በግንቦት 20 ዋዜማ ዋልታ ቴሌቪዥንን እያየሁ ነው። ጋዜጠኛው ዝግጅቱን ከአመት አመት በማይቀየሩት መፈክሮች( ለምሳሌ “ግንቦት 20 የህዝቦች ሁሉ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ቀን ነው) ጀመረና፣ ዛሬም በጭንቅላቴ ውስጥ የሚፈነጩትን ጥያቄዎች ዘርዝሬ ለማሰብ እንኳን እድል ሳይሰጠኝ፣ “ከግንቦት 20 ወዲህ የተወለዱ ልጆችማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ገዳዬ…ገዳዬ…››
(መነሻ ሃሳብ፤ የሞፋሳ (ኬንያዊ ገጣሚ) ‹‹ልጅቷ›› ግጥም) ፀሐያቸው ጠልቃ በሰው ሀገር መሽቶብኝ ነበር። ጨልሟል። የተለመደውን አውቶብሴን ተሳፈርኩ። አዲስ ነገር የለውም። ሁሌም የምጠብቀው፣ ሁሌም በጠበቅኩት ሰአት የሚመጣው የማይዛነፍ የእለት ውሎዬን የሚደመድመው አውቶብስ ነው። እንደተቀመጥኩ፣ ሰንደቅ የሚያሰቅል ቁመት ያለው ውብም፣ ሎጋም ኢትዮጵያዊማንበብ ይቀጥሉ…
እንግዶቹ
“… ዓይን ወረተኛ ነው ያመጣል እንግዳ’’ የሚል ስንኝ ያለበት የባላገር ዘፈን አውቃለሁ፤ በርግጥ ዘፈኑ እንደሚነግረን ዓይን ብቻ አይደለም አዲስ ለምዶ እንግዳ ይዞ የሚመጣው፤ ጆሮም፣ ልብም፣ እጅም፣ እግርም መጠናቸው ይለያይ እንደሆነ ነው እንጂ፣ ከአዲስ ነገር ጋር አስተዋውቀውንና አላምደውን እንግዳ ይዘውብን ይመጣሉ።ማንበብ ይቀጥሉ…
ሌ/ጄነራል ጃገማ ኬሎ
ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
(ትራጄዲ ትረካ) ሰሞኑን የወንድሙ ጂራን ዘፈን የምገርበው ያለ ምክንያት አይደለም። ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ካልሲየን ፍለጋ በየጥጉ እሰማራለሁ። የቀኝ ካልሲየ ምስኪን ናት። እንደ ገራም የድመት ግልገል ከመመገቢያው ጠረጴዛ እግር ስር ኩርትም ብላ ትገኛለች። የግራ ካልሲየን ግን እፀ -መሰውር የረገጥሁባት ይመስል ደብዛዋማንበብ ይቀጥሉ…
ጋሹ እንዴት እንደተሰደደ?
የዚች ጨዋታ መነሻ የሆነኝ የዛሬ ምናምን አመት ያነብኩት “ያረብ ሌሊቶች ” ተረት ነው። ጋሹ ታታሪና አይናፋር ባላገር ነው። ሲኖር ሲኖር; በስንት መከራ አንዲት ቆንጆ አጭቶ አገባ። የሰርጉ ቀን ተበልቶ ተጠጥቶ ጭፈራው ደራ። ሚዜዎችና አጃቢዎች ሙሽሮች እንዲጨፍሩ ጋበዙዋቸው። ጋሹ ግብዣውንማንበብ ይቀጥሉ…
ራስ አሉላ አባ ነጋ – የኢትዮጵያ ጀግና!!
በዘመነ አብዮቱ (ደርግ) በትግራይ ክፍለ ሀገር ፣ ዓድዋ አውራጃ ፣ አባ ገሪማ ገዳም ከወትሮው የዝምታ እና የመናንያት የተመስጦ ቀናት ውጪ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብና የጦር ሰራዊት ገዳሙ ተርመስምሷል። የገዳሙ መናንያንም በከፍተኛ የድግስ ዝግጅት ተጠምደዋል። በቦታው በአካል ከነበሩ ሰዎች መሀል የልጅነትማንበብ ይቀጥሉ…
ኢትዮጵያ በአማልክት እና በተከታዮቻቸው ዓይን
“… እናቴ ሆይ በዚህች በምባርካት አገር በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሰዎችን እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ አሥራት ይሆኑሽ ዘንድ ሰጥቼሻለሁ። እናቴ ሆይ አሁንም ወደዚያች አገር እንሄድ ዘንድ ተነሺ። ደሴቶችና የተቀደሱ፣ ወንዞችዋ ያማሩ፣ ውሃዎችዋ የጠሩ፣ ዛፎችዋና ተራራዎችዋ የተዋቡ ናቸውና አሳይሻለሁ አለኝ።” ይላል አንብር መስቀልየማንበብ ይቀጥሉ…
እርዳታ እና እኔ
ግኑኝነታችን የሚጀምረው፣ በልጅነቴ ከበላሁት የእርዳታ “ፋፋ” እና “ዘይት” ነው። የሆነ ጊዜ ወተትም ነበር። የሆድ በሽታ ለቀቀብኝና ለሳምንታት ላይና ታይ በሌ ስል ኖሬ ይቺን ዓለም በጨቅላነት ሳልገላገላት ለትንሽ አመለጥኩ። ኑሮን በድህነት ስትገፋ በወር የሚሰጥህ 5 እና 10 ኪሎግራም ምጽወታ ነፍስህን ለማቆየትማንበብ ይቀጥሉ…
እትት በረደኝ
“ጅላዋት ሆይ፣ ጮማ ክፋት ከመጣ ሰላሳ እግዜር፣ ሰላሳ አላህ አይመልሰውም።” “….በዲሞክራሲ ስለማምን አይደለም። ምንድን ነው እሱ? ልግመኛ ቢሰበሰብ የአንዲት ጮጮ ክዳን አይከፍትም። ፍትህ ፍትህ ፍትህ የምትባለዋም የነብር ቂንጥር ናት። በሥዕል ይህቺ ፍትህ የሚሏት ሴትዮ ቆማ አይቼአታለሁ፤ ሚዛንና ሰይፍ ይዛ። ሰይፉማንበብ ይቀጥሉ…
የጎረቤት ወግ
ወደቤቴ ከመግባቴ በፊት ከጨዋ ሚኒ ማርኬት ሁለት ኪሎ ማንጎ ገዛሁ፤ “በጥቁር ፌስታል አርጊልኝ” አልኩዋት ማሾን(ማሾ የሚኒ ማርኬቱ ባለቤት ናት) “አንተ ደሞ የጥቁር ፌስታል ልክፍት አለብህ “አለችኝ እየሳቀች። ውነቷን ነው! ከፍራፍሬው ጥራት በማይተናነስ መጠን የፌስታሉ ቀለም ያሳስበኛል፤ ጥቁር ፌስታል በውስጡማንበብ ይቀጥሉ…