አባዱላ
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በ1993 ለሁለት በተከፈለበት ወቅት ገዥዎቻችን ያልጠበቁት አብዮት በኦህዴድ ውስጥም ፈንድቶ ነበር። በክስተቱ የደነገጠው አቶ መለስ ዜናዊ የኦህዴድ ገዲም ካድሬዎችን ተጠቅሞ አብዮቱን መቆጣጠር ተሳነው። ከሚተማመንባቸው የኦህዴድ ጓዶቹ መካከል ከፊሉ እየወላወለ፣ ከፊሉ እየከዳ አስቸገረው። በነገሩ በጣም ተጨንቆ ሲጠበብ አንድማንበብ ይቀጥሉ…
“ኦሮማይ” እና በዓሉ ግርማ
ኦሮማይ ከልቡ መጽሐፍ ነው። በአማርኛ ልብ-ወለድ መጻሕፍት (Novel) ታሪክ በጣም አነጋጋሪውና አከራካሪው መጽሐፍ ነው። እስከ አሁን ድረስ የህዝብ ፍቅር ካልተነፈጋቸው ጥቂት መጻሕፍት አንዱም ነው። በህይወቴ ብዙ ጊዜ እየደጋገምኩ ካነበብኳቸው መጻሕፍት መካከልም በመጀመሪያው ረድፍ ይሰለፋል። ይሁንና ሰዎች ለዚህ መጽሐፍ ያላቸው አድናቆትማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል አስራ አንድ)
ክፍል አስራ አንድ፡ “የጨለማው መስከረም” (Black September) የዮርዳኖሱ ንጉሥ ሑሴን የፍልስጥኤም ድርጅቶች እስከ መስከረም 20/1970 ከዮርዳኖስ ግዛት እንዲወጡ ያዘዙበት ውሳኔ ከዐረቡ ዓለም ውግዘት ሲያከትልባቸው ፈራ ተባ ማለት ጀመሩ። በዚህን ጊዜም የጸጥታ ኃይሎቻቸው ንጉሡን ሳያማክሩ አንድ ድራማ አቀናበሩ። በዚህም መሠረት የዮርዳኖስማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል አስር)
ክፍል አስር፡ በ“ጨለማው መስከረም” ዋዜማ ዮርዳኖስ የፍልስጥኤም ታጋዮች በ1968 እና በ1969 ያካሄዷቸውን ጠለፋዎች “አስደናቂ ጀግንነት ነው” በማለት ካወደሱት ሀገራት አንዷ ነበረች። ከዓመት በኋላ የPFLP አባላትና ደጋፊዎች ሶስት አውሮፕላኖችን ጠልፈው ወደ ግዛቷ ሲያመጡ ግን በጣም ነበር የተቆጣችው። የግንባሩ መሪዎች በግዛቷ የነበሩትንማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ዘጠኝ)
ክፍል ዘጠኝ፡ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ ከዚህ ቀደም እንደገለጽነው የPFLP መሪዎች የአውሮፕላን ጠለፋዎችን ለማካሄድ የወሰኑት “ለፍልስጥኤማዊያን ትግል ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማስገኘትና ለጥያቄአችን የተሻለ መደመጥን ለመፍጠር ያስችላሉ” በማለት ነበር። በእርግጥም አመራሩ እንደጠበቀው በተከታታይ የተካሄዱት የአውሮፕላን ጠለፋዎች ግንባሩን በዓለም ህዝብ ዘንድ ታዋቂማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ስምንት)
ክፍል ስምንት፡ በወዛደራዊ ዓለም አቀፋዊነት መርህ ባለፈው ትረካችን የጠቀስናቸው ሶስት አውሮፕላኖች በተጠለፉበት ዕለት (መስከረም 6/1970) ለይላ ኻሊድም በሌላ የጠለፋ ኦፕሬሽን እንድትሳተፍ ታዝዛ ነበር። ለይላ ጠለፋውን እንድታከናውን የታዘዘችው ከሁለት ፍልስጥኤማዊያን እና ፓትሪክ አርጌሎ ከሚባል የኒካራጓ ተወላጅ ጋር ነበር። ፓትሪክ አርጌሎ ከደቡብማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ሰባት)
ክፍል ሰባት፡ ተከታታዮቹ ኦፕሬሽኖች PFLP በዚያው ዓመት (በ1969) ውስጥ ጥቃቱን በማስፋት “የወራሪዋ እስራኤል ተባባሪዎች ናቸው” የሚላቸውን ሀገራት በሙሉ ዒላማ ማድረግ ጀመረ። በዚሁ መሠረት “ፊዳይን” የሚባሉ ኮማንዶዎቹን በብሪታኒያና በሌሎች የምዕራብ ሀገራት በማሰማራት ልዩ ልዩ ጥቃቶችን ፈጸመ። “ወዝ አደራዊ ዓለም አቀፋዊነት” በሚባለውማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል አምስት)
ክፍል አምስት፡ ለይላ ኻሊድ እና የፍልስጥኤማዊያን ትግል የPFLP አመራር ታጋዮቹ በ1968 ያካሄዱት የአውሮፕላን ጠለፋ የፍልስጥኤማዊያንን ትግል ለማስተዋወቅ እንደረዳ ተገነዝቧል። በመሆኑም በቀጣዩ ዓመት (1969) ከመጀመሪያው ጠለፋ በበለጠ ሁኔታ ብዙዎችን ሊያነጋግር የሚችል ኦፕሬሽን እንዲካሄድ ወሰነ። የግንባሩ የወታደራዊ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የነበረው ዶ/ርማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ስድስት)
ክፍል ስድስት፡ ለይላ ኻሊድ በዓለም ህዝብ ፊት በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል ብዙዎቹ ስለአውሮፕላን ጠለፋ ሰምተዋል። ይሁን እንጂ ጠላፊዋ ሴት ስትሆንባቸው በጣም ነበር የተደናገሩት። ይህም የሆነው በዘመኑ ወንዶች እንጂ ሴቶች በአውሮፕላን ጠለፋ ሲሳተፉ ስላልታየ ነው። በዚህም የተነሳ ተሳፋሪዎቹ ከመደናገጥ ይልቅማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል አራት)
ክፍል አራት፡ ትግሉን ለዓለም ማኅበረሰብ ማስተዋወቅ በጆርጅ ሐበሽ የሚመራው PFLP እስራኤልን በትጥቅ ትግል ብቻ ለመፋለም የወሰነ ድርጅት ነበር። በመሆኑም በወቅቱ ከስድስት መቶ ያልበለጡ ተዋጊዎቹን በማሰማራት በፍልስጥኤም ግዛቶች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያደርግ ጀመር። በሊባኖስ፣ በዮርዳኖስ፣ በሶሪያ እና በሌሎች የዐረብ ሀገራት የተበተኑት ፍልስጥኤማዊያንማንበብ ይቀጥሉ…
ሶማሊ እና ኦሮሞ ወንድማማቾች ናቸው!
ታሪካችን የመረዳዳት እንጂ የግጭት አልነበረም። ታሪካችን የአብሮ መኖር እንጂ የመበላላት አልነበረም። ታሪካችን የመፋቀር እንጂ የመናቆር አልነበረም። እጅግ በሚገርም ሁኔታ አንዳችን ለሌላው መብትና ጥቅም መከበር ስንል አብረን ተዋግተናል። ህይወታችንን ሰውተናል። ለምሳሌ ታዋቂ የኦሮሞ አርበኞች የሆኑት ኤሌሞ ቂልጡ (ሐሰን ኢብራሂም)፣ እና ሁንዴማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ሶስት)
ክፍል ሶስት፡ የአዲስ ግንባር ምሥረታ ጆርጅ ሐበሽ እና ዋዲ ሀዳድ ሶሪያን እንደ ዋነኛ ቤዝ በመጠቀም ትግላቸውን በማካሄድ ላይ ሳሉ በ1962 የባዝ ፓርቲ አፍቃሪ የሆኑ መኮንኖች በሳላህ አል-ቢጣር መሪነት የሀገሪቱን መንግሥት ገለበጡ። ይህም የሶሪያ መንግስት ይከተለው በነበረው ፖሊሲ ላይ ትልቅ ለውጥማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ሁለት)
ቀዳሚው የትግል ምዕራፍ ዶ/ር ጆርጅ ሐበሽ እና ዶ/ር ዋዲ ሀዳድ በቀዳሚዎቹ ዓመታት አዲሱን ድርጅታቸውን በማስተዋወቅና አባላትን በመመልመል ላይ ነበር ያተኮሩት። በዚህ መሠረት በተለያዩ ሀገራት ወደሚገኙት የፍልስጥኤም ኮሚኒቲዎች ወኪሎቻቸውን እየላኩ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን አስተዋውቀዋል። አባላትን እየመለመሉ በድርጅቱ ህዋሳት ስር አዋቅረዋል። ከተለያዩ መንግሥታትማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ
ክፍል አንድ፡ የትግል ጅማሮ ይህ ተከታታይ ትረካ የሁለት ግለሰቦችን የትግል ጉዞ በአጭሩ ለማስተዋወቅ ታስቦ የተሰናዳ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ፍልስጥኤማዊያን ናቸው። ሁለቱም ክርስቲያን ዐረቦች ነበሩ። ሁለቱም ከሀብታም ቤተሰቦች ነበር የተገኙት። ሁለቱም በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ አጥንተው በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል። ሁለቱም በዩኒቨርሲቲውማንበብ ይቀጥሉ…
የመውሊድ ትዝታዎቼ
የመውሊድ በዓልን እያከበርነው ነው። በዚህ ጽሑፌ ስለበዓሉ አከባበር የማወጋችሁ ነገር የለም። ከዚያ ይልቅ ያኔ በልጅ ወኔአችን ከሰራናቸው “አድቬንቸሮች” አንዳንዶቹን አጋራችኋለሁ። ***** በህዳር ወር 1980 ነው። በወቅቱ እኔ (አፈንዲ)፣ መሐመድ አብደላ (ማመኔ)፣ ጆሀር ሀጂ ዩሱፍ (ጀዌ)፣ አድናን ዑመሬ (አግሽ)፣ እና አሕመዶማንበብ ይቀጥሉ…
“ሌ ሚዝረብል” እና “ዣንቫልዣ”
=== እንደ መግቢያ === እነሆ የቪክቶር ሁጎ ታላቅ ስራ የሆነውን “Les Misérables”ን ልንዘክረው ነው። ይህ ድርሰት የፈረንሳይ ምድር ካበቀለቻቸው የፈጠራ ስራዎች መካከል በጣም ዝነኛው ነው። መጽሐፉ በዓለም ዙሪያ የሚታወቀው “Les Miserables” (ሌ ሚዝረብል) በተሰኘው የፈረንሳይኛው ርዕስ ነው። በበርካታ ቋንቋዎች ሲተረጎምምማንበብ ይቀጥሉ…
ጋሽ ታደሰ ኃይሌ- የአማራ ህዝብ ደግነት ምሳሌ
“ጂንኒ ጀቡቲ” የሚለውን አባባል ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁበትን ሁኔታና ጊዜ ከዚህ በፊት አውግቼአችሁ ነበር። እነሆ ዛሬም መድገሙ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የገለምሶ ከተማን የተቆጣጠረው ግንቦት 22/1983 ነበር። ኦነጎች ለሶስት ቀናት አካባቢውን ሲያረጋጉ ከቆዩ በኋላ እሁድ ግንቦት 25/1983 በፖለቲካማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል አምስት)
(እውነተኛ ታሪክ) ያ የኦነግ ወታደር አስደንግጦኝ “ወደቤት” ስገባ ትቶኝ የነበረው ፍርሃት እንደገና ተቀሰቀሰብኝ። ልቤም እንደ ቃልቻ ድቤ “ድው ድው.. ድው… ድው….” ማለት ጀመረ። “ምን ዓይነት ቀን ነው?” አልኩ ለራሴ። የአክስቴ ልጆችም እንደኔው ተሸብረዋል። “ወዴት መሄድ ይሻላል?” በማለት መነጋገር ስንጀምር “ሙበጀል”ማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል አራት)
(እውነተኛ ታሪክ) ረቡዕ ሰኔ 17/1984…. ከጧቱ 12፡30 ገደማ አክስቴ ከሁላችንም ቀድማ ነው ከእንቅልፏ የተነሳችው። እኔና ልጆቿ ከመኝታችን በመነሳት ላይ በነበርንበት ጊዜ ደግሞ እርሷ ወደ ሰፈር ሄዳ ወሬ ቃርማ መመለሷ ነው። “ምን ተፈጠረ?” አልናት። “ኢህአዴጎች ሳይጠበቁ በኦነግ ጦር ላይ ጥቃት ከፍተዋል?”ማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል ሶስት)
(እውነተኛ ታሪክ) ያ የኦነግ ወታደራዊ አዛዥ ከእግር እስከ ራሴ ከገረመመኝ በኋላ ወደ “አይካ” እና ዘኮ በመዞር “ይህ ልጅ ከናንተ ጋር ነው የመጣው?” በማለት በኦሮምኛ ጠየቃቸው። እነርሱም “አዎን!” አሉት። ከዚያም ወደኔ ዞሮ “የድርጅታችን አባል ነህ?” አለኝ። እንዳልሆንኩ ነገርኩት። “ታዲያ ለምን ወደዚህማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል ሁለት)
(እውነተኛ ታሪክ) ቀደም ባለው ጽሑፌ እንደገለጽኩት ኦነግና ኢህአዴግ ባደረጉት ስምምነት መነሻነት በኢህአዴግ ስር ያለው የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ-OPDO) በአካባቢያችን በሚኖረው ህዝብ ውስጥ ተሰማርቶ የፖለቲካ ስራ እንዲሰራ ተፈቅዶለት ነበር። በዚህም መሰረት የተወሰኑ የኦህዴድ ወታደሮች በሀብሮ አውራጃ ማረሚያ ቤት (ከርቸሌ) እንዲሰፍሩማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (እውነተኛ ታሪክ)
ዛሬ የማወጋችሁ ታሪክ ከመጽሐፍ የተገኘ አይደለም። በሬድዮ ጣቢያም አልተላለፈም። በቴሌቪዥን ፕሮግራምም አልቀረበም። በኢትኖግራፊ ጥናት (ethnographic research) ሰበብ በየከተማውና በየመንደሩ እየዞርኩ ከሰበሰብኩት ዳታ የተወሰደም አይደለም። በዐይኔ ያየሁትንና በራሴ ላይ የደረሰውን ነው እንደወረደ የማጫውታችሁ። ይህንን ታሪክ የማወጋበት በርካታ ምክንያቶች አሉኝ። በመጀመሪያ በህይወቴማንበብ ይቀጥሉ…
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናትን በጨረፍታ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ሲጠቀሱ በቅድሚያ የሚታወሱት በላስታ አውራጃ፣ በ“ሮሃ” (ላሊበላ) ከተማ አጠገብ ከአንድ-ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩት አስራ አንድ ቤተ ክርስቲያናት ናቸው። የአስራ አንዱ ቤተ ክርስቲያናት ስም እንደሚከተለው ነው። 1. ቤተ መድኃኒ-ዓለም 2. ቤተ ማርያም 3. ቤተ ደናግል 4.ማንበብ ይቀጥሉ…
እስልምና፣ ጂሐድ እና ጽንፈኝነት
ኢራቅ በሳዳም ሁሴን አገዛዝ ስር በነበረችበት ዘመን ከሞላ ጎደል ሰላምና መረጋጋት ነበራት። ሀገራዊ አንድነቷም የተጠበቀ ነው። አሜሪካ አንድም ማስረጃ ባልነበረው ወሬ ተነሳስታ በ2003 (እ.ኤ.አ) ሀገሪቷን ከወረረቻት በኋላ ግን አንድነቷም ሆነ ሰላሟ ተናግቷል። በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች ላይ የከተመችው ውቢቷ ባግዳድም በየዕለቱማንበብ ይቀጥሉ…
ኢራን፣ ሩሚ እና መስነቪ
አዎን! ዛሬ በወግ ሽርሽር ብዙ ሀገር አቋርጠን “ፋርስ” ገብተናል። የዑመር ኻያም ሀገር! የፊርደውሲ ሀገር! የኒዛሚ ሀገር! የጃሚ ሀገር! የሓፊዝ ሀገር! በሩባኢያትና በገዛላት ዓለምን እያስፈነደቁ ለብዙ ክፍለ ዘመናት የዘለቁ የቅኔ ጠቢባን የተገኙባት ምድር! ዛሬ ፐርሺያ ነን! ዛሬ ኢራን ነን። ዛሬ ቴህራንማንበብ ይቀጥሉ…
አስደሳች ጨዋታዎች
.(ከተስፋዬ ገብረአብ ) ተስፋዬ ገብረ-አብ “በጋዜጠኛው ማስታወሻ” በርካታ ፖለቲካ-ነክ ወጎችን አውግቶናል። እኔ እዚህ የምጽፍላችሁ ግን ፖለቲካውን ሳይሆን ተደጋግመው ቢነገሩ የማይሰለቹ ሌሎች ጨዋታዎቹን ነው። (እኒህን ጨዋታዎች የቀዳሁት ከዚያው መጽሐፍ ነው)። ===አቶ ፍሬው ለምለም እና የቼክ እደላው=== አቶ ፍሬው ለምለም ደግ አዛውንትማንበብ ይቀጥሉ…
የቀይ ኮከብ ዘመቻ
የኤርትራ አማጺያንን ለማጥፋት ከተደረጉ ዘመቻዎች መካከል ብዙ የተባለለት ነው- የቀይ ኮከብ ዘመቻ። ታዋቂ የጦር ጠበብት እየደጋገሙ አውስተውታል። በጋዜጣና በሬድዮ ብዙ ተለፍፎለታል። አጀማመሩም ሆነ አፈጻጸሙ ትንግርተኛ መሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ዘመቻው የተካሄደበት ለየት ያለ ድባብና በርሱ ሳቢያ የተፈጠረውማንበብ ይቀጥሉ…
የአፋቤት ጦርነት
መጋቢት 17/1988 (መጋቢት 9/ 1980) እኩለ ሌሊት። በዚያች ደረቅ ሌሊት ሕዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ (ሻዕቢያ) ሳይጠበቅ የናደውን እዝ ወረረ። የህዝባዊት ኢትዮጵያ አብዮታዊ ሰራዊትም ይዞታውን ለማስጠበቅ ተከላከለ። ይሁንና በለስ ሊቀናው አልቻለም። ሻዕቢያ ቀደም ብሎ ያገኘውን መረጃ በሚገባ ሊጠቀምበት ስለቻለ የአብዮታዊ ሰራዊትንማንበብ ይቀጥሉ…
ጥቂት ስለ “አዳል”
በመካከለኛው የታሪክ ዘመን (Medieval Era) ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን፣ ጅቡቲን፣ ሶማሊላንድን እና ሶማሊያን በሚያቅፈው የአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና የተለያየ ቅርጽና አወቃቀር የነበራቸው መንግሥታት ተመሥርተዋል። ከነዚያ መንግሥታት መካከል ከአስር የማያንሱት የሙስሊም ሱልጣኔቶች ነበሩ። ከሱልጣኔቶቹ መካከል ስሙ በጣም ገንኖ የነበረውና በአፍሪቃ ቀንድ ሕዝቦች ታሪክ፣ ጂኦ-ፖለቲካማንበብ ይቀጥሉ…
የአርሲ ዐጃኢባት
እኛ (እደግመዋለሁ “እኛ”፣ “ኑቲ”፣ “ናህኑ”) የኢትኖግራፊ ፈረሳችንን ተሳፍረን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከመሀል እስከ ሰሜን መጋለብ ሱስ የሆነብን ጸሐፊ ከሀረር መሆናችንን ታውቃላችሁ አይደል? ታዲያ እኛ (አሁንም እደግመዋለሁ “እኛ”) ወደ ሌሎቹ ስፍራዎች ስንጋልብ የነበረው ከሌሎች አካባቢዎች ሁሉ የሚቀርበንን አንድ ጎረቤታችንን እያለፍን ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…
ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጅማ (ክፍል ሁለት)
እነሆ ከተሚማ ጋር የጂማን ምድር “ሽርርርር” እያልንበት ነው። ሆኖም “ተሚማ” የትናንትናው ሙገሳ አንሶኛል ብላለች። “የነየታችሁት ሐጃ ሞልቶላችሁ በደስታ እንድትፍለቀለቁ ካሻችሁ ሙገሳውን ጨመርመር አድርጉልኝ” ትላለች። ታዲያ እኛም አላንገራገርንም። “ምን ገዶን! አንቺ ሰኚ ሞቲ! ሙገሳ በየዓይነቱ ይኸውልሽ” ብለን በድጋሚ መወድሳችንን ልንደረድርላት ተዘጋጅተናል።ማንበብ ይቀጥሉ…
መረራ ጉዲናን ሳስታውስ
በ1988 የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ESLCE) እንደወሰድኩ ነው። ዕለቱ ከሚያዚያ ወር መአልት አንዱ መሆኑ ይታወሰኛል። በዚያች ዕለት የጀርመን ድምጽ ራድዮ ከቀደሙት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለየ ዓላማን ያነገበ ድርጅት መቋቋሙን ዘገበ። የድርጅቱ መስራች የሆኑት ግለሰብ የተናገሩትንም ቀንጨብ አድርጎ አስደመጠን። በጉዳዩ ዙሪያማንበብ ይቀጥሉ…
ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጅማ!
በለምለሚቷ ምድራችን ላይ እየተሽከረከረ ዚያራ ማድረግ ወጉ የሆነው የኢትኖግራፊ ፈረሳችን ታሪካዊቷን ጅማንና ህዝቧን መጎብኘት አሰኘው። እኛም “አበጀህ! ጥሩ ሀገር መርጠሃል” በማለት መረቅነው። ፈረሳችንም የደቡብ ምዕራብ አቅጣጫን ይዞ ገሰገሰ። ከጊቤ ዉሃ ከተጎነጨ በኋላም ወደ ታሪካዊቷ ቀበሌ ሰተት ብሎ ገባ። ጅማ! የአባጅፋርማንበብ ይቀጥሉ…
ወለጋ እና ሌንሳ ጉዲና
ከዚህ በፊት ስለወለጋ የሚያትት አነስተኛ ጽሑፍ በዚህ ግድግዳ ላይ ለጥፌ ነበር። ይሁንና ያቺ ጽሑፍ ለወለጋ ክብር የምትመጥን አልመሰለኝም። ብዙ ድርሳናትን ለሚያስጽፈው ምድር ትንሹን ብቻ እንደ መወርወር ነው። በመሆኑም በዛሬው የኢትኖግራፊ ጉዞአችን ወለጋን ደግመን ልንዘይረው ተዘጋጅተናል። ጉዞ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ! ዳይ!ማንበብ ይቀጥሉ…