‹‹ለፀጥታ እንከፍላለን››

ከበር እንደገባሁ፣ ልክ እድሜ ልክ ሳደንቀው እንደኖርኩ ታዋቂ ሰው ሳየው ተንሰፍፌ አብሬው ‹‹ሰልፊ›› የተነሳሁት ከሰፋፊ ቅጠሎች ጋር ነው። እነዚህ ቅጠሎች በልጅነታችን ከደጃፋችን እንደዋዛ ቀጠፍ አድርገን ለጢባጢቢ የምንጠቀምባቸው ነበሩ። እዚያ ጋር እንደ ብርቅ መአድን የምነካካው ዛፍ ልጆች ሳለን ከሰው ግቢ ገብተንማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ምሽት

ከጥናት፤ከጥፈት እና ከዩቲውብ በተረፈኝ ጊዜ አውደለድልበታለሁ በተለይ አርብ ምሽት ፤በቤቴ አቅራቢያ ወደ ምትገኝ ባር ጎራ ማለት ደስ ይለኛል፤ እዛ አሪፍ የአይርሽ ድራፍት አዝዤ ወደ ባንኮኒው አፈጣለሁ፤ባንኮኒው ጀርባ የባሩ ባለቤት ቆማ አስተናጋጆችን ታሰማራለች ፤ባየችኝ ቁጥር ረጅም ፈገግታ ትለግሰኛለች፤ እኔም እንደ ውሃማንበብ ይቀጥሉ…

መንዲስ

ፈረንጆች አለመጠን ረጅምና ግዙፍ የሆነን ሰው Giant ብለው ይጠሩታል ። “ጋይንት” ብሎ እሚያነበው ስለማይጠፋ “ጃየንት” – /jai·uhnt መሆኑን አስታውሼ ልለፍ። በአማርኛ መንዲስ የሚል አቻ አለው። በታሪካንችን ዝነኛው መንዲስ ከታች ፎቶው ላይ ያለው ይመስለኛል። ይህ ሰማይ- ጠቀስ ሰውየ፤ መጀመርያ የቤኒሻንጉሉ ጌታማንበብ ይቀጥሉ…

ሞቱ በስርአት

ጥሩንባ ተነፋ ህልፈት ተለፈፈ እድር ቢያሰማራው ፤ህዝቤ ተሰለፈ የቅፅር ጥድ መስሎ፤ የተከረከመ በስልት እየሄደ፤በወግ እየቆመ ፖሊስ ከነ ማርሹ፤ ቄሱ ከነፅናው ፤ ከሳሹ ወራሹ፤ ወዲህ አሰለቃሹ፤ወዲህ የሚያፅናናው፤ ሁሉም ባጀብ ያልፋል፤በፈሊጥ፤በፊናው፤ ከቀብር መልስ ግን፤የንቧይ ቤት ሆነና፤ ተቀልሷል ሲባል፤ተመልሶ መና መንገድ ላይ ሲጋፋማንበብ ይቀጥሉ…

የዛኔውና የዛሬው ጷግሜ 5 አንድ ናቸዉን?

ጷግሜ 5 በኢትዬጽያ ታሪክ ዉስጥ የራስዋ ድርሻ ኢንዲኖራት ካደረጉ ክስተቶች መሃል የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት አንዱ ነበር። ምንም እንኳን ንጉሱም የካቲት 19/1966 ለተነሳባቸው ህዝባዊ አመፅ መፍትሄ ይሆናል በሚል ስልት የጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ሀብተወልድን ካብኔ አፍርሰው በእንዳልካቸው መኮንን የሚመራ አዲስ ካቢኔ በተማሪዎችናማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ሃገሬ ቆማበት››

ቢሮ መግቢያዬ አካባቢ ዘወትር ማለዳ አላጣውም። አንድ እግር የለውም። ሆኖም ሁሌም ክራንቹን ተደግፎ በፍጥነት ወዲህ ወዲያ ይላል። ሁለት የባለፀጋ ልጆች የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ደጃፍ ነው ላይ ታች ሲል የሚያረፍደው። ልጆቻቸው ከመኪና ወርደው ሶስት አራት እርምጃ በእግራቸው ቢራመዱ እንደ እንቁላል ከሽ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ሃሳብ አትሞትም(ሶስት ታሪኮች)

በመካከለኛው ዘመን በመላው አውሮፓ መንግስት የነበረችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያን አምባገነን ነበረች። በሃይማኖት ስም ታስራለች ፣ ታሰቃያለች ፣ ትገድላለች። ሳይንስ ተቀባይነት ያለው ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ጋር ስሙም ሲሆን ብቻ ነው። ከዚያ በተረፈ አዳዲስ ሃሳቦች ብቅ ካሉ መልሳ ትቀብራቸዋለች። ሶስት ታሪኮችን እንይ፦ማንበብ ይቀጥሉ…

ውጉዝ ከ መ ቄስ በላይ

በድሮ ዘመን አንድ አርዮስ የሚባል የነገረ ክርስትና ሊቅ ነበረ። እነሱ “አርኪሜዴት“ የሚሏቸው ስብስብ ደረጃ የደረሰ ሁላ ነበር። እናም በዛን ዘመን ጋሽ አርዮስ ተመራመርኩ፡ አወኩ አለና(በሴይጣን አነሳሽነትም ይመስለኛል) ቤተክርስትያንን ለሁለት የሚከፍል የኑፋቄ ትምህርት ይዞ ተነሳ። በዚህ ዘመን ደግሞ ቄስ በላይ የሚባልማንበብ ይቀጥሉ…

ሃይማኖት ወይስ ፖለቲካ

ያለፈውን አመት ለውጥ ተከትሎ ለአገራችን አንድነት፣ ለሕዝባችን ሰላም አደገኛ የሆኑ አጀንዳዎች በድፍረት ሲነሱ አይተን ደንግጠናል። ሰሞኑን ከኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ጋር ተያይዞ እየጮኸ ያለው መንፈሳዊነት የነጠፈበት አጀንዳ ዋነኛው ነው። የትላንት ታሪክ እንደሚነግረን አትዬጵያ-ጠል የሆኑ ኃይሎች ቤተክርስትያኗ ላይ አደጋ ሲጥሉ ቆይተዋል። ከጉዲትማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...