ለከፋ ችግር የማይዳርግ ለከፋ

ከጥቂት አመታት በፊት” የምነው ሸዋ “ ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና፥ ለእህቱ ልደት፥ ዲሲ በሚገኝ ክለብ ውስጥ የእራት ግብዣ አዘጋጀ፤ በእሱ መጥርያ ወደ አሜሪካ የመጡ ዘፋኞች አንደኛው ጥግ ላይ ተከማችተው ተቀምጠዋል ፤ ፋሲል ደሞዝ ፥ አጫሉ ሁንዴሳ ፥ ሃይሉ ፈረጃ ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ምኞት፥ ስለ ለመጪው አሮጌ ዐመት

አዲስ ሆኖ ይምጣ፤ መጪው አሮጌ ዐመት ሰው በውድ ይገመት እህልና ሲሳይ በርካሽ ይሸመት። በጦም በፍስክም፥ ዱላ ለምንጠግብ ጨቅላ ልጅ አስርበን፥ ጆፌ ለምንመግብ ሰላም ይለግሰን ከለታት አንድ ቀን ፥ የሰው ወግ ይድረሰን። ያርሶ በሌ ልጆች በእንግዳ ሰው እጆች ሳናረጅ ከመጦር፥ ይሰውረንማንበብ ይቀጥሉ…

ስለአወዳመት

አሜሪካን አገር፥ አበሻና ላቲኖ የሚበዛበት ሰፈር ውስጥ ቤት ስከራይ ለደላላው እማቀርበው የመጀመርያው ጥያቄ “ ሽንት ቤቱ የብቻ ነው የጋራ ?” ሚል ነው። ወድጄ አይደለም፤ ደባል አበሻ ነህ እንበል! ዶሮ ወጥ ትወዳለህ! አሜሪካን አገር ያለው “ችክን” ደግሞ ችክ ያለ ነው ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ዘመም ይላል እንጂ

እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ። የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ። ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...