የእናኑ መልዕክት ለሽሮ ሜዳ ዜጎች

. . . ሁሉን ነገር ካስተዋሉት ያስገርማል። የኑሮ ትንሽ የለውም። እዛ የወደቀችው ሳር አስገራሚ ናት። ወፍ ለቅሞ ጎጆ ይሰራባታል። ይሄን ሳር አጭዶ ያመጣው ማጭዱ አስገራሚ ነው። ሰዎቹ ማጭድ ማሰባቸው?! .. ሳሩን አጭዶ ያመጣልኝ ሰውዬ ዘገየ ይባላል። ጨዋታ ያውቃል። እሱ ሲያወራኝማንበብ ይቀጥሉ…

…ገነት

” እየተስለመለምኩ ፊትዋን በሁለት እጆቼ ያዝኩ . . አሟልጮኝ እንደሚወድቅ ሁሉ. . . እንደሚፈስ ሁሉ . . . ፊቴ ገነት ፊት ላይ ወደቀ… አፌ ዉስጥ ከንፈሮቿን እንደ ቢራቢሮ ክንፎች ይዤአቸዋለሁ በገላዬ ዉስጥ አየር እንደሚያልፍ ሁሉ ነበር . . . እንኰይማንበብ ይቀጥሉ…

ምንቸት አብሽ

አንድ ፋሲካ እነ ወሰን የለሽ ቤት ተልኬ መልዕክቴን ካደረስኩ በሁዋላ እንድቀመጥ ተነገረኝና ከዋናው በር ጎን ያጋጠመኝን የጉሬዛ አጎዛ የለበሰ የሳጠራ ወንበር ላይ ኮሰስ ብዬ ቁጭ አልኩ። (መንኩዋሰሴ ለራሴ ይታወቀኛል) ብዙም ሳይቆይ እንዲህ ሆነ ……………… ነጭ የላስቲክ ሳህን ፊት ለፊቴ ተቀምጧል…ማንበብ ይቀጥሉ…

ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ግንባታ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ሥነ ፅሁፍ’ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ፤ የጸጋዬ ገብረመድህንና የአዳም ረታን ስራዎች ዋቢ በማድረግ ስለ ብሔርተኝነትና ሀገር ግንባታ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። የጥናታዊ ፅሑፉ ጨመቅ (Summary) ለንባብ እንዲመች ተደርጎ እንደሚከተለው ቀርቧል።ማንበብ ይቀጥሉ…

“መንገድ ተዳዳሪ ነኝ

“መንገድ ተዳዳሪ ነኝ። ‘መተዳደር’ ከባድ ቃል ነው። ‘መተዳደር’ የሚለው ቃል በሐምሌ ብርድ ወፍራም ጋቢ ተከናንቦ አጃ መጠጣት ይመስላል። ግን እንዴት ነው መንገድ ላይ እየኖሩ መተዳደር? . . . ላውንቸር ተሸክሜ በኩራት የተራመድኩበት ጎዳና ላይ፤ ሀገር እንደሌለው ሰው አፈር ‘እፍ’ ብዬማንበብ ይቀጥሉ…

ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ (ዳሰሳ)

“የኢትዮጵያ ምድር አንቺ የደም ጎዳና መስክሪ አፍ አውጪና” (ምኒልክ ወስናቸው) “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ”፤ አዳም ረታ በአብዮቱ ዘመን የነበሩ የአንድ ሰፈር ልጆችን ሕይወትና ዕጣ ፈንታ የሚያሳይበት ትረካ ነው። አዳም፤ የእነዚህን ልጆች እድገትና ጉርምስና፣ የፖለቲካ ንቃትና አሳዛኝ ፍፃሜ በሰባት መንገዶች ወግማንበብ ይቀጥሉ…

‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ

‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ። ተረቱን ያመጣሁት፤ ደንባራ የሆነ የባዕድ ባህል ቅጂ ምን ቦታ እንደሚከተን ሳስብ እያለሁ፤ ‘ሙሾ አውራጆች የኋላ ቀር ባህል እሴቶች እንደሆኑ’ ሊነግረን የሚጥር፣ በምርምር ያልተደገፈ፣ ጥልቅ በሆነ ፍልስፍና ሞትን፣ ሃዘንና ኪነትን እንድንረዳ ለደቂቃ እንኳን ያልጣረ፣ ለስሙ ‘ለኪነ ጥበብማንበብ ይቀጥሉ…

‘The past is a foreign country’ (ያለፈው ዘመን ባዕድ አገር ነው)

ይሄን የእንግሊዝኛ ተረት በዚህ ዓመት ውስጥ ሺህ ጊዜ ሳልሰማው አልቀርም። ግን መደጋገሙ ሲበዛብኝ፤ አባባሉ እንዲወደድ ስልት ያለው የማለማመጃ ዘመቻ ወጣቱ ላይ እየተሰራ መሰለኝ። ዘይቤውን የሚናገሩት ብዙ የጥቁር ሀበሻ (ሀበ) ፈረንጃዊያን ብቅ ብለዋል። እነሱም ʻየአገራችንን መልካም ታሪክ እንጥቀስʼ ስንል ዐይኖቻቸው ቀልተውማንበብ ይቀጥሉ…

በርበሬ

“አንድ ወዳጄ . . . በርበሬ ኢትዮጵያዊ ቅመም እንዳልሆነና ሲጀመር በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ ወረራ ጊዜ ፖርቹጋሎች ወደዚህ ሀገር እንዳመጡት ተናገረ . . . ነገሩ እየከበደ ውይይቱ አስደሳች ገፅ አበጀ። ጓደኛዬን ‘በርበሬ ከፖርቹጋል እንደመጣ፤ ምን ማስረጃ አለህ?’ አልኩት። እሱምማንበብ ይቀጥሉ…

“ማሕሌት” አጭር ልብ ወለድ ላይ የተሰጡ ሃሳቦች

፩ “… ማሕሌት ሕይወትን ከልጅነቷ ጀምራ እንደ ፈቀደችው ያልኖረች፣ ዕጣ ፈንታዋ በጉልበተኛ ወንዶች ጫማ ሥር ያዋላት ልብ ሰባሪ ገፀ – ባሕሪ ናት። በልጅነቷ ተገዳ የተዳረች፣ ከገጠር ሸሽታ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ በአጎቷ ጓደኛ የምትደፈር፣ ይህን ለማምለጥ ሥራ ብትቀጠር እንደ ቀደሙትማንበብ ይቀጥሉ…

ትንንሽ ቅመሞች

ቅዳሜ ቅዳሜ ማታ በዙረቴ የማልደርስበት የከተማችን ክፍል የለም። ሳምንት ወይ አስራ አምስት ቀን በሙሉ ከቤት ሳልወጣ እቆይና፣ እመሽግና አንድ ቅዳሜ መርጬ ከወጣሁ ግን የምመለሰው ተበለሻሽቼ ነው። በደንቤ ሳምንት፣ ሁለት ሳምንት ሙሉ ከቤት አልወጣም…… ከእሁድ እስከ ዓርብ። ብዙ ጊዜ ቅዳሜ ግንማንበብ ይቀጥሉ…

‘እኛ’

በዛሬ ብልጣብልጥ ዘመን ከሌሎች ተውላጠ ስሞች ያልሆነ የወል ፍቺ ተቀብቶ በየቦታው ብቅ የሚል የሰዋሰው ክፍል ነው። ‘እኛ’ የተባለው ማነው? ‘እኛ’ በእኔ ግምት ሁለት ዝርያዎች አሉት። የመጀመርያው ዝርያ አዲሱ ራሳችን የፈጠርነው ‘እኛ’ ነው። ጥቂቶች ያበላሹ፣ አበላሺ (ብልጥ የሆኑት)፤ የአበላሺ ተከታይ (ነፋፋማንበብ ይቀጥሉ…

ሥግር ልብ ወለድ፤ ሕፅናዊነት (ክፍል 4)

ሕፅናዊነትን በዚህ ዘመን አስፈላጊ ያደረጉት የአገሪቷ ሁኔታዎች መብዛት፣ መስፋት፣ የተለያዩ ብቻ ሳይሆን መያያዛቸውም ነው። ጥቂቶቹን ወይም ክሱቶቹን ልጥቀስ 1. ከስድሳ ስድስት ዓመተምህረት በፊት የዜጎች ስደት ትልቅ ጉዳይ አልነበረም። 2. ሽብር ትልቅ ጉዳይ አልነበረም። 3. በፖለቲካ ምክኒያት መሞት ትልቅ ጉዳይ አልነበረም።ማንበብ ይቀጥሉ…

ሥግር ልብ ወለድ፤ ሕፅናዊነት (ክፍል 3)

 ‘እንካነት’ አፍ ለንባብ ወደ አደባባይ ከመምጣቱ በፊት፤ ደራሲው ለአምስት ወንድም ደራሲዎች የመፅሀፉን የተተየበ ኮፒ በመስጠት ሥግር እንዲሰሩበት ጋብዞ ነበር። የደረሱኝን እነዚህን ሥግሮች በአፍ ሁለተኛ ዕትም ላይ እንደማቀርብ ተስፋ አደርጋለሁ። ‘እንካ’ ብዬ የምጠራውም ይህን ደራሲያኑን የመጋበዝ ድርጊት ነው። አፍ የተባለውን ይሄንማንበብ ይቀጥሉ…

ሥግር ልብ ወለድ፤ ሕፅናዊነት (ክፍል 2)

“ነው” ተብሎ ቢደነገግም ባይደነገግም ማንኛውም ልብ ወለድ ሥግር ነው። ማለት የራሱን ጉጥ/ዐይን መርጦ የራሱን ሥግር ይሰራል። የየራሱን አቋምና ልዩነት ይደነግጋል። ልዩነት ሲባል ሂደት ማለት ነው። ስለዚህ አፍ ሥግር ነው ብዬ በንዑስ ርዕስ መጥቀሴ ስለ ነጠላ ዕቅዴ ይናገራል እንጂ ስር ነቀልማንበብ ይቀጥሉ…

ስግር ልብወለድ፣ ሕጽናዊነት (ክፍል 1)

‘I see the world in a grain of sand And a heaven in a wild flower…. ‘ (1803) እንግሊዛዊው ገጣሚ ዊሊያም ብሌክ የሰፈራችን ልጅ ቴንሳ እንዲህ የሚል ግጥም አለው፤ ‘አለምን በደቃቃ ጤፍ አያታለሁ አገሬንም በቁራሽ እንጀራ’ የዋህነት እንዴት ያደክማል? ከተባለውማንበብ ይቀጥሉ…

ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ግንባታ

“ለአዳም፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በጊዜ ውስጥ አይደለም የተፈጠሩት። ከጊዜ ጋር አብረው ነው የተፈጠሩት” የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ስነ ጽሁፍ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ የጸጋዬ ገብረመድህንና የአዳም ረታን ስራዎች ዋቢ በማድረግ ስለ ብሔርተኝነትና ሀገር ግንባታማንበብ ይቀጥሉ…

እንጀራ

የተሟላ አይነት ውክልና አለው። ይታያል (እንደ ስዕል)፣  ይነካል፣ ይቀመሳል፣ እናም ይበላል፡፡ የመጨረሻው ፀባዩ የተለየ ያደርገዋል። እንደ ብዙ ቁሳቁስ በሩቅ የሚታይ አይደለም። ከሳብጀክቱ (የሰው ልጅ) ጋር ይዋሃዳል (embodied)። የትውስታም ሰሌዳ ነው። አርኪዮሎጂስቶች በጥንት ጊዜ የተሰራ ቁስ አግኝተው በመሳሪያቸው መርምረው የእነዚህን ቁሶችማንበብ ይቀጥሉ…

ጉርሻ

‘ጉርሻ የሚያቀራርብ ነው። በጉርሻ አይኖቻችን የፈጠሩት ርቀት ይጠፋል። በኋላ እንዳየሁት መጎራረስ ወደ ወሲብ የሚጠጋ ኢትዮጵያዊ ድርጊት ነው። በማዕድ ዙርያ እንዲቀመጥ የተገደደው ተከፋፍሎ ግለሰብ የሆነው ቡድንና ማሕበረሰብ በሚዘረጋው የበላተኛ እጅ ድልድይነት ይቀራረባል። ‘አብረን በልተን’ ሲባል ውስጡ ከባድ የጉርሻ ይዘት አለ። ጉርሻማንበብ ይቀጥሉ…

ቀጠሮና እሷ

ዜጎቻችን ቀጠሮ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ቢደመር ለፍርድ ቀን፡ በዓለም የመጠናቀቂያ ዕለት የተከመረ ሐጢያት ሆኖ መንግስተ ሠማያት የሚባል ቦታ አንድ ሀበሻ አይገባም ነበር። መልካም ቀጠሮ አክባሪዎች በእግዜር ቀኝ ሲሰለፉ፤ 80ሚሊዮን የሚደርሰው ሀበሻ በጠቅላላ በእግዜር ግራ። ግራ ይግባንና። የማይገባኝ ግን ምክንያቱ ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…

እትት በረደኝ

“ጅላዋት ሆይ፣ ጮማ ክፋት ከመጣ ሰላሳ እግዜር፣ ሰላሳ አላህ አይመልሰውም።” “….በዲሞክራሲ ስለማምን አይደለም። ምንድን ነው እሱ? ልግመኛ ቢሰበሰብ የአንዲት ጮጮ ክዳን አይከፍትም። ፍትህ ፍትህ ፍትህ የምትባለዋም የነብር ቂንጥር ናት። በሥዕል ይህቺ ፍትህ የሚሏት ሴትዮ ቆማ አይቼአታለሁ፤ ሚዛንና ሰይፍ ይዛ። ሰይፉማንበብ ይቀጥሉ…

‘ጉልባን’

“… ድል አውሪ በኦፊሻል ሙያው ‘ዳቦ ጋጋሪ’ ይባል አንጂ በድብቅ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ ትዝታ አንደርግራውንድ (ትን) የተባለ ድርጅት አባልና አነቃናቂ ነው። የዚህ ድርጅት ስራው ከጥንት ጀምሮ በሀገሪቷ የነበሩ የኪነት ስራዎችን በፓይሬት ሬድዮ ለከተማው ህዝብ ማሰማት ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…

“የፖለቲካ ትልቁ ጥቅም ሽፋን መስጠቱ ነው”

ታውቃላችሁ ፖለቲከኞቻችን ትልልቅ ነገር እየተናገሩ ይማርኩናል። ጋዜጣ፣ ሬዲዮና ቲቪ አስደግፈው ያማልሉናል። አንድ ዛፍ ይተክሉና ስለዚህ ስለተከሉት ዛፍ አስር ሰአት ያወራሉ። ይሄን የሚሰሙ የዋሃን እና ቂሎች፣ ዛፍ ብቻ ሳይሆን በቃ ደን ያደገ ይመስላቸዋል። ድርጊቱ ደቃቃ ቢሆንም ከጥዝጠዛው ብዛት የእውነት ትልቅ ይመስላቸዋል።ማንበብ ይቀጥሉ…

ቀለማቱን በተመለከተ . . .

‹‹የስንብት ቀለማት ውስጥ ያሉትን ቀለማት በተመለከተ ጥያቄ ቢቀርብም ቀደም ሲል ራሴም እንደማሳሰቢያ ለማስቀመጥ በልቦናዬ የሻትኩት ነጥብ ነው። በጥልቅ ሂስ ስራ ወይም እዛም ባይደርስ በተራ ግምገማ ድርሰቱ ውስጥ የተጠቀሱት ቀለማት ምን ማለት ናቸው? ምን ይወክላሉ? ብሎ ጥያቄ ማንሳት ትክክል ነው። በአጭሩማንበብ ይቀጥሉ…

ከአዳም ረታ ቃለ መጠይቅ

በድርሰቶችህ ውስጥ መልክዓ ምድራዊ ገለጻን የገጸባሕሪያት ልቦናዊ መልክ ማሳያ አድርገህ ስትጠቀም ይስተዋላል። የዚህ ምክኒያቱ የገለጻ ፍቅር ነው ወይንስ ከዚህ በፊት ያጠናኸው የጂኦግራፊ ትምህርት ተጽእኖ ነው? ጂኦግራፊ መልክዓ ምድር ብቻ አይደለም። መዓት አይነት ጂኦግራፊ አለ፤ ስለዚህ እሱ አይመስለኝም። ጂኦግራፊ ስትማር ስለማንበብ ይቀጥሉ…

አድባርና…

በዚህ በኩል የእኛ ቤት አለ አይደል…… እንዲህ ከተሰለፉቱ አንዱ። በዚያ በኩል ደሞ ሌሎች ቤቶች ነበሩ… በነገረ-ሥራቸው ከእኛው የማይለዩ። ግራና ቀኛችን ለመቶ ሜትሮች ያህል ቤቶች። ቤቶቹ በሙሉ ትናንንሾች ሲሆኑ የምኖረው ሕዝብ ብዛት ግን የጉድ ነበር (ዛሬም እንደዛው ነው)። በዐይን ብቻ የማውቃቸውማንበብ ይቀጥሉ…

እሷ…

. . . እየተስለመለምኩ ፊትዋን በእጆቼ ያዝኩ። አሟልጮኝ እንደሚወድቅ ሁሉ። እንደሚፈስ ሁሉ። ፊቴ ገነት ላይ ወደቀ – አፌ ውስጥ ከንፈሮቿን እንደቢራቢሮ ክንፎች (እንዲህ የሚቀስሙት አበባ ላይ አርፈው ምናልባትም በወለላ ሰክረው ልባቸውን ነስቷቸው እያሉ ክንፎቻቸውንም እንደመፅሐፍ ገጾች ገጥመው – በቀስታ ከበስተሁዋላቸውማንበብ ይቀጥሉ…

ዳዊት

ዳዊት የታወቀ ታስሮ የተፈታ ሪቮ ነው። (በተማሪ ‘ትግል’ ታስሮ መፈታት ራሱ ‘ችሎታ’ ነው፤ በምን ሂሳብ እንደሆነ ባይታወቅም።) ዝናው በኋላ ከመጡት ከነመኮንን ይበልጣል፣ ከነጥላሁን፣ ከነዋለልኝ ይስተካከላል። የተናገረው ነገር ብዙው መሬት ቢወድቅም፤ በትክክል ማን ዝነኛ እንዳደረገው እንዴት ዝነኛ እንደሆነ ባይታወቅም…… የዝነኝነት ስሙንማንበብ ይቀጥሉ…

ዕውቀት ይቅደም

” . . . ዕውቀት ይቅደም ነው ያልኩት። ያውም ሰፊ ዕውቀት። ከአትኩሮት ጠባብነት እንውጣ ማለቴ ነው። ከደቃቃዊነት (Minimalism) ወይም አሹራዊነት (ከአስሩ አንዱን ብቻ ማየት) መሸሽ ነው። በሌሎች ሃገሮች እዚህ ‘ቀይ ሌሊት’ ዐይነት ስራ ከመድረሳቸው በፊት ታላላቅ ስራዎች ተደጋግመው ተሰርተዋል። ድልድዩማንበብ ይቀጥሉ…

(ሕልም)

የሕልም ዓይነት አለ፡ እየጮሁ መጮህ የማይችሉበት፣ እየሮጡ መሮጥ የማይችሉበት፣ እያለቀሱ ዕንባ የማያወጡበት። ሕልምም አለ፡ የማያልቅ የማያልቅ መንገድ የሚጓዙበት…… ሕልምስ አለ የዘለቃ ባነው እንኳ የሚወቃ (ዘለቃ አስቀያሚ በመሆኗ) ሕልምስ አለ የነ አልማዝ ከወር እወር የሚያፈዝ (ደደብ ስለሆኑ አልማዞች) ሕልምስ አለ የመዘዞማንበብ ይቀጥሉ…

…ምስክሬ ነው

ወላጅ አባቴ በእናቴ አሳቦም ይሁን አስመርራው ሸሽቶኝ ቢሄድም ይሄ ዓላዛር የተባለ የሽሮሜዳ ሸንኮራ እግሮቼን ተከትሎ ወደምሄድበት ሄደ፥ አረፍኩበት አረፈ፥ ሳቄን ሳቀ። አባቴ ወደ ቆላ ቢኮበልልም ዓላዛር እጄን ያዘኝ። ዘመናይ ለዘመናይ። እዚህች ደጋና ወይና ደጋ ሰላሜን አገኘኋት፥ አዚዬ በቁጭት የተጨበጠች ግራማንበብ ይቀጥሉ…

ጩጬ ብንሆንም ይገባናል

ምሽቱ ለዓይን ሲይዝ ቤታችን ፊት ለፊት በሩን ራቅ ብዬ እያየሁ ወዲያ ወዲህ እላለሁ፡፡ የሰፈሩ ልጆች ሁሉ በየቤታቸው ገብተው እኔ በዛ ቀዝቃዛ ምሽት አስፋልት ዳር ቀጠሮ እንዳለው ሰው ወዲያ ወዲህ እላለሁ፡፡ ቤቴ አልገባም፡፡ ታዲያ ወላጆቼ እኔን መጠበቅ ይሰላቹና..…. እናቴ ኩታዋን ተከናንባማንበብ ይቀጥሉ…

የመዲባ ኡሪ

ከዕለታት አንድ ቀን ‘ጣይቱ’ የተባሉ እተጌ እዛች ፍልውሃ የምትባለው የምትጤስ ቦታ፣ እዛች እርጥብ ፊንፊኔ ገላቸውን ተጣጥበው ጨርሰው፣ ከተቀመጡበት በርጩማ ብድግ ሲሉ፣ እንደ ደንግ የምታበራ የሕልም እንቁላላቸው የምትሞቅ ግልገል ኩሬ ውስጥ ወደቀች፡፡ ከዛም ወደ ተሰራላቸው ማረፊያ ጎጆ አቀበቱን ሲያዘግሙ፣ ስሟ የተጠራማንበብ ይቀጥሉ…

ለፅጌሬዳ ሐብታሙ

‹‹እንደ አንቺ አንድ ቦታ የበቀልኩ ባሕር ዛፍ ሳልሆን እንደ ኮባ ውላጅ የተሸከረከርኩ ነኝ፡፡›› 03/07/79 ለፅጌሬዳ ሐብታሙ ፓ.ሣ.ቁ 0000 አዲስ አበባ ለጤናሽ እንደምን ከርመሻል? ሦስት ሳምንቶች ያህል ከጠፋሁብሽ በኋላ በዐይነ ስጋ ሳይሆን—እንዲህ በወረቀት፣ በቀለም፣ በሆሄያት፣ በፓስታ ላናግርሽ መሆኔ ግራ ሳይሆንብሽ አይቀርም፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…

ጉድጓዱና ውሃው

አንዳንዴ እያካፋ…… አዲስአባ ቀላል ደመና ተከናንባ…… እንደ ነጠላ…… ሲያካፋ፣ ፀሐይም…… ፀሐይ ከራ ወበቅና የቀዝቃዛ አየር እጥረት እግሮቼን አሳስሮአቸው ያጋጠመኝ ቦታ ተቀምጬ አገጬን እጆቼ ላይ አስደግፌ ሳስብ፣ ሕሊናዬ በእጅና በእግሩ እየዳኸ፣ እየወደቀ፣ እየተነሳ ወደ ንፋስ መውጪያ ይነዳኛል፡፡ ብጠላውም፣ ተዘርቼ የበቀልኩበትን ብጠላውምማንበብ ይቀጥሉ…

ፀጥታ ነጋሲ

ይኼ አብኛዛውን የምንኖርበት አለም ፀጥታ ነው፡፡ ያልተነገረለት ነው፡፡ ሆሄ፣ ቃል፣ አንቀፅ፣ ምዕራፎች፣ ቅዳሴና ዘፈን፣ እንጉርጉሮና ምንትስ አልተነዳበትም የሚባል፡፡ ምድር ላይ ከተሰሩና ከተደረጉ ከታሰቡና ከታለሙ ነገሮች የተመዘገበው ስንቱ ነው? የአዳም የመጀመሪያ ሳቁ ተመዝግቧል? የመጀመሪያው የአዳም ወይ የሄዋን እንጉርጉሮ ይታወሳል? የሐጢያት መጀመሪያማንበብ ይቀጥሉ…

ኩልና ተኮላ

ተኮላ የተባለ ሰው አፍቅሬ በትዳር መኖር ከጀመርኩ አሁን ሰማንያ ሰባት ነው አይደል? አዎ አንድ አመት ተኩል አለፈኝ፡፡ በዚህ …. ማለት በቃ ከእሱ ጋር አንድ ቤት ውስጥ ሚስቱ ሆኜ በመኖሬ ደስተኛ ነኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በማያገባቸው መግባት የሚወዱ ወይም የማናቀፍ ጉጉታቸው ወሰንማንበብ ይቀጥሉ…

ቡቡ ዘተበሃለ ስንዝሮ (ከ “የስንብት ቀለማት” የተወሰደ)

ተረት ተራች ነኝ፡፡ ድሮ ድሮ እንደ እኔ አይነቱ ተራች፣ ጉዳይ ቀማሚ ፣ የታሪክ ጉድፍ ነቃሽ ‹ሐዳሚ› ይባል ነበር፡፡ በጥንት አፍ እንግዲህ ሐዳሚ ነኝ፡፡ ህይወት ተወሳስባ፣ ተተረማምሳና ተሸፋፍና ልታልፍ ስትል ለአፍታ ጆሮዎ ስር አቆማትና በአንደበቴ (በልሳነ ጥንት፣ በልሳነ ድንጋይ ዘመን ቀባጢሶ)ማንበብ ይቀጥሉ…

…ቸል ያደርገኛል

‹‹ከጠዋት እስከማታ እለፋለሁ፡፡ የምለፋውም በቸልታ፡፡ ነገሥታቶቹ ምቹ ላይ ይተኛሉ፡፡ የሚንቀጠቀጥ ማለፊያ እንጀራ ሰሀኖቻቸው ላይ ዘርግተው የእኔ የደንባራው ነገር ገርሟቸው በሳቅ ይፈርሳሉ፡፡ በንቀት የመጣ አለመግባባት እንጂ ሌላ ምንድን ነው? ይሄ ቸል ያደርገኝ ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ በቆዳ ቦት የታሰሩትን እግሮቼን ማታ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ከአዳም ረታ ቃለ መጠይቅ

. . . አብዮት ሲመጣ (እንዲመጣ ሲደረግ) ልብ ወለድ መጽሃፍት ቢረባም ባይረባም በፓምፍሌት ተተኩ፡፡ ለመጀመሪያ ሰሞን ደስ የሚል ነገር ነበረው፡፡ ምክኒያቱም አዲስ ነው፡፡ (እዚህ ዘመን ላይ ቦታ ስለማይበቃን ልዝለለው እንጂ በሰፊው የምለው ኑዛዜያዊ ግለ ሂስ ነበር) ብዙ ሳልቆይ ሲጀመር መሰላቸቴንማንበብ ይቀጥሉ…

ወጣቶች ፖለቲካ ውስጥ …

“ወጣቶች ፖለቲካ ውስጥ ተንጋግተው የገቡበት ሁኔታ ባብዛኛው በእኔና በሳል በሆኑ ሰዎች ግምት (ወይም በገባቸው ሰዎች ግምት) በአገራችን የሰፈነው ጭቆና አስከፊ ሆኖ መላወሻና መንቀሳቀሻ ጠፍቶአቸው ሳይሆን በረቀቀ ፕሮፓጋንዳ ግፊት መሆኑ ነው። ፕሮፓጋንዳ አዲስ ፍጡር አይደለም፡ ድሮም ነበረ። ዛሬ የፈረሰውን የሰለሞናውያን ስርወማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...