Tidarfelagi.com

እኔን የሆነው ማነው?

አመድ አፋሽ መሆኔን ነግሬያችኃለሁ?🤣 የምሬን ነው ያበደርኩት ሰው ‘ብሩን ከምፈልገው ሰዓት ሶስት ደቂቃ ዘግየብኝ’ ብሎ የሚቆጣኝ ሰው ነኝ 🤣
ሰርጉን: ውልደቱን… ደስታውን ሁሉ ከሌሎች ወዳጆቹጋ ሲፈነጥዝ ያላስታወሰኝ ወዳጅ ‘ለሀዘኔ ያነባሽው እንባ ሀያ ስድስት የእንባ ዘለላ ከግማሽ ነው.. በደንብ አላላቀስሽኝም’ ብሎ የሚያኮርፈኝ ሰው ነኝ።

ቦይፍሬንዷ ልቧን ሰብሮት ቁጭ ብዬ ሳስተዛዝን አድሬ ‘በጠዋት ትተሺኝ ሄድሽ’ ተብዬ የምኮርፍ ሰው ነኝ …
‘እንዲህ ገብቶ … ይሄ ሆኖ … ይሄን ያህል ብር ላኪ’ ያለኝ ሰው … ብሩ እስኪደርስ አንድሺህ ሶስት ጊዜ ደውሎ ብሩ ሲደርስ ‘ወስጃለሁ’ ለማለት ብሩ እስኪያልቅ የሚረሳኝ ሴትዮ ነኝ ….

እቤት ውስጥ የሆነ ሰው ‘እንዲህ ቢደረግ’ ብሎ ሀሳብ ሲያመጣ በአናቴ ተተክዬ ነገርየውን አሳካዋለሁ አይደል? በመጨረሻ ‘እሱ ፓ ፈጣሪ የባረከው… የተመረቀ’ የሚባለው ቢደረግ ያለው ሰው እንጂ እኔን ማን ሰው ብሎኝ 🤣🤣

ምን አለፋችሁ አብዛኛውን ጊዜ ….. ከመምጣቴ ይልቅ መዘግየቴ ይቆጠርብኛል…. ካደረግኩት 10 ነገር ያላደረግኩት አንድ ነገር አስር ዓመት ይወራልኛል። … እድሜዬን ሙሉ ከሰጠሁት ፍቅር አንድ ቀን ያስቀየምኩት ደምቆ ይፃፍልኛል …
እኔን ነህ ወይ? ነሽ ወይ ? ተከተሉኝ
የምሬን ምስጋና የምሻ ሰው ሆኜ አይደለም🤣🤣 ሆ …. ‘ብርጉድሽ ቀርቶብኝ ፈስሽን በያዝሽልኝ’ አለ የሀገሬ ሰው ….
እና አንዳንዴ ‘ሜዬ ለምን ዝም ብለሽ አትኖሪም? ማን የሚሏት ሴትዮ ነሽ? ዝም ብለሽ ለምን የራስሽን ኑሮ አትኖሪም?’ እላለሁኮ 😜
በቀደም የሆነ ሰው ደስ ላሰኝ ብዬ ተፍ ተፍ ስል ቆይቼ ስደርስ አርፍጄ ነበርና ‘ክፉ ሴት ነሽ.. ዘገየሽ’ የሚል ምስጋና ጠበቀኝ… በጣም ምርር ስል ያየ ወዳጄ
‘አንቺ ግን አትለምጂም እንዴ?🤣’ብሎ አስቆኛል

ዋናውን ነጥብ ያዙልኝማ ….
በህይወቴ ውስጥ አስቀያሚ ውድቀት ስወድቅ እጃቸውን የዘረጉልኝ ሰዎች …. ወይ የማላውቃቸው … ወይም በነሱ ህይወት ውስጥ ምናምኒት ጥሩነት ያላበረከትኩላቸው ሰዎች ናቸው። ምናልባትም ወላ ቦታ ያልሰጠኃቸው ሰዎች ናቸው። …… (ፈጣሪ መማረሬን ሲያሳፍረኝ አያቹልኝ?)

አሁን ላይ…..
እንደ ህይወት መመሪያ ምን አምናለሁ መሰላችሁ? መልካም ስሆን ምላሹን ከጠበቅኩ … የሚከፈል ውለታ እንጂ ያስቅመጥኩት መልካምነት አላሳየሁም ….. እናም አመድ አፋሽ መሆኔን እያወቅኩም 🤣🤣 በተቻለኝ መጠን ሁሉ በሰዎች ፊት ላይ ለሚታይ ፈገግታ እንጂ ለእንባቸው ምክንያት ላለማበርከት እጥራለሁ። …. እግዜሩ ደግሞ እኔ ፊት ላይ ለሚታይ ፈገግታ ቦዝኖ አያውቅም።

እግዚአብሄርም ህይወቴን በብዙ ቅን ሰዎች እየሞላው …. ያስገርመኛል። ….. እናም ደስተኛ ነኝኮ ….

ውብ ውቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝማ❤️❤️❤️❤️

One Comment

  • eyuel commented on June 6, 2021 Reply

    ጥሩ መክርሻል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...