Tidarfelagi.com

ለቃልህ ታምኜ…

በአንዲት እርጉም ቀን ልቤ ፅድቅ ሻተ;
ከመፅሐፍህ መሃል “ግራህን ቢመቱ ቀኝ ስጥ” የሚል ቃል ለነብሴ ሸተተ;
እልፍ ጠላቶቼ መንገዴን ተረዱ;
በእፀድቃለሁ ሰበብ መስከኔን ወደዱ ;
መጡ ተሰልፈው:-

ግራዬን ነገሉ;
ከቀኙም አንድ አሉ
ወገሩኝ ደጋግመው ክንዳቸው እስኪዝል;
ሁሉን ዝም አልክዋቸው ፅድቅህ ይበልጣል ስል !
እነሱ ቀጠሉ…
የሩቅ ጠላቶቼም እየተጠራሩ;
የድል ፈገግታና ቡጢ ሰነዘሩ
በዚህ ሁሉ መሀል አንተ ዝም ብለሀል;
በልቤ መሀል ላይ ቃልህ ይንገዋላል

…ቡጢያቸው በረታ ዝምታህ አየለ;
እልቦናዬ ውስጥ ትዕዛዝህ ዋለለ!
‘…ቀኝህን ስጣቸው’ ይል ቃልህ ተነቅሮ;
ግራህን ሲመቱ ቀኛቸውን አንግል ሆነ ተቀይሮ
ዝም ብሎ መጠፍጠፍ መነረቱን ትቼ;
እጥፍ ቡጢዎችን ሰነዘሩ እጆቼ;
በዙሪያዬ ሆነው ሲያሹኝ የነበሩ;
ጠላቶቼ ሁሉ ደንብረው በረሩ
ታዲያ ይህን ጊዜ አንድ ነገር ገባኝ…

እፀድቃለሁ ብሎ ፊትን ከመሰዋት;
ቀድመው እየመቱ መቺን ካገር ማጥፋት!

የራስ ናቸው፡፡ የማንንም ሃሳብ ለመፃፍ አልተከፈተም! የሚያስማሙንን ሃሳቦች እዚህ ካገኛችሁ እሰየው፡፡ ለመስማማት አንፅፍም፣ ለመፃፍ አንስማማም፡፡ ወዘተ

5 Comments

  • ሲራጅ ሙሀመድ commented on February 24, 2017 Reply

    በጣም ጥሩና አስተማሪ ነዉ ቀጥሉበት

  • henokmarye@gmail.com'
    legess commented on April 13, 2017 Reply

    ታሪክ ነዉ አገኘው፥ቀጥልበት

  • woudassegaga@yahoo.com'
    JOJO commented on October 26, 2017 Reply

    You are amazing…gifted …you are belong to Debebe Seifu, Tsegaye G.Mefihin….shakespear …serious, What you need to have is more practice, if possible a mentor.

    I am not a poet ….but i have read many books, mostly books written by western authors….cheers…A London.

  • solomon215mekonnen@gmail.com'
    ሰለሞን መኮንን commented on March 18, 2018 Reply

    ህይወቴ ባንተ ተሥተካክሏል፡፡

  • value commented on July 31, 2019 Reply

    አሪፍ ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...