ሰናይት እባላለሁይ ትውልዴ እዚሁ ሸዋ አንድ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። እትዬ ቤት በቤት ሰራተይነት ከተቀጠርኩ 5 አመት አልፎያል ነገር ግን አንድም ቀን ቤተሰቦቼየን እንድጠይቅም ከግቢ እንድወጣም ተፈቅዶልይ አያውቅም።
የመጀመሪያ ቀን አንድ ደላላ ወደ እትዬ ቤት ሲያመጣይ ወደ ውጪም ወደ ሹፌሩም በማያሳይ ድፍንፍን ያለ መሂና ነበርና ከሰው ጋር አብሬ መኖሬን እይ የት እንዳለሁ አላውቅም ነበር ያለሁት አዲስ አበባ መሆኑን የነገረይ እይሁ ቤት ውስጥ በዘበይነት ተቀጥሮ የሚሰራው በልሁ ነበር።
ሆኖም የትዬ ቤት ምቾትና የተንደላቀቀ ኑሮ ሌላውን አለም ያስረሳልይ።እንኳን አምስት አመት አምስት ወር የሆነይ ያክል ተሰምቶይ አያውቅም።
ተቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የትዬ ቤት የአንድ ቀን ሂወት እንደ አመት የረዘመ ሆኗልይ።
እትዬ ሁለት ልዦች ቢኖራቸውም ቅሉ ሀገር ውስጥ አይኖሩም ባለቤታቸው የደለበ ስልጣን የነበራቸው ቲሆን ምህንያቱ ባይገባይም ከ ወራት በፉት እቤት መዋል ዥመሩ።ለእረፍት ነው እንዳይባል አርፈው አያውቁም በፊት ያልነበረባቸውን ባህሪይ ሲጋራውን በላይ በላይ እየማጉ ግቢ ውስጥ ወዲህ ወዲያ እየተንቆራጠጡ ስልክ ቲደውሉና ቲያወሩ ነው የሚውሉት አቤት የስልክ መአት!ቲላቸው ደግሞ ቀንም ማታም እቤቱ ማማ ላይ ያለው መናፈሻ ላይ ይወጡና እሚጠብቁት ሰው ያለ ይመስል አንገታቸውን ወዲህ ወድያ እያመላለሱ ሰፈር መንደሩን ሲቃኙ ይውላሉ ለምሳም አይገቡ።
እትዬም ፀባያቸው ተለዋውጧልይ፣ ያ ሳቂታ ፊታቸው ጠቁሯል።በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አንድ ቀን በጥዋት ፓሊሶይ ድንገት ግቢውን ወረሩት ወድያው ምንም ሳያወሩ ጋሼን እያንከወከው ወሰዷቸው ያኔ የትዬ ጭንቅት ወደ እብደቱ ታይጠጋ አልቀረም።
እንቅልፍ እሚባል ነገር ከኧእምሮቸው ተነ ጭራሹጨ ጠፋ ቀን እና ሌት መቆሚያ መቀመጫ አሳጡይ ተሳቸው ጭንቀት እና ፍርሀት ጋር አብሬ መጨነቅና መፍራት ሰለቸይ ያንን ቤት መልቀቅ ፈለኩይ ታድያ ቤቱን ለመልቀቅ ማሰቤን ለእትዬ ተመናገሬ በፊት ለዘበኛው ለበልሁ ላማኽረው አሰብሁና አንድ ቀን ወደ ማደሪያው ጠጋ ብዬ የመልቀቅ ሀሳቤን አውጋሁት።
በድንጋጤ ጋደም ታለበት በርግጎ ተነሳ።ምነው ምን አስደነገጠህ? ትለው…
“ይቅርብሽ የኔ እህት እኔ ልምከርሽ ይቅርብሽ እኔ ተወጣትነቴ ዥምሮ ለብዙ አመት እይህ ቤት በዘበኝነት አገልግያለሁ ።ግን የይህ ቤት ሰራተኞች ቲገቡ እንዢ ቲወጡ ተመልኽቼ አላውቅም ” ምን ማለትህ ነው ?በቃ እሄው ነው ትለዚህ ቤት ሚስጥር ታወቁ ቡሀላ መፈናፈን እህህህም! አለ በልሁ ። ምናልህ? እልሁት። “አበቃሁ!” አለ።
ስንት ሰራተኛ ገብቷልይ? እስታሁን?ትለው
” ኧረ ተዤም ጣቶች የላቁ ናቸው አለኝ ደነገጥሁ
ታድያ ቲወጡ ታላየህ የት ገቡ?
“እንዣ እሱ የኔም የእድሜ ይፍታ ጥያቄ ነው ብቻ ይቅርብሽ እሄውልሽ አንዳንዶቹ እንዲህ እንደ አንቺ መውጣት እንደፈለጉ መጥተው ያማኽሩኛል ከቀናት ቡሀላ ወጡ ቲባል እንዢ ቲወጡ አይቼ አላውቅም እሄው እንደምታይኝ ቀንም ሌትም ከበር ላይ አልነቃነቅ!”እንዲህ ቲለኝ በጣም ነበር የደነገጥኹት ቀጠለና “ቆይ አንቺ ምን ሆነሽ ነው? የድሀ አምላክ ፈጣሪ እስቲፈታሽ ቁጭ እማትይ!? “አለኝ።
እኔ ወድጄ አልነበረም ለመውጣት የወሰንሁት የትዬ ፀባይ እና ሁኔታ ባንድ ግዜ ተሰው ወደ አውሬነት በመቀየሩ እንዢ በየእለቱ ቀን እና ሌት ድንገት ይነሱና ያዙኝ ፣የፀሎት ቤቱን በር ከፈቱት እንዴ? ፀጉሬን ቆረጡት፣ ታልጋው ጋር አሰሩይ፣ ሁሉንም በር ምን ከፈተው? ሆኗልይ ወሬያቸው ምንም ታይፈጠር…
ይቀጥላል