ፈቅደን ሲመሩን፤ ችቦ ተቀባይ ለሚነዱን ግን ፤ አሻፈረን ባይ ካልነኩን በቀር፤ ቀድመን ማንዘምት ከጋሻ በፊት ፤ ጦር የማንሸምት ኢትዮጵያዊ ነን! ህብር ያስጌጠው፤ ህይወት ለማብቀል ዘር ሳናጣራ ፤ የምንዳቀል ለነዱን ሰይጣን፤ ለመሩን ሰናይ ጌታን ከገባር፤ ለይተን ምናይ፤ ኢትዮጵያዊ ነን! ብዙ ህልሞችን፤ማንበብ ይቀጥሉ…
ስግር ልብወለድ፣ ሕጽናዊነት (ክፍል 1)
‘I see the world in a grain of sand And a heaven in a wild flower…. ‘ (1803) እንግሊዛዊው ገጣሚ ዊሊያም ብሌክ የሰፈራችን ልጅ ቴንሳ እንዲህ የሚል ግጥም አለው፤ ‘አለምን በደቃቃ ጤፍ አያታለሁ አገሬንም በቁራሽ እንጀራ’ የዋህነት እንዴት ያደክማል? ከተባለውማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ቦግ – እልም››
ቅድም ባንክ ሄጄ ነው። የሚመለከተኝን ቅፅ ሞልቼ ከደብተሬ ጋር ወረፋ አስያዝኩና ሊሞላ አንድ ሰው በቀረው አንዱ አግዳሚ ላይ ተቀመጥኩ። ከመቀመጤ መብራት ሄደች። ‹‹ኤዲያ! ምን ጉድ ነው …አሁንማ ባሰባቸው….›› አሉ አጠገቤ የተቀመጡት ሰውዬ። ሙሉ ልብስ ካለ ከረቫት የለበሱ፣ ባርኔጣ ያጠለቁ ስልሳዎቹማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹እኔን ነው?››
ገና እምቦቃቅላ ሳለሁ፣ አባቴ ..‹‹ጠይም ልጅ ባይኔ ላይ ተሸክሜ እንደኩል›› እያለ ጥቁረቴን የሚያወድስ ዘፈን ይዘፍንልኝ ስለነበር ከኩል የተሰራሁ ይመስለኝ ነበር። ከኩል ስለተሰራሁ ፣ ገና ልጅ ሳለሁ ኩል መኳል ያጓጓኝ ስለነበር አባቴ በእሱ ሃገር ሴት ልጅ የምትኳለው ልትዳር ስትል እንደሆነ እያጫወተ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹በኤንጂኦ ስብሰባ ላይ ብልህና አርቆ አሳቢ የመምሰል ጥበብ ….››
ትላንት ዘ ጋርዲያን ላይ ከወጣ የከረመ አንድ ፅሁፍ ሳነብ ሁሌም የሚያስቀኝ፣ የሚያሳዝነኝ እና የሚያስገርመኝ ነገር ስለሆነ እሱን ተመርኩዤ በዚህ ጉዳይ ለምን አላወራም ብዬ አሰብኩ። ጌሪ ኦውን የጻፈው የጋርዲያኑ ፅሁፍ ርእስ 10 tricks to appear intelligent during development meetings ይሰኛል።ማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ጨዋታው ፈረሠ…›› (ክፍል ሁለት)
ይሄ ኑሮ ነው? ከዚህ ኑሮ ለመነጠል የምፈራው ለምንድነው? ይሄን መፈራረስ የጀመረ ጎጆ ፈፅሜ መደርመስ የምሰጋበት ምክንያት ምንድነው? በትዳሬ የደስታ ቅንጣት፣ የእርካታ ፍንጣሪ ሳይኖረኝ፣ ይሄ ምሶሶው የተንጋደደ ቤቴ ቢፈርስ አለም እላዬ ላይ የምትፈርስ የሚመስለኝ ስለምን ነው? ለውሳኔ ምን አውሸለሸለኝ? ሌሊቱንማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ጨዋታው ፈረሠ…›› (ክፍል አንድ)
ሄኖክን ከተዋወቅኩ ጀምሮ ልቤን በደስታ ያዘለለ የፍቅር ጊዜ ትዝ አይለኝም። በሴት ወግ ፍቅሩ ይዞኝ የተጃጃልኩበት፣ ነጋ ጠባ ስለእሱ ያሰብኩበት፣ እንቅልፍ ነስቶኝ የተቸገርኩበት ወቅት ትዝ አይለኝም። ትውውቃችን ተራ እና ቀላል፣ ለሰው ቢነግሩት አፍ የማያስከፍት- አ-ላስደናቂ ነበር። በምኖርበት ህንፃ ላይ ለወራት ክፍትማንበብ ይቀጥሉ…
ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል እብሪት ግን ለውድቀት ይዳርጋል
ጎሽ! ጎሽ! እሰይ —- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን በየእለቱ እየወደድኩት ነው። ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ያለኝ አድናቆትም እየናረብኝ ነው። ታዲያ አቶ ኢሳያስ ዛሬ ያደረገውን አስገራሚ ነገር ልብ ብላችኋልን? ፊርማውን ሲፈርም እኮ የባድመ ጉዳይ ከቁም ነገር ተቆጥሮ አልተነሳም። ድሮስ? ድሮማ “ባድመን ካላስረከባችሁን ድርድርማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ልቤ››
አዲስ ፀባይ ካመጣች ሰነባበተች። ስሙን ለመጥራት ሰበብ መፈለግ እስክታቆም ወዳዋለች። ይሉኝታዋን እንደ ቆሸሸ ልብስ እስክታወልቅ ልቧን ሰጥታዋለች። ፍቅር ይሉኝታ ያስጥል የለ? ምን ይሉኝ ፍርሃትን ይገፍ የለ? እህ…እንደሱ። የጀማመራት ሰሞን ፣ ‹‹በረከት እኮ…ሂ ኢዝ ሶ ስማርት…እኛ ቢሮ የሚቆይ አይመስለኝም…ማስተርሱን ይጨርስ እንጂማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ሚያው››
አብረን ያየን ሰው ሁሉ ‹‹አፈስሽ አፈስሽ›› እያለ ያወራል። ቆንጆ፣ ሎጋ፣ ረጋ ያለ እና ዝምተኛ ነው። የወንድ ልጅ አማላይነት የተሰራው ከእነዚህ ተንኮለኛ ንጥረ ነገሮች አይደል? በፍቅር መውደቅ ከገደል እንደመውደቅ ያማል? በፍቅር መያዝ እንደ ተስቦ ያማቅቃል? አዎ። ቢሆንም እያመመኝ እወደዋለሁ። እየማቀቅኩ አፈቅረዋለሁ።ማንበብ ይቀጥሉ…