ሕዝባዊ ገጣምያን፣ እነዚያ ሬዲዮ ጣቢያ የሌላቸው፣ ግጥም ማንበብያ መድረክ ያልተዘረጋላቸው፣ ግጥሞቻቸው የሚያሳትሙበት ጋዜጣም ሆነ ሌላ ሚዲያ ያልተመቻቸላቸው እነዚያ አዝማሪያንና አልቃሾች ነገሥታቱን ብቻ ሳይሆን፣ በሕብረተሰቡ ውስጥ ልሂቅና ጉልህ የተባለውን ሁሉ ይተቻሉ። ቃሉን ያጠፈውን፣ በሕዝብ ላይ የቀለደውን ይገስፃሉ። ንጉሥ ሣህለሥላሴ ንጉሥ ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ጥቂት ቁንጣሪ ሃሳብ ከ “Born a Crime” መፅሐፍ!
የዚህ መፅሐፍ ፀሐፊ ትሬቨር ኖህ (Trevor Noah) በሙያው አዘጋጅ፣ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ተዋንያን እና ኮሜዲ ነው። ይሄ ፀሐፊ የኮሜዲ ስራውን ማቅረብ የጀመረው በሐገሩ በደቡብ አፍሪካ ነበር። ይሄንንም ስራውን በመቀጠል አሁን በሚገኝባት አሜሪካም በተፅዕኖ ፈጣሪነት በሚታወቀው ፕሮግራም ላይ ምፀታዊ ዜናዎችን የሚያቀርብ (Theማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦31)
ምነው ፍጣሪዬ በህልም የመሰለኝን እራሱን ህልም አርገህልይ ያየሁት ነገር እውን በሆነልይ አልሁና ደግሜ ታስበው ግን ህልም ባይሆን ሻንቆ ሊጨርሰን እንደነበር ውል ትላለብይ እንኳንም ህልም ሆነ ፈጣሪዬ ይቅር በለይ ብዬ ተመልሼ ተጠቅልዬ ተኛሁ፣ ጥዋት ተንቅልፌ የነቃሁት ተረፈደ ነበር።ብድግ አልሁና ድምጥ ለመስማትማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦30)
ጋደም እንዳለሁ ሸለብ አረገይ ወድያው ተሁለት አንዳቸው ለሽንት ቲወጡ ሰማሁ ብድግ አልሁና የክፍሌን በር በመጠኑ ከፍቼ ትመለከት የሽንት ቤቱ መብራት በርቷል።ትጠባባቅ ሻንቆ በውስጥ ሙታንታ ተሽንት ቤት ወጣ። እንዳየሁት በሁለት እግሩ የሚሄድ ትልቅ በሬ እንዢ ሰውም አልመስልሽ አለይ። ወደ እትዬ መኝታማንበብ ይቀጥሉ…
የዶክትርና ድግሪ ጉዳይ
በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የተዛባ አስተሳሰብ አለ። ብዙ ሰው ዕውቀትንና ብቃትን ድግሪ ከመያዝና ካለመያዝ ጋር ይመዝናል። ድግሪ ሳይኖራቸው ዓለምን የለወጡ ተመራማሪዎች እጅግ ብዙ ናቸው። ድግሪ ያለው ሁሉ ባለዕውቀት አይደለም። ይህ ማለት የድግሪን ዋጋ ማናናቅ አይደለም። መማር፣ መመራመር ተገቢ ነገር ነው። የዶክትርናማንበብ ይቀጥሉ…
ጃጋማ ኬሎ
በ15 አመቱ ሀገሩን ከወራሪ ፋሽስት ኢጣልያ ጦር ነፃ ያወጣው ባለ አፍሮ ፀጉሩ ወጣት አርበኛ: ጃጋማ ኬሎ በሚልድሬድ ዩሮፓ ቴይለር ጃጋማ ኬሎ ሀገሩ ኢትዮጵያን ከ1928ቱ የኢጣሊያ ወረራ ለመከላከል ወደ ጫካ በመግባት መዋጋት ሲጀምር ዕድሜው ገና 15 ብቻ ነበር። በመስከረም 1928 ኢጣልያዊውማንበብ ይቀጥሉ…
ፍልስፍናህን ኑርበት እንጂ አታውራው!
(“Do not explain your philosophy. Embody it”) ፈላስፋነት ጠያቂነት፣ መላሽነት፣ መርማሪነት፣ ምክንያታዊነት፣ ጥልቁን አዋቂነት፣ ረቂቁን ተረጂነት፣ እውነትን ፈላጊነት ነው። የፈላስፋነትን ባህሪ መላበስ የሚቻለው በጠያቂነት ሱስ መጠመድ ብቻ አይደለም። አዎ! ፈላስፋነት ድንቅ ጥያቄ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ከባባድ መልሱንም ጭምር መፈለግ ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…
መርፌ
አብዬ መንግስቱ ለማ እጅግ ሲበዛ አስተዋይ ነበሩ። አማሪካን ሀገር ሄደው ተምረው ሲመለሱ ከሀሳብ ሁሉ ገዝፎ ሀሳብ የሆነባቸው ከአንድ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ጋር ድንገት ቢገናኙ ሊጠይቃቸው የሚችለው ጥያቄ ነበር። ውጪ ተምረው እንደመጡ ሲያወሩ ድንገት የሰማ ገበሬ ጠጋ ብሎ “መርፌ ትሠራለህ? ” ብሎማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦29)
ቁልቁል እየተመለከቱ ሽቅብ ቲወጡ የልቤ ትርቷ ተመቅፅበት እጥፍ ሆነይ። ተጦሎት ቤት ወጥተው ወደ ምኝታ ክፍላቸው እስቲገቡ ቸኮልሁ።እትዬ ተዛ ድብቅ ዋሻ ወጥተው እንዳበቁ የጠሎት ቤቱን ድብቅ የወለል በር ዘግተው ተመሄድ ይልቅ አፋፉ ላይ ተገትረው ቁልቁል ቲመለከቱ ይህቺ መሰሪ ሰትዬ ምን ሆናማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦28)
ተሽጉጡ መሀል አንድ በቁመቷ ዘለግ ያለችውን መረጥሁ። አይኔ ሽጉጦቹ ታሉበት መሳቢያ ውስጥ ጥግ ላይ እተቀመጡት ነገሮይ ላይ አረፈ። ትዝ ይለኛል የዛሬ ሶስት አመት አከባቢ ታይሆን አይቀርም። ቡና እያፈላሁ ነበር ጋሼ እትዬን እንዲህ አላቸው ” ሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ጥሩ ትላልሆነማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦27)
እህን ግዜ እራሴን መቆጣጠር ተስኖይ ጩሂ ጩሂ ትላለኝ አፌን በሁለት እጄ ግጥም አድርጌ ያዝሁት። አጣብቆ ተያዛት ግድግዳ ላይ ትንፋሽ አጥሯት አይኗ እስቲገለበጥ አቆያትና ተላይ አንገቷን ባንድ እጁ እንዳነቃት ተስር ሁለት እግራን ባንድ እጅ ጠርንፎ ሽቅብ በማንሳት እትከሻው ላይ ቲሸከማት እሷንምማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦26)
ዘንዶው መስኮት የሚያህል አፉን ከፍቶ የተወረወረለትን ሰውዬ መሬት ታይነካ ቀለበው።ተመቅፅበት እስተወገቡ በመዋጥ ሰውየው ነብስ ይዞት ቲታገለው ተግራ ወደ ቀኝ ተቀኝ ወደ ግራ እያላተመ ወደ ውስጥ ያስገባው ዥመር። ልጅቱ እትዬ ላይ እያፈጠጠይ ጨካኛይ ናችሁ አረመኔዋይ ናችሁ ፈጣሪዬ ለምን ዝም አልህ እባክህማንበብ ይቀጥሉ…
የግንቦት ህልም
ትብልዬ
የማያልፉት የለም ፣ ያ ሁሉ ታለፈ ታጋይ የህዝብ ልጅ ፣ ምርጫ በሌለበት ፣ ምርጫ እያሸነፈ በደሙ በላቡ ፣ ትውልድ አከሸፈ🙄(ርዕሱ አይደለም😂) ።። መቸም የማያልፉት የለም ያ ሁሉ ታልፎ ያ ሁሉ መሥዋእት ተከፍሎበት የግንቦት 20 በዓል አከባበር በዚህ ደረጃ ቀዝቅዞ ማየትማንበብ ይቀጥሉ…
ፉት ሲሉት ጭልጥ
ግንቦት ሃያ ተመልሶ መጣ። ከሶስት አመታት በፊት የግንቦት ሃያ አረፋፈዴን እንደዚህ አውግቻችሁ ነበር ። ።።።።።።።።።።።። ዛሬ.. ግንቦት 20 ማለዳ 1.45 ከበራፌ ላይ ቀጭን እና ስለታም ድምፅ ‹‹ልዋጭ! ልዋጭ!›› እያለ ሲጮህ ነቃሁ። የዚህ ሰውዬ ድምፅ በዛሬ ቀን ከነገር ሁሉ ቀድሞማንበብ ይቀጥሉ…
ኢትዮጵያ ቅኝ ገዢ፤ ኤርትራ ነፃይቱ ምድር¡
ትልቅ ስላቅ ነው። ኢትዮጵያን የኤርትራ ቅኝ ገዢ አድርጎ መሳል ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ ያለህን የታሪክ፣ የማህበረሰብ፣ የባህል፣ የሀይማኖት፣ የስነልሳን ሕብረቀለማትን መካድ ነው። Why we buried the distant history we lived in? ጥንት፡- ደአማታውያን፣ አክሱማውያን ሀገርን በሚመሩበት ዘመን “ባህረ ነጋሽም (የአሁናማንበብ ይቀጥሉ…
ሰንኖር ማንም ሰንሞት ምንም!
በየቀኑ በሚባል ሁኔታ በታላላቅ አለማቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋማት ፣ዩኒቨርስቲዎችና የትምህርት ኢኒስቲቲዩሽኖች ከመላው ዓለም የሚጋበዙ የሳይንስ ፣የሃይማኖት ፣ የኪነጥበብ ሰዎች የሚጋበዙባቸው ቁጥር ሰፍር የሌላቸው ሲንፖዚየሞች ዎርክሾፖች ይካሄዳሉ ! ዓለም በሙሉ እንዴት የተሻለ ዓለም እንፍጠር የሚል ሃሳብ በእያንዳንዱ ደይቃ ያወርዳል ያወጣል! ታዲያማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦25)
እኝህ ሴትዬ መጥተው ተምድረ ገፅ ታይሰውሩኝ በፊት የማመልጥበት መላ ቢከሰትልይ ብዬ ታወጣ ታወርድ ቆየሁ። ትለ ባለቤቶ መፈታት ቲያወሩ ውስጤን ደስ ብሎት ትለነበር ይሆናል ታይታወቀይ ያመለጠኝ ልበላቸው አይ ይህም አይሆንም አንድ ግዜ አላልሁም ብያለለሁ አላልሁም በቃ በዚሁ ተመድረቅ ውጪ ሌላ ማምለጫምማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦24)
አረ ምንም አላልሁም እትዬ ምን እላለሁ ብለው ነው። “ቆይ..ቆይ ቆይ ቆይ … እሄን ሁሉ አመት ሰናይት ብለው ሲጠሩሽ አቤት ሲያዙሽ እሺ ከማለት ውጪ ድምፅሽ የማይሰማ ልጁ ዛሬ እንደማይረባ ከሰል እላዬ ላይ የምትንጣጭብኝ ምንድን ነው ሚስጥሩ ለመሆኑ? እ ንዴ: ማን ነውማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦23)
ቀማምሰው እንደመጡ የአይናቸው መቅላትና የድምጣቸው መቀየር ያስታውቃል።መደንገጤ እንዳይታወቅብይ ጥረት እያረግሁ የለለይን ምራቅ ሁለቴ ዋጥሁና …. እንዴ እትዬ መጡ እንዴ ቆዩ ምነው? ብቻዬን ትለተቀመጥሁ ነው መሰል ተሌቪዥኑን ታናጠፋው በፊት ትናይ የነበረው የሀገራችን ክፉ ነገር በሙሉ ፊቴ ድቅን ቢልብይ ሀገሬ አሳዘነችይ።ተዛ ምንማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦22)
ም…ን…አልክ..በልሁ? “ምን ላርግ ሰንዬ …” በል ዝም በል አልሁና አፉን ያዝሁት።የሰይጣን ጆሮ አይስማው በልሁ እንዳትደግመው። አልሁት። እንኳን እቤቱ ተቀምጠን በየሄድንበትም እየተከተለ አላስቀምጥ ያለን ሰይጣን በልሁ ያለውን ተኔ ቀድሞ እንደሰማው እያሰብሁ።እሄን ተማረግ ሞቴን እመርጣለሁ!። ጭራሽ በጄ እንዳጠፋህ ጠየከኝ በልሁ! ደግመህ እንዳታስበው።ደሞማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦21)
“ሀብታቸውን ተጠቅመው እዚህ ላደረሰቻቸው ሀገር ትምህርት ቤት እና ሆስፒታል ተመገንባት ይልቅ በየጉራንጉሩ እስርቤት እየገነቡ ለዘመናት የፍዳ ቀንበር መሸከም ያመረረውን ትውልድ በሸክም ላይ ሸክም በችግር ላይ ችግር እየጨመሩ ተዘመን ዘመን በጦርነት ተወልዶ በጭቆና አድጎ በጭቆና እንዲሞት ያደርጉታል። ሰንዬ ተድህነት ባያወጡን እንኳማንበብ ይቀጥሉ…
ዐምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ” (ክፍል ሁለት)
የጥንት ግብጻዊያን አንድ ልማድ ነበራቸው። በየዓመቱ ቆንጆ ልጃገረድ ይመርጡና ለአባይ ወንዝ (ኒል/ናይል) ይሰውለት ነበረ። እነዚያ ግብጻዊያን ናይል በየዓመቱ መስዋዕቱን ካላገኘ ውሃውን ይቋጥርብናል የሚል እምነት ነበራቸው። አምር ኢብን ኣስ ሀገሪቱን በያዘ በጥቂት ወራት ውስጥም ግብጻዊያኑ ለወንዙ መስዋእቱን ለማቅረብ እንደሚፈልጉ ነገሩት። አምርማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦20)
…ሳጥናኤል ወ አጋንንት አስርቱ ትዛዛት.. ትእዛዝ ሶስት፦ እሄ ጦሙን እያደረ ፈጣሪውን ጥዋት ተነስቶ የሚያመሰግን ህዝብ ወደኔ ለማምጣት ብልሀተኛች ሁኑ። ነፃ እናወጣችኋለን እያላችሁ ነፃ ሆነው እንዳይኖሩና ዘወትር ያልታሰሩበትን ገመድ ለመፍታት እረፍት አልባ ሂወት እንዲገፉ በማድረግ እረፍት ያገኙ ዘንድ ምግባረ እርኩሰትን እንዲፈፅሙማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦19)
ቄራ ነው”። አለይ። እቤቱ ግድግዳ ላይ ተትንሿ ቢላ ዥምሮ እስከ ላይኛው ግዥራ ፣ተትንሿ መቀስ ዥምሮ እስተ ትልቁ የጥድ ማኸርከሚያው መቀስ ፣ ማዋለጃ የሚመስል ባለ ጎማ አልጋ፣ተበልሁ ጀርባ በስተቀኝ 2 ተከፋች የቀብር ሀውልቶይ ቲኖሩ በስተግራ ደሞ አንዱ ጥቁር መጋረዣና አንድ ቀይማንበብ ይቀጥሉ…
አምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ”
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ለአፍሪቃ አህጉር የመጀመሪያ የሆነውን መስጊድ ነው። ይህ መስጊድ የተሰራው በ641 ሲሆን የሚገኘውም በግብፅ መዲና ካይሮ ውስጥ ነው። መስጊዱ የሚጠራው በመስራቹ በ“አምር ኢብን ኣስ” ስም ነው። ይሁንና አምር እና ጓዶቹ መስጊዱን የሰሩት በአል-ፉስጣጥ እንጂ በካይሮ አልነበረም። ታዲያ መስጊዱንማንበብ ይቀጥሉ…
የአገር ፍቅር በቪያግራ !?
ምን ሰለቸኝ ? ፉከራ! ታዝባችኋል ግን ? በቃ ወጣቱ ሁሉ በየመድረኩ ነጭ ልብሱን ለብሶና አናቱ ላይ ባንዲራ አስሮ እየተንዘረዘረና ዱላውን እየወዘወዘ ዘራፍ ማለት ሆነኮ ስራው ! ጭንቅላት ባንዲራ ስለታሰረበት አይለወጥም! ባንዲራም አናት ላይ ሰለታሰረ ከፍ አይልም! ጭንቅላት በትምህርት እና ዊዝደምማንበብ ይቀጥሉ…
”ኦ አዳም”
አዳምን ልነካው ስለ ደፈርኩ ይቅርታ እጠይቃለው። ይቅርታ ጠይቄ ግን እፅፋለው። ((የማፈንገጥ አንድ ገፅ የአዳምም መልክ ነው።)) ግራጫ ፀጉር አለው። ትከሻው ሰፊ ነው። አይኖቹ መነፀር ይለብሳሉ። እጆቹ ለስላሳ ናቸው። ጣቶቹ ሲጋራ ይይዛሉ። እሱን ሳይ ሲጋራ አጢስ ብሎኝ ያውቃል። ብሄራዊ ሰፈር የምከርምማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦18)
እትዬ ተጣጥበው እና ተኳኩለው እንደጨረሱ ተላይኛው ክፍሎች ባንዱ ውስጥ ገቡ። ወድያው አንድ የመሂና ታርጋና መፍቻ ይዘው በመውጣት መሂናቸው ላይ የነበረውን ታርጋ ፈተው ቀየሩት። ተዛ የቀየሩትን ወደ ቤት አስገብተው የጎንዬሽ ገርመም አርገውይ ነይ የውጭውን በር ክፈች አሉይ። የከፈትሁበትን ቁልፍ ተቀብለውይ ተውጪማንበብ ይቀጥሉ…
በእዳ የተያዘ ጡት
ጠበቃ:— የተከበረው ፍርድ ቤት ተከሳሽ አስቀድሞ በግልፅና በአፅኖት እንደተናገረው ከደንበኛዬ ድርጅት የመዘበረውን 120 ሺህ ዮሮ ለፍቅረኛው ጉች ጉች ያለ ጡት ማሰሪያነት ተጠቅሞበታል። የቀረቡት ማስረጃዎች እንደሚያመላክቱት በእጁ የሚገኝ ውድ ንብረት የፍቅረኛው ጡት ብቻ ነው። ዳኛ:— ምን እያመላከትክ ነው? ጠበቃ:— ይሄ ሰውማንበብ ይቀጥሉ…
የሸገር ገበታን በጨበጣ ታደምኩኝ
በትላንቱ ስብሰባ ላይ ለመታደም ወደ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) ቅጥር ግቢ ልገባ ስል በር ላይ የቆመ ፖሊስ በዲያስፖራ ቅላፄ “ሞባይል ይዘሃል?” አለኝ። እኔም ጥያቄው ገርሞኝ “አዎ” አልኩት። “ሞባይል ይዞ መግባት አይቻልም!” አለኝ። ከአንዴም ሁለቴ በECA በተዘጋጁ ስብሰባዎች ላይ ተሳትፌያለሁ። ያኔማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦17)
እሳቸው ቲጮሁ እኔ እንደፈዘዝሁ በልሁ ጋር ትለረሳሁት ሰሀን ታስብ መላሽ ትላልሰጠኊቸው በሽቀው… ወደ እኔ ይበልጡን በመጠጋት “ያን ሁሉ ሳንኳኳ ምን ስትሰሪ ነበር እያልኩሽ እኮ ነው ብለው ቲያፈጡብኝ ተሄድኩበት ሀሳብ ባነንሁና የባለፈውን እንደመብረቅ ልብ የሚያቀዘቅዝ ጥፊያቸውን ታያልሱኝ በፊት… ወደ ላይም ወደማንበብ ይቀጥሉ…
“ኑ ሀገር እንስፋ!”
ክፍፍል መችነበር፥ በአምላክ አሰራር ፥በቅድመ አፈጣጠር ሰው ሰው ብቻ ነበር ፥ዘሩ ሳይቆጠር። ሰውነት ተንዶ፥ እንዲህ እንደዛሬ ፥ ሳይኖር መበታተን የመቆጣጠር ዛር ፥ መቃብር ሳይከተን አንድ እናት ነበረን ፥ ቀሚሷ እንደኪዳን ፥ ሁላችን ምንለብሰው ዛሬ ተለያይተን፥ ክብሯን እንደ እቃቃ ፥ ዳቦማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦16 )
የሞት ሞቴን ይቅር ይበሉይ እትዬ ታለወትሮዬ ዛሬ የታሸገ ውሃ አምሮት ውል ቲልብይ ግዜ ነው ትለተኙ ታላስፈቅዶት የወሰድሁት አልሁና በድንጋጤ ምን እንደምሰራም ታይታወቀይ ውሃውንም አፌንም ከፈትሁና አንቆረቆርኩት። ታሁን ታሁን እትዬ ዘለው አናቴ ላይ የሚከመሩብይ ትለመሰለይ አይኔን ታልነቅል ትመለከታቸው ..ቃል ታፋቸው ታይወጣማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦15)
እኔም አሁን አንድ ነገር ታፌ ቢወጣ እትዬ ተነስተው ተነጨርቄ ተመዋጥ አይመለሱም። “ተእብድ አጠገብ ፥ ድንጋይ አይወረወርም” አለች ያቺ ያገር ቤቷ ሚስኪን ጎረቤቴ። እዚህ እማ ምን ኮረቤት አለ። ሰው ሁሉ ደም የተቃባ ይመስል ተሸሽጎ ነው የሚኖረው። ተቸገርኩ ቢባል ለጋሽ፣ ኡኡ ቢሉማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦14)
ብጋደምም እንቅልፍ ተየት ይመጣል ። ፈጣሪዬ እባክህ ክፉውን እርቅለት። እንደው በልሁ ምንም ታይሆን በፊት አንዴ ባወራሁት እና ምን እንደሚለኝ በሰማሁ። እሄን አርጊ ታለኝ ምንም ይሁን ምን ተማረግ አልመለስም !። ተዳንም ባንድ ላይ! ተሞትንም ባንድ ላይ! እዚህ ቤት ውስጥ ምን አለውማንበብ ይቀጥሉ…
ክርስቲያኗ ፍቅረኛዬ ናፈቀችኝ!
ረመዳን ሲመጣ ከማስታውሳቸው ሰዎች አንዷ ናት። በእድሜዋ ከኔ በሁለት ዓመት ታንሳለች። ከ1996-2004 በነበረው ዘመን የኔ ምርጥ ጓደኛ እርሷ ነበረች። ሌላ ሴት የመጋበዝ ባህል አልነበረኝም። እርሷን ግን ከፒያሳው ኡመር ኻያም ጀምሮ እስከ ውድ ሬስቶራንቶች ድረስ እየወሰድኳት እጋብዛት ነበር። እርሷም አጸፋዋን በመክፈሉማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦13)
ደምስሮቼ ሁሉ ስራቸውን አቁመው ማን እንደነካኝ ለማየት አንገቴን ወደ ጀርባዬ ማዞር ተሳነኝ። የሞትኩ ያህል ትንፋሽና ድምጤን አጥፍቼ በፍርሀት ተውጬ ትጠባበቅ ተውሃላ የነካኝ ነገር እዛው እነካኝ ቦታ እንደተጫነኝ አልንቀሳቀስ ቲል የሞት ሜቴን ዘወር ብዬ ታይ። ተደነገጥኩት ባልተናነሰ ባስደነገጠኝ ነገር በሸቅሁ። “ፍርሀትማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦12)
“በቀላሉ እማ ገድዬ አልቀብርህም በቁምህ አስቃይቼ እሄን እልህክን አበርድልሀለሁ። “አሉና ሽጉጡን ታፉ ውስጥ ቲያወጡት መርፌ ወግተው ወደ ሰውነቱ ያንቆረቆሩት ፈሳሽ ምን እንደሆን እንጃ ታፉ ውስጥ የሚዝለገለግ ነጭ ፈሳሽ እየወጣ እንደቅድሙ ለመጮህ ተሳነው መሰል በለሆሳስ እያቃሰተ ” ግደይኝ አንቺ አረመኔ ሴትዬማንበብ ይቀጥሉ…
ህክምናው ይታከም
የዛሬ ሰባት አመት ግድም ጆሮን እያመመኝ በጣም እሰቃይ ነበር፤ጉዳዩን መነሻ አድርጌ” መግባት እና መውጣት” የተሰኘውን ልቦለድ በመፃፍ ፤ስቃዩን ወደ ሳቅ ቀይሬዋለሁ፤ አሁን ያልፃፍኩትን ልንገራችሁ። በድፍን ጦቢያ ዶክተር ነጋን የሚያክል የጆሮ ሀኪም የለም ተባልሁ! ወደ ፒያሳ ወረድሁ፤ ዶክተሩ በትህትና በጨዋነት መረመሩኝ፤ማንበብ ይቀጥሉ…
“ለይለቱል በድር” እና “በርቲ በርቲ” በሀረር
ረመዳንን የሚጾም ሰው ስለ“ለይለቱል ቀድር” ማንነት በሚገባ ያውቃል ብዬ እገምታለሁ። “ለይቱል በድር”ን ግን ብዙዎቻችሁ ላታውቁት ትችላላችሁ። ስለዚህ በዛሬው የረመዳን ወጋችን “ሀረር ጌይ” በተሰኘው መጽሐፌ ስለ “ለይለቱል በድር” የጻፍኩትን አጋራችኋሁ። ***** “በድሪ” እና “በድሪያ” እኔ በተወለድኩበት አካባቢ በጣም ከሚታወቁት ስሞች መካከልማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 11)
እንዳልፈጠፈጥ ፈራሁ ቀና ብዬ እራሴን ለማረጋጋት ሞከርሁ። ጥጉን ይዤ እምዬ እሄን ጉዴን አላየሽ እስተዛሬ ታውሬ ጋር አብሬ ነው የኖርኩት አልሁ ለራሴ። ትንሽ ተቀመጥሁና ትንፋሽ ወስጄ መልሼ በሆዴ ተኝቼ ቁልቁል ትመለከት የበልሁ ሁኔታ አንጀቴን አላወሰው። እትዬ የ ባእድ የአምልኮ ጠሎታቸውን ጨርሰውማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 10)
ሻወር ቤት ውስጥ ሆኜ ያለሁበት ክፍል ውስጥ ዘው ብለው ቲገቡ እኔኑ የተከተሉኝ መስሎኝ ወደ ውስጥም ወደ ደጅም ትንፋሽ ማውጣት ተስኖኝ ፀጥ አልሁ። እሳቸው ግን እክፍሉ እንደገቡ ግድግዳዉ ላይ የተሰቀለውን ትልቅ ስእል ተግድግዳው ላይ አወረዱ። ደሞ ቀጠሉና ቀለሙ ተግድግዳው ጋር የሚመሳሰልማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 9)
ቀጥታ ወደ ክፍሌ ገባሁ የሰውየው አስተያየት እና አስፈሪ ገፅታ ተፊቴ አልጠፋ አለኝ።ትናንት ያንን ምስኪን ደሀ በልሁን አስሬ እስሩ እየሄድኩ ተፖሊሶቹ ጋር ታልሄዱኩ እያልሁ ትጨቀጭቀው ሰውየው አይቶን ታይሆን አይቀርም እትዬ በልሁ ሚስጥር ያወጣ መስሏቸው የጨከኑበት። አይ እትዬ ምን አይነት ጨኳኝ ሰውማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ግን…. ባይሆንስ?››
ቴድ ቶክ ማየት በጣም ደስ ይለኝ የለ? ከምሳ ሰአቴ ቀንሼ ነው የማየው…አፌን በምግብ፣ አእምሮዬን ደግሞ በጥሩ የቴድ ቶክ ተናጋሪዎች ታሪክ ስሞላ ፍስሃ ይሰመኛል። በሁለት በኩል መመገብ ነዋ! ዛሬ ያየሁት የዳያንን ነው። ዳያን ቮን ፈርነስተንበርግ (ስሟ መርዘሙ፣ ደግሞ ማስቸገሩ).. ዳያንማንበብ ይቀጥሉ…