አንድ ተረት ልነግራችሁ ነው በቅድሚያ ግን ጭብጤን ላስቀድም። ላለፉት 13 ወራት እንደ ቀበሌ መታወቂያ በኪሴ ይዤ የማንከራትተው ፓስፖርቴ ከፍተኛ እንግልት ደርሶበታል። ከሀገር ሀገር ለመዟዟር ብቻ ያገለግል የነበረው ፓስፖርት፤ ኢትዮጵያም ውስጥ በተንጻራዊ ነጻነት ለመዘዋወር ብቸኛ አማራጬ ሆኖ ቆይቷል። ይህ ሁሉ የሆነውማንበብ ይቀጥሉ…
ይሄ የኔ ትውልድ
(የዚህ ፅሁፍ ባለቤት፣ እራሱን ከትውልዱ መገለጫዎች አልነጠለም፣ አይነጥልም። ፅሁፉም ፍፁም ጅምላ ምደባ አይደለም) ይሄ የኔ ትውልድ የተካደ ትውልድ ነው። ከገዛ ዘመኑ ተገፍቶ ላለመውደቅ ፈፋ ዳር የሚውተረተር ምስኪን። ሀገር የሚያስረክቡት መስሎት ደጅ በመጥናት ሲንከራተት ቆይቶ ገሚሱ ወደ ሃይማኖት ቤት፣ ገሚሱ ወደማንበብ ይቀጥሉ…
ቀጠሮና እሷ
ዜጎቻችን ቀጠሮ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ቢደመር ለፍርድ ቀን፡ በዓለም የመጠናቀቂያ ዕለት የተከመረ ሐጢያት ሆኖ መንግስተ ሠማያት የሚባል ቦታ አንድ ሀበሻ አይገባም ነበር። መልካም ቀጠሮ አክባሪዎች በእግዜር ቀኝ ሲሰለፉ፤ 80ሚሊዮን የሚደርሰው ሀበሻ በጠቅላላ በእግዜር ግራ። ግራ ይግባንና። የማይገባኝ ግን ምክንያቱ ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…
እወድሻለሁ እኔም
«ምንድን ናት» ለሚል ጠያቂ ትርጉምሽን ባልፈታም «ሀገር ሃሳብ ብቻ ነው» የሚል ሞጋች ባልረታም ሀገሬ ሆይ እወድሻለሁ! እርግጥ፣ ሲበድሉሽ እንዳላየ፣ ሲገድሉብሽ እንዳልሰማ ሲተኩሱ እንዳልደማ ጌቶች ሲቆጡ ለስልሶ ጫን ሲሉ አፈር ልሶ ሲያስሩብሽ እንዳልታሰረ ሲመቱሽ እንዳልነበረ ሆኖ ማለፉን አውቃለሁ ቢሆንም እወድሻለሁ። «የህዝብማንበብ ይቀጥሉ…
ሀገርኛ በሽታ ይዞ፣ የባህር ማዶ መድሃኒት የመፈለግ ክፉ አባዜ
አንዳንድ ሰዎች አሉ፤ያልተማሩ የምናላቸው። ሲያማቸው ጎረቤታቸው ጋር ሄደው «ባለፈው እንዲህ እንደኔ ሲያምህ ሀኪም የሰጠህ መድሃኒት የቷ ነበረች? » ብለው ተቀብለው ያለምንም ምርመራ የሚውጡ፤ እቺን ሀገር የመሰሉ!! የውጭውን ሁሉ እያመጣን እላያችን ላይ ማራገፋችን ለዓመታት የሚከተለን ችግር ነው። እየተከተለ ይኮረኩማናል። አንሰማም። አንነቃም።ማንበብ ይቀጥሉ…
ጀምጃሚዎች (ቅፅ 2)
የቸኮልየት ሆቴል ባለቤት ጋሽ ካሌብ ባሁኑ ጊዜ ከጎኔ ይገኛሉ። የሆነች: በሳቅና በሳል ማሃል ያለች ድምፅ እያሰሙ አጠገቤ ያለውን ቁሞ-ቀር ሳይክል ይጋልባሉ። ጋሽ ካሌብ ወደ መጀምጀሚያው አዳራሽ የሚመጡት ሰውነቴን ላፍታታ በሚል ሰበብ የጂም ማሺኖች በጥንቃቄ መያዝ አለመያዛቸውን ለመሰለል ነው። “አልተቻሉም ጋሽማንበብ ይቀጥሉ…
የ deቫልዌሽኑ ጉዳይ
(ንፋስ አመጣሽ ንፋስ ወሰደሽ ) መጀመርያ ይቺን የድሮ ዜና ያዝልኝ [Jan 2011 – የ ብር ዲቫልዌሽንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ባንኮች በነፋስ አመጣሽ ታክስ 1.5 ቢልየን ብር ለመንግስት ከፈሉ።] ሀገሪቷ ያደረገችውን የትላንቱን የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ ተከትሎ ብዙ ብሶቶች ጭንቀቶች ና እስተያየቶች እያየሁማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል አምስት)
(እውነተኛ ታሪክ) ያ የኦነግ ወታደር አስደንግጦኝ “ወደቤት” ስገባ ትቶኝ የነበረው ፍርሃት እንደገና ተቀሰቀሰብኝ። ልቤም እንደ ቃልቻ ድቤ “ድው ድው.. ድው… ድው….” ማለት ጀመረ። “ምን ዓይነት ቀን ነው?” አልኩ ለራሴ። የአክስቴ ልጆችም እንደኔው ተሸብረዋል። “ወዴት መሄድ ይሻላል?” በማለት መነጋገር ስንጀምር “ሙበጀል”ማንበብ ይቀጥሉ…
የአፍሪካ የቁም ቅዠት
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል አራት)
(እውነተኛ ታሪክ) ረቡዕ ሰኔ 17/1984…. ከጧቱ 12፡30 ገደማ አክስቴ ከሁላችንም ቀድማ ነው ከእንቅልፏ የተነሳችው። እኔና ልጆቿ ከመኝታችን በመነሳት ላይ በነበርንበት ጊዜ ደግሞ እርሷ ወደ ሰፈር ሄዳ ወሬ ቃርማ መመለሷ ነው። “ምን ተፈጠረ?” አልናት። “ኢህአዴጎች ሳይጠበቁ በኦነግ ጦር ላይ ጥቃት ከፍተዋል?”ማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል ሶስት)
(እውነተኛ ታሪክ) ያ የኦነግ ወታደራዊ አዛዥ ከእግር እስከ ራሴ ከገረመመኝ በኋላ ወደ “አይካ” እና ዘኮ በመዞር “ይህ ልጅ ከናንተ ጋር ነው የመጣው?” በማለት በኦሮምኛ ጠየቃቸው። እነርሱም “አዎን!” አሉት። ከዚያም ወደኔ ዞሮ “የድርጅታችን አባል ነህ?” አለኝ። እንዳልሆንኩ ነገርኩት። “ታዲያ ለምን ወደዚህማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል ሁለት)
(እውነተኛ ታሪክ) ቀደም ባለው ጽሑፌ እንደገለጽኩት ኦነግና ኢህአዴግ ባደረጉት ስምምነት መነሻነት በኢህአዴግ ስር ያለው የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ-OPDO) በአካባቢያችን በሚኖረው ህዝብ ውስጥ ተሰማርቶ የፖለቲካ ስራ እንዲሰራ ተፈቅዶለት ነበር። በዚህም መሰረት የተወሰኑ የኦህዴድ ወታደሮች በሀብሮ አውራጃ ማረሚያ ቤት (ከርቸሌ) እንዲሰፍሩማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (እውነተኛ ታሪክ)
ዛሬ የማወጋችሁ ታሪክ ከመጽሐፍ የተገኘ አይደለም። በሬድዮ ጣቢያም አልተላለፈም። በቴሌቪዥን ፕሮግራምም አልቀረበም። በኢትኖግራፊ ጥናት (ethnographic research) ሰበብ በየከተማውና በየመንደሩ እየዞርኩ ከሰበሰብኩት ዳታ የተወሰደም አይደለም። በዐይኔ ያየሁትንና በራሴ ላይ የደረሰውን ነው እንደወረደ የማጫውታችሁ። ይህንን ታሪክ የማወጋበት በርካታ ምክንያቶች አሉኝ። በመጀመሪያ በህይወቴማንበብ ይቀጥሉ…
የ 500 ሺህ ዶላሩ ጉዳይ
በቅርቡ ከ አዲስ አበባ ወደ ጠረፍ ሲጔጔዝ የነበረ 500 ሺህ ዶላር ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መያዙን ተከትሎ…… ለፀረ ሰላም ጉዳይ ከጃዋር የተላከ ነው ፣ አይ ለቡጡቡጥ ከህወሀት ለአብዲ ኢሌ የተላከ ነው እያሉ አንዳንዶች ሲያደነቁሩን ነበር። ከዛም አልፎ ይህንኑ አጋጣሚ ከ ኢህአዴግማንበብ ይቀጥሉ…
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናትን በጨረፍታ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ሲጠቀሱ በቅድሚያ የሚታወሱት በላስታ አውራጃ፣ በ“ሮሃ” (ላሊበላ) ከተማ አጠገብ ከአንድ-ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩት አስራ አንድ ቤተ ክርስቲያናት ናቸው። የአስራ አንዱ ቤተ ክርስቲያናት ስም እንደሚከተለው ነው። 1. ቤተ መድኃኒ-ዓለም 2. ቤተ ማርያም 3. ቤተ ደናግል 4.ማንበብ ይቀጥሉ…
እስልምና፣ ጂሐድ እና ጽንፈኝነት
ኢራቅ በሳዳም ሁሴን አገዛዝ ስር በነበረችበት ዘመን ከሞላ ጎደል ሰላምና መረጋጋት ነበራት። ሀገራዊ አንድነቷም የተጠበቀ ነው። አሜሪካ አንድም ማስረጃ ባልነበረው ወሬ ተነሳስታ በ2003 (እ.ኤ.አ) ሀገሪቷን ከወረረቻት በኋላ ግን አንድነቷም ሆነ ሰላሟ ተናግቷል። በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች ላይ የከተመችው ውቢቷ ባግዳድም በየዕለቱማንበብ ይቀጥሉ…
ኢራን፣ ሩሚ እና መስነቪ
አዎን! ዛሬ በወግ ሽርሽር ብዙ ሀገር አቋርጠን “ፋርስ” ገብተናል። የዑመር ኻያም ሀገር! የፊርደውሲ ሀገር! የኒዛሚ ሀገር! የጃሚ ሀገር! የሓፊዝ ሀገር! በሩባኢያትና በገዛላት ዓለምን እያስፈነደቁ ለብዙ ክፍለ ዘመናት የዘለቁ የቅኔ ጠቢባን የተገኙባት ምድር! ዛሬ ፐርሺያ ነን! ዛሬ ኢራን ነን። ዛሬ ቴህራንማንበብ ይቀጥሉ…
ሳንሱራም!
ሳንሱራሞችን አትከልክሏቸው፣ ብትከለክሏቸውም አይከለኩልም የሚል ያልተከተበ ህግ አለ መሰለኝ።ሰዉ ሳንሱራም ነው። ያንተ ሃሳብ በገዛ ሞዱ ልክክ ብሎ ካልገጠመለት፣ ይጎመዝዘዋል። ሊያጣጥለው ላይ ታች ይወርዳል። አይዞህ ብቻህን አይደለህም፤የብዙዎቻችን ችግር ነው። የገዛ ሃሳብን እያሽሞኖሞኑ፣ የገዛ ልጅ ነው ብለው ከነንፍጡ የሚወዱ ሰዎች የሌሎች ለየትማንበብ ይቀጥሉ…
አስደሳች ጨዋታዎች
.(ከተስፋዬ ገብረአብ ) ተስፋዬ ገብረ-አብ “በጋዜጠኛው ማስታወሻ” በርካታ ፖለቲካ-ነክ ወጎችን አውግቶናል። እኔ እዚህ የምጽፍላችሁ ግን ፖለቲካውን ሳይሆን ተደጋግመው ቢነገሩ የማይሰለቹ ሌሎች ጨዋታዎቹን ነው። (እኒህን ጨዋታዎች የቀዳሁት ከዚያው መጽሐፍ ነው)። ===አቶ ፍሬው ለምለም እና የቼክ እደላው=== አቶ ፍሬው ለምለም ደግ አዛውንትማንበብ ይቀጥሉ…
የቀይ ኮከብ ዘመቻ
የኤርትራ አማጺያንን ለማጥፋት ከተደረጉ ዘመቻዎች መካከል ብዙ የተባለለት ነው- የቀይ ኮከብ ዘመቻ። ታዋቂ የጦር ጠበብት እየደጋገሙ አውስተውታል። በጋዜጣና በሬድዮ ብዙ ተለፍፎለታል። አጀማመሩም ሆነ አፈጻጸሙ ትንግርተኛ መሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ዘመቻው የተካሄደበት ለየት ያለ ድባብና በርሱ ሳቢያ የተፈጠረውማንበብ ይቀጥሉ…
የአፋቤት ጦርነት
መጋቢት 17/1988 (መጋቢት 9/ 1980) እኩለ ሌሊት። በዚያች ደረቅ ሌሊት ሕዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ (ሻዕቢያ) ሳይጠበቅ የናደውን እዝ ወረረ። የህዝባዊት ኢትዮጵያ አብዮታዊ ሰራዊትም ይዞታውን ለማስጠበቅ ተከላከለ። ይሁንና በለስ ሊቀናው አልቻለም። ሻዕቢያ ቀደም ብሎ ያገኘውን መረጃ በሚገባ ሊጠቀምበት ስለቻለ የአብዮታዊ ሰራዊትንማንበብ ይቀጥሉ…
“እኔ ምን ሀብት አለኝ!? ሀብቴ የኢትዮጲያ ህዝብ ነው!”
“እኔ ምን ሀብት አለኝ!? ሀብቴ የኢትዮጲያ ህዝብ ነው!” የሚሎውን ኒጊጊር ከራዲዮ ዲንገት ስሰማ ተናጋሪዋ ያው አስቴር አወቀ ወይም አንዷ ቺስታ አርቲስት መስላኝ ነበር….ጪራሽ አንቺ ናሽ! ኢሱን ሲትገረፊ ታወጪዋለሽ! ….ዲምጹን ጨምሬ በጉጉት መስማት ቀጠልኳ….ያለሚኒም ሃፍረት አይኗንን ፊጢጥ አድርጋ ጀለሴ ቤሳቤስቲን የለኝምማንበብ ይቀጥሉ…
ጅምጃሚዎች
(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ላሎ ወደ መርሀባ ተጠጋና ምንጣፉ ላይ በጀርባዋ አንጋለላት። ከዚያ በእግሮቿ ማሃል በርከክ አለና ቁልቁል ተመለከታት። ፊቷ በላብ ተጠምቋል!! ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። እግሯን ብድግ አድርጎ ወደ ደረቱ ሳበው። አንባቢ ሆይ! የወሲብ ታሪክ የምተርክልህ መስሎህ እግርህን በእግርህ ላይማንበብ ይቀጥሉ…
ላንችይቱ
[Come out of the circle of time and into the circle of love. ~ Rumi] ~ ምንኛ ነው ግን… ‘የነገን ማወቅ ፈለግሁኝ’ ብሎ ምኞት… ዛሬ ላይ ሳይቆሙ ወደ ነግ መጎተት… የሚያውቁትን ጥለው በማያውቁት መሳብ… ምንኛ ነው ‘ነገን ላየው እጓጓለሁ’ ማለት…ማንበብ ይቀጥሉ…
አቶ ሀዲስ አለማየሁ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች
አቶ ሀዲስ አለማየሁ በልቦለድ ፀሀፊነታቸው የተጋረደ የፖለቲካ ሰብእና ነበራቸው። በተለያየ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች እንደ ደረቅ ትንቢት የሚቆጠሩ ነበሩ። ለዛሬ: መጋቢት 19: 1985 አመተ ምህረት ባዲሳባ ዩንቨርሲቲ ካቀረቡት ንግግር የሚከተለውን ለመቀንጨብ ወደድሁ። በጥሞና አንብበን በሰከነ መንፈስ እንወያይበት። የንግግሩማንበብ ይቀጥሉ…
ምንሽን
የሰው አገር ሙጥኝ ብየ-በወጣሁበት እንዳልቀር ሀገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ -ግና ምንድር ነው ማፍቀር? እንዳስመሳይ አዝማሪ -ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስተዛሬ ከጣትሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መች ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላ ስለቅምማንበብ ይቀጥሉ…
የቀበሌ 01 የመጨረሻዋ ድንግል እንደምን አረገዘች!?
(በመጀመሪያ ከላይ የተጠቀሰውን ርእስ ከሁለት ታላላቅ ደራሲዎች የተዋስኩት እንደሆነ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።”የቀበሌ 01 የመጨረሻዋ ድንግል” የሚለውን ሀረግ ከአዳም ረታ መጽሃፍ የተዋስኩት ሲሆን “እንደምን” የሚለውን ቃል ደግሞ “ጃፓን እንደምን ሰለጠነች?” ከሚለው የከበደ ሚካኤል መጽሃፍ የወሰድኩት ነው።”አረገዘች” የሚለው ቃል እና የጥያቄ ምልክቱ(?) ግንማንበብ ይቀጥሉ…
እንቁጣጣሽ
ራሴው ማበዴ ነው (የመጨረሻ ክፍል)
[አልነገርኩትም። የማላውቀው ሰው የሆስፒታሉ መግቢያ በርጋ ጠብቆኝ የትዝታን ጉዳይ ማነፍነፍ ካላቆምኩ ከምወዳቸው ሰዎች አንዳቸውን እንደማጣ እንዳስጠነቀቀኝ አልነገርኩትም። ብዙ ነገር አልነገርኩትም። እንዲያውም ምንም አልነገርኩትም። እማዬ ከዚህ በኋላ ህክምና የሚፈይድላት ነገር ስለሌለ ወደቤቷ ወስደናት ዓይን ዓይኗን እያየሁ የምትሞትበትን ቀን መጠበቅ ትኩስ ቁስልማንበብ ይቀጥሉ…
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል አሥር)
የገዛ ሚስትህ በአደባባይ አብረሃት እየሄድክ ጡቶቿን የከለላቸውን ጨርቆች ገፋ ሳምልኝ ብትልህ ብልግና ይሆንብሃል። በሷ ድርጊት አንተ ትሸማቀቃለህ። መኝታ ቤታችሁ ውስጥ ራቁቷን ሆና ያንኑ ነገር ብትልህ ለቦታው የሚገባ ቅድስና አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ። ምናልባትም ከዛ በላይ ‘ስድ’ ብትሆንልህ ያምርሃል። በመንፈሳዊው ዓለም የመጀመሪያውማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ዘጠኝ )
“አገኘሁት! ራሁ አገኘሁት!” ይለኛል የሆስፒታሉ ኮሪደር መሃል እየደነሰ “ምኑን? እስኪ አንዴ ዳንስህን አቁመህ ንገረኝ!” “የትዝታን ፍቅረኛ አገኘሁት!” “በጣም ጥሩ! የሚጠቅም መረጃ አገኘህ?” “ገና ነው። ደቡብ አፍሪካ ነው ያለው። ከሀገር እንዲወጣ ያደረገው ማን እንደሆን ገምቺ? የትዝታ አጎት! አስፈራርተውት ነው ከሀገር እንዲወጣማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ስምንት)
በሰላሳ አንድ ዓመቴ ማንም ወንድ ነክቷት የማታውቅ ድንግል ሴት መሆን የሚያኮራ ነገር ይሁን የሚያሳፍር አላውቅም። (‘ድንግል’ የሚለውን ቃል እጠላዋለሁ። ቃሉን እንጂ ነገርየውን አይደለም። በእርግጥ ነገርየውንም ልውደደው ልጥላው እርግጠኛ አይደለሁም። ቃሉ ግን የሆነ አፍ ላይ ሲባል ራሱ ድንግል፣ ደናግል፣ ድንጉላ……… ድንዝናማንበብ ይቀጥሉ…
ድልድዮቹን ተውልን
እመሃል ላይ ተገምሰው ማዶ ለማዶ የሚያተያዩን ሰባራ ድልድዮች እየበዙ ነው… አንዳንዶቹን ሆን ብለን ሰብረናቸዋል… አንዳንዶቹ በሌሎች ሰንኮፎቻችን ዳፋ ተሰብረዋል… ሌሎቹን ግን መሰበራቸውን እንኳ አልተረዳንም… ~ አንዳንዶች የሚሰብሩትን ድልድይ ፋይዳ በወቅት ስሜታቸው ትኩሳት ውስጥ ብቻ ስለሚመዝኑ የሰባሪነት ወኔ እንጂ የአስተዋይነት ስክነትማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሰባት)
“ይሄ ኬዝ እንዲህ ቀልብሽን የሳበው የትኛው ነጥብ ነው? ግልፅ ማስረጃ ነው የተያዘባት። ራሷም ድርጊቱን መፈፀሟን አምናለች።” “ፍትህ ሰዎቹን ፈራሃቸው እንዴ?” “በፍፁም ፈርቼ አይደለም። ከእነሱ ጋር ስለመያያዙም ገና መላምት ነው ያለሽ።” ከፍትህ ጋር ሻይ እየጠጣን እየተነጋገርን ያለነው ስለትዝታ ነው። ትዝታ የ23ማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ስድስት)
እናቴ ከመሞቷ በፊት ልውልላት የምችለው አንድ ውለታ አባቴ እንዲያገኛት ማድረግ ነው። ቢያንስ የዘመናት ፍቅሯን እጁን ዳብሳ ደስተኛ ሆና ትሞታለች። እናቴን ማጣት ማሰብ አልፈልግም። የባሰው ደግሞ ስትለየኝ ማን መሆኔን እንኳን ሳታውቅ እብደቷ ተነስቶባት መሆኑን ማሰብ ያሳብደኛል። ያ እንዲሆን አልፈልግም። የቀራትን ጊዜማንበብ ይቀጥሉ…
ጥቂት ስለ “አዳል”
በመካከለኛው የታሪክ ዘመን (Medieval Era) ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን፣ ጅቡቲን፣ ሶማሊላንድን እና ሶማሊያን በሚያቅፈው የአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና የተለያየ ቅርጽና አወቃቀር የነበራቸው መንግሥታት ተመሥርተዋል። ከነዚያ መንግሥታት መካከል ከአስር የማያንሱት የሙስሊም ሱልጣኔቶች ነበሩ። ከሱልጣኔቶቹ መካከል ስሙ በጣም ገንኖ የነበረውና በአፍሪቃ ቀንድ ሕዝቦች ታሪክ፣ ጂኦ-ፖለቲካማንበብ ይቀጥሉ…
Nothingness!!
መስመር መስራት ስትጀምር ወዲህና ወዲያን ትፈጥራለህ… አጥር መገንባት ስትጀምር ውስጥና ውጭ ትፈጥራለህ… ፍርድ መስጠት ስትጀምር ክፉና ደግ ትፈጥራለህ… በመስመር – አጥርና ፍርድህ ምክንያት የልዩነት ዜማ ሰርክ ይቀነቀናል… እንዲህ ‘የሆኑ’ እና እንዲያ ‘ያልሆኑ’ ክልል ይበጃል… ‘የኛ’ እና ‘የእነርሱ’ ምድብ ይሰራል። ሕይወትማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል አምስት)
“ራሔል ከዚህ በላይ እናትሽን እቤት ልታቆያቸው የምትችዪ አይመስለኝም። አደገኛ ነው የሚሆነው።” “ዶክተር በፍፁም ሆስፒታል እንደማልተዋት ቃል ገብቼላታለሁ። አይሆንም!! ታውቅ የለ ምን ያህል እንደምትጠላ?” “ራሔል እስቲ ተቀመጪ።” አለኝ ወንበሩን እያሳየኝ። በእማዬ ምክንያት ከማውቀው ልምድ በዶክተሮች አባባል ‘እስኪ አረፍ በይ፣ እስኪ ተቀመጪ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
እኛ፣ሾፌሩና አውቶብሱ
‹ዛጎል› ልቦለድ ውስጥ የምናገኘው ዮናስ የተባለው ገጸ ባሕርይ እንደሚከተለው ያስባል፤ያምናል፤ይናገራልም! ‘በእኛ ፈቃድ አይደለም ነገሮች የሚከወኑት። እግዜራችን ነው ሾፌር። እሱ ነው ፈላጭ ቆራጭ! እሱ ነው የእኛ ሃይል። በየትኛው ጊዜ – በየትኛው ቦታ – እኛን ከመኪናው ማውረድ እንዳለበት የሚወስን። እኛ ‘ወራጅ አለ’ማንበብ ይቀጥሉ…
ልጅነቴን አፋልጉኝ
ማደግ በመሰለኝ ረግረግ ውስጥ የጠፋች ልጅነቴን አፋልጉኝ – ማወቅ በመሰለኝ ጥልቅ ውስጥ የተደበቀች ልጅነቴን አፋልጉኝ – ከድቅድቅ ጽልመት ውስጥ የዘነጋሁዋትን እውነት አፋልጉኝ… ~ ዕድሜ የሥጋ ኑረት መስፈሪያ እንጂ የውዷ ሕይወት መግለጫ አይደለም… ሕይወቴ ልጅነቴ ነው… ዕድሜ ደግሞ የልጅነቴን ንጽሕና የነጠቀኝማንበብ ይቀጥሉ…
“ሁ ኢዝ ባድ?!”
ይህቺ ጭዌ ከዚህ ቀደም ተፖስታ የነበረ ሲሆን ሰሞኑን ከሚከበረው የአጼ ሚኒሊክ ልደትና የጠ/ሚ መለስ ሙት አመት አንጻር ለሁለቱም ቀደምት መሪዎች ወዳጅም ሆነ ጠላት ሚዛናዊ ነው በሚል በአድማጭ ጥያቄ በድጋሚ የቀረበች ነች።ጽሁፉ ትንሽ ረዘም ይላል ያው የምታነቡት ካጣችሁ ብቻ ተደበሩበት። መቼቱማንበብ ይቀጥሉ…
ቡሄ ከኃይማኖትና ትውፊት አንጻር
ጠፍታ አገኘችኝ
የደመናው ጽልማሞት በዝናብ ፍርሃትና በቀጠሮ አለማክበር ስጋት መሃል አዕምሮዬን እያላጋብኝ ወደ ታክሲ መያዣው የማደርገውን ግስጋሴ ትቼ ቅርቤ ወዳለ ካፌ ዘለቅሁ… ፒያሳ ነኝ… ከመቀመጤ ሸገር እሪ ብላ አነባች… በጣም ከባድ ዝናብ መውረድ ጀመረ… “ሸበሌ እንገናኝ” ነበር ያለችኝ… ፍቅረኛዬ ናት… ‘ጥብቅ ጉዳይ’ማንበብ ይቀጥሉ…
የአርሲ ዐጃኢባት
እኛ (እደግመዋለሁ “እኛ”፣ “ኑቲ”፣ “ናህኑ”) የኢትኖግራፊ ፈረሳችንን ተሳፍረን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከመሀል እስከ ሰሜን መጋለብ ሱስ የሆነብን ጸሐፊ ከሀረር መሆናችንን ታውቃላችሁ አይደል? ታዲያ እኛ (አሁንም እደግመዋለሁ “እኛ”) ወደ ሌሎቹ ስፍራዎች ስንጋልብ የነበረው ከሌሎች አካባቢዎች ሁሉ የሚቀርበንን አንድ ጎረቤታችንን እያለፍን ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…