ጓዴና እኔ፡-
አብረን በላን፣ አብረን ጠጣን
በሱ ስቃይ አቃሰትኩኝ
በህመሙ አልጋ ያዝኩኝ
በእኔ መሰበር እሱ አነከሰ
እኔ ላይ ሲዘንብ አካሉ ራሰ፡፡
ጥርሴ ቢመታ የሱ ወለቀ
እኔ ለወደኩ፣እሱ ደቀቀ፡፡
ኦፕራዎን ሲያደርገው ዶክተር
የራሱ ነበር/ ወይስ የኔ ሆድ የሚተረተር
ስንቱን ተካፈልን ስንቱን ተጋራን
እንደ አንድ ሳንቲም ሁለት ግልባጭ
አንድ ተብለን ፍፁም ሳንጋጭ
ሺህ ዓመት አልፎ ሌላ ሺ ሲቋጭ
ባልተጋራነው አንድ ነገር ላይ፣ታየ አሉኝ ሲቆጭ
እኔና እሱ፣ አንካፈለው የሌለ መስሎት
ምን ይሆን ብሎ ሲፈልግ ክፍተት፣
– – – እሷን አገኛት!
ያለፈው ፍቅር ጥልቅ ትስስብ፣
ወጥቶ ከልቡ፣ ብልቱ ሲያስብ
የቆመ አካሉን ሊሞርድባት፣
ካልጋዬ ወስዶ- እንደኔው አርጎ – ሚስቴን አወቃት፡፡
/ዲላ፣ 2003/
One Comment
Arife .new berta