ሰዎች ይመስሉኛል። በጎችም ይመስሉኛል። ሰዎች ብዬ ስጠራቸው አቤት ይላሉ። በጎች ብዬ ስጠራቸውም አቤት ይላሉ። ሰዎች ናቸው በጎች? በቡድን ነው የሚኖሩት። በቡድንን ይንቀሳቀሳሉ።እንደማንነታቸው ሁሉ አንዳቸውን ከአንዳቸው ለመለየት ከባድ ነው። ጠጋ ብዬ እረኛቸውን ጠየኩት። “አልገባኝም በጎች ናቸው ሰዎች? ” ፈገግ ብሎ መለሰልኝ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ስሚ!
ስሚ መስሚያ ካለሽ። ከሰማሽ ደሞ ተስማሚ፤ ወዲያ ሂጂልኝ እስቲ። ማነሽ እውነት ነኝ የምትይ፣ እስቲ ስሚን የስንቱን አለመስማት እንችላለን? መንግስት አይሰማን፣ ፈጣሪ አይሰማን፣ አንቺ አትሰሚን… ኸረ እስቲ አንቺ እንኳን?!! ማን ነበረ ስምሽ? “እውነት ” ነው አይደል? እውነቱን ልንገርሽ፣ በደረስኩበት ባትደርሺ ደስማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱ ካድሬዎቹ
ሁለቱ ካድሬዎች የማነ እና ዳንኤል ካድሬዎች ናቸው። ይሁኑዋ ታዲያ! ካድሬ በበዛበትሀገር እነገሌ ካድሬ ናቸው ማለት ምንድነው? የማነ እና ዳንኤል ጓደኛሞችም ናቸው፤ ውሏቸው አንድ ላይ ነው፣ ወሬያቸውም አንድ ዓይነት። ስለ ልማቱ ያወራሉ፣ ያደጉትም፣ ያላደጉትም ፣የማያድጉትም ከኢትዮጵያ መውሰድ ሰላለባቸው ተሞክሮ ያወራሉ፣ አዲስማንበብ ይቀጥሉ…
የዚህ ትውልድ አባል ነኝ!
በመውደድ ወይ በመጥላት አልፍቀውም። ያለፈው ትውልድ ውላጅ ነኝ። የመጪው ትውልድ ወላጅ ነኝ። ያለፈው ትውልድ “አዬ ልጅ” እያለ ያሾፍብኛል፤ መጪው ትውልድ ይኮርጅኛል( ወደፊት “አይ አባት” ብሎ ይስቅብኝ ይሆናል -ግድ አይሰጠኝም) ለሁሉ ፈጣን ነኝ። ሁሉን በፍጥነት አይቼ በፍጥነት አልፋለሁ። ችክ ማለት አልወድም።ማንበብ ይቀጥሉ…
መረቅ
(ስሜቴን ለመግለፅ እንጂ፣ እንዳይንዛዛ( እንዳልንዛዛ) ሁለት ወይ ሶስት ጊዜ ቆራርጬ ለመፖሰት እገደዳለሁ) ክብነት(ሙሉዕነት) በመረቅ የመፅሓፉ ሀይለኛ ጉልበት እዚህ ጋር አለ።አዳም የህይወትን ክብነት ለማሳየት ገፀባህሪያቱንና ታሪክን በመጠቀም እንጀራውን ይጋግራል። ሀ. በገፀባህሪቱ፡― መፅሐፉ አራት ዋና ገፀባህሪያት አሉት።አራት(ምናልባትም “ዐራት”) የምልዑነት መገለጫ ነው። በማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት እህትማማቾች ወግ
የዛሬ ወር ተኩል ገደማ ለሳምንታት ቆይታ ወደ አሜሪካ ሄጄ ነበር፡፡ የጉዞ ሃሳቤን የሰሙ እዚህም አዚያም ያሉ ዘመድና ወዳጆቼ እኔ ‹‹ልዋጭ ልዋጭ›› የምለውን የእቃ ውሰጂና አምጪልን ጥያቄያቸውን ጀመሩ፡፡ በርበሬና ሽሮን በጋላክሲ ስልክና በሌቫይስ ጅንስ የመለወጥ ጥያቄ፡፡ ቡላና ኮሰረትን በናይኪ ስኒከርና በሬይባንማንበብ ይቀጥሉ…
በመጨረሻም…
በመጨረሻም ራሴን ላጠፋ ነው። ቃሉ ራሱ ደስ ሲል! ራስን ማጥፋት!! ፓለቲከኞች “የራስን ዕድል በራስ መወሰን ” እንደሚሉት ነው። ከህይወት ምን ቀረኝ? ምንም! አንድ የቀረኝ ነገር ራሴን የማጥፋት ድርጊት ብቻ ነው። ከዛ በኋላ ሀገሬ ሞት ነው። ከሞት ግድግዳ ወዲህ ምንም የሚጎትተኝማንበብ ይቀጥሉ…
ላንቺ ግጥም እየፃፍኩ ነበር!
የሆነ የዓለም ጥግ ላይ ህፃናት በረሃብ ሲያልቁ እኔ ላንቺ ግጥም እየፃፍኩ ነበር። ሁሉም ሲያድጉ አንቺን ማግኘት እንደማይችሉ ስለገባችው እንደሚያለቅሱ ይሰማኝ ነበር። እንደዚህ እያሰብኩ ግጥም እየፃፍኩልሽ ነበር። ፈጣሪ ዓለም የሚያጠፋት በቁጣ ነው ሲሉኝ እገረማለሁ። ፈጣሪ ዓለምን ካጠፋ አንቺ ስትሞቺ በሚደርስበት ሀዘንማንበብ ይቀጥሉ…
ይሰለቻል
በመጀመሪያ እግዜር ብቻውን ነበር። ብቸኝ ት ሰለቸው። ብቸኝነት ሰለቸውና ዓለምን ፈጠረ። የፈጠረውን አይቶ ደስ አላለውም፣ ሰለቸው እንጂ። የሰለቸውን ዓለም ትቶ ሌላ አዲስ ነገር ፍለጋ ሄደ። ዓለምም ከዛን ወዲህ መሰልቸት ወለል ላይ ሆና የአምላኳን መምጣት በጥፍሯ ቆማ ትጠብቃለች። እኔ የዓለም አካልማንበብ ይቀጥሉ…
ባትሄጂ ኖሮ…!
ባትሄጂ ኖሮ፣ ብትሆኝ ከኔ እቅፍ እዚህ ከፃፍኩት ላይ፣አንድም መስመር አልፅፍ፡፡ አቤት ባትሄጂ! ግን አንቺ አልቆምሽም መጓዝ አልደከምሽም፡፡ ይሄዋ፡- ከሄድሽ በኋላ ዐይኔም አይታየው፣ ጆሮዬም አይሰማ ልቤም ደም የሚረጭ፣ ባንቺ ስለደማ፡፡ አንቺ በመሄድሽ፤ ያለህይወት በህይወት ተነጥላኝ ነብሴ፣ ያው አለሁ ሙት ሆኜ፣ ለሰዉምማንበብ ይቀጥሉ…
ቤት ሰራሽ ጦርነት
በአንዲት ሀገር ላይ ጨለማና ብርሃን ክፉኛ ተጣሉ አሸናፊ እስኪለይ ድብድብ ቀጠሉ የጨለማን ግንባር-አናቱን ሊበሳ ብርሃን ይጥራል የጨረራ መዓት ጨለማን ለመምታት ተግቶ ይወረውራል እውሩ ጨለማ መርግ መርግ ፅልመት ከአካሉ ያነሳል ድቅድቅ አሰልፎ ብርሃን ላይ ያፈሳል ተው ባይ በሌለበት ሃይ ባይ በጠፋበትማንበብ ይቀጥሉ…
የተደገሙ ወላጆች!
(ልጆቻችሁ፣ ልጆቻችሁ አይደሉም?) ካህሊል ጅብራን “The Prophet” በተባለ ስራው “ስለ ልጆች ንገረን” ለሚል ጥያቄ በነብዩ አንደበት ይናገራል። “your children are not your children” ምን? ልጆቻችሁ ልጆቻችሁ አይደሉም? እና የኛ ካልሆኑ የማን ናቸው? ነው ወላጆቻችን ናቸው? አትቀልዳ ካህሊል። እስቲ ትንሽ አብራራው።ማንበብ ይቀጥሉ…
ፈሪ ነኝ!
ፈሪ ነኝ! ሞዴል ፈርቶ አደር! ውሃ ውስጥ ሆኜ የሚያልበኝ። በርግጥ ውሃው “ፍል ውሃ” ከሆነ ማንም ሊያልበው ይችላል። እኔ ግን አጥንት በሚቆረጥም ውሃ ውስጥም ያልበኛል። መፅሀፉ፣ “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” ይላል። እኔ ግን “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ፣ መጨረሻውም ሁሉንም መፍራትማንበብ ይቀጥሉ…
ሆድ ሀበሻዊ ንጉስ…
የኛ ሰው ሆዱን በጣም በመውደዱ የሚወደውን ሰው እንክዋ ሲያቆላምጥ “ሆዴ” ብሎ ነው:: ግፋ ካለ “ማሬ” ቢል ነው:: ማርም የሚበላ ነው; ሆድም ምግብ ከታች ነው:: ምሳሌዎቹ እራሱ በሆድ ዙሪያ ድክ ድክ የሚሉ ናቸው:: -የወፍ ወንዱን የሰው ሆዱን አያውቁም! -ሆድ ያባውን ብቅልማንበብ ይቀጥሉ…
ድርብርብ ስቅላት
የመሲሁ ስቅየት ግርፊያ ስቅላቱ አምላክ ነኝ ስላለ በድምቀት ተሳለ የኛንስ ስቅላት ማነው ያስተዋለ? ተመልካች ጠፍቶ እንጂ ዐይን የሚለግሰን መውረድ እንደናፈቅን እኛም መስቀል ላይ ነን:: ዘውትር ዱላ እና አሳር ዘውትር ችንካር ሚስማር የሚገዘግዘን የሚጠዘጥዘን እኛም ክርስቶስ ነን እኔም ታዝቤያለሁ… ሺ ዱላማንበብ ይቀጥሉ…
ወጣትነቴን ያያችሁ
አላያችሁም አውቃለሁ! መጠየቅ፣ ልማድ ሆኖብኝ፣ ቁጭቴ ብሶት ጭኖብኝ የሄደች ወጣትነቴን፣ ያያችሁ…ያያችሁ እያልኩ፣ ባታዩም እጠይቃለሁ፡፡ * * * * ያያችሁ ወጣትነቴን? አፍለኛ፣ ማራኪ ወቅቴን? በጫት ጉዝጓዝ አፍኜ፣ ከፍኜ የገደልኳትን በማይገባኝ የፈረንጅ አፍ፣ አደንቁሬ የጣልኳትን ወጣትነቴን ያያችሁ፣ ሳልጨብጥ ያበረርኳትን፡፡ * * *ማንበብ ይቀጥሉ…
ጨዋታው ፈረሰ ዳቦው…
ጨዋታው ፈረሰ ዳቦው ተቆረሰ የሚል ተረት ይዘን በባዶ ሆዳችን ጨዋታ ማፍረስ ነው-ትልቁ ትልማችን የዳቦ መቆረስ በጨዋታ መፍረስ ታጅቦ ከመጣ ደህና ሁን ጨዋታ-ከሀገራችን ውጣ! ሆዷን በመብሰክሰክ ለሞላች እቺ ሀገር ከጨዋታው ሳይሆን ዳቦው ነው ቁምነገር ይህንን በማመን… ስንት ዓይነት ጨዋታ ግብ እንደናፈቀማንበብ ይቀጥሉ…
ክፈት በለው በሩን…የጌታህን
ክፈት ጌታው ክፈት ደብድበን, ወጋግረን, ሰብረነው ሳንዘልቅ; ክፈት በለው በሩን- ክፈት በሩን ልቀቅ:: ሕዝቡን ዘግተውበት; ነስተውት ማለፊያ ንገረው ለጌታህ እዚህ ያለውን ግፊያ! በክፋት ተገፍቶ የዘጋውን ሳንቃ ጥበቃችን ሳትመሽ ትዕግስታችን ጠልቃ ክፈት በለው በሩን, ክፈት በሩን ክፈት! ይህ ምስኪን ሕዝባችን; ልቡንማንበብ ይቀጥሉ…
ልጅነቴ…. ልጅነቴ ዱላና ብሶቴ
(ፓለቲካ ልጅነቴ ውስጥ ስትዞር አገኘኋት) ከመረገዜ በፊት እናትና አባቴ የባልና ሚስት ሙያቸውን እየሰሩ ሳለ አባቴ እናቴን፤ “እስቲ አንድ ስንወጣ ስንገባ ሰፈሩም እኛም የምንደበድበው ልጅ እንውለድ…?” ያላት ይመስለኛል። እናቴም ከአፉ ቀበል አድርጋ፤ “በአንድ አፍ! እኔም እኮ አንዳንዴ ቤቱ በአስፈሪ ፀጥታ ሲዋጥማንበብ ይቀጥሉ…
አማርኛ እንዳበጁሽ አትበጂም
“ ያስለቅሳል እንጂ ይህስ አያሳቅም ግንድ ተደግፎ ዝንጀሮ ጫት ሲቅም” (አማርኛ እንዳበጁሽ አትበጂም) እህህ…..ኡህህ…..ውይይ….. አማርኛ ተኝታ ታቃስታለች። የሀገር ውስጥ እና የዓለም ትልልቅ ቋንቋዎች በዙሪያዋ ተሰብስበዋል። ጥቂት የቋንቋ ምሁራንም አሉ። “ኡውይይ…. ኸረ አልቻልኩም፣ ቆረጣጥሞ ሊገለኝ ነው!” “ አይዞሽ…. አይዞሽ… እኛም እኮማንበብ ይቀጥሉ…
ዘመን ሆይ ማን ልበል?
ምን ዓይነት ዘመን ነው፣ የዘመን ጉንድሽድሽ ባንዳ እያከበረ፣ ጀግናን የሚያንቋሽሽ? ኸረ መን ዘመን ነው፣ የዘመን ቅራሪ ኮብል የሚያስጠርብ የጊዜያችን ዲግሪ ምን ዓይነት ዘመን ነው፣ የዘመን እግረኛ ስደት የሆነበት ብቸኛው መዳኛ ምን ዓይነት፣ ምን ዓይነት ምን ዓይነት ዘመን ነው፣ ዘመንን ለመስደብማንበብ ይቀጥሉ…
ታክሲው!
ታክሲው እየሄደ ነው። ወዴት እንደሚሄድ አናውቅም። ሾፌሩ ያውቀዋል ብለን እናምናለን። የኛ ስራ መሳፈር ነው። የሾፌሩ ደግሞ መንዳት። ሾፌሩ ይነዳል። እኛ እንነዳለን። መንገዱ ጭር ብሏል፣ ይህ ከታክሲዎች ሁሉ የዘገየው ሳይሆን አይቀርም። ከሾፌሮች ሁሉ ሰነፉ ጋር ተሳፍረን ሊሆን ይችላል። መንገዱ ገጭ ገጭማንበብ ይቀጥሉ…
በባህሩ እና “በባህር ዳር”መካከል…
በባህሩ እና “በባህር ዳር”መካከል… (የዘረኝነት መንቻካ ልብሶችን እናጥባለን!) ባህሩ ውስጥ ነኝ:: እልፍ ሰዎች ከባህሩ ወጥተው ዳር ላይ ተኮልኩለዋል:: ጥንት ዳሩ መሀል ነበር:: አሁን ዳሩ ወደ መሀል ገብቷል! ባህሩ ሰውነት ነው:: የባህሩ ዳር ዘረኝነት- የሰውነት ደረቅ መሬት! ባህሩ ውስጥ ነኝ:: ባህሩማንበብ ይቀጥሉ…
ምክንያት በጠና ታማለች
ምክንያት በጠና ታማለች:: ምን እንደነካት ማንም አያውቅም:: አሉባልታ ግን አለ:: እነ ባህል; ዕድር; ሃይማኖት…መርዘዋት ነው የሚሉ አሉ:: ፍልስፍናም ይህን አሉባልታ ሰምቷል:: ሳይንስ ናት የነገረችው:: ባሉባልታ አያምንም:: ባያምንም ሰምቷታል:: ሁሉም በምክንያት ዙሪያ ቁጭ ብለዋል:: ፍልስፍና ያዘነ ይመስላል- ፊቱ ስለማይነበብ በእርግጠኝነት መናገርማንበብ ይቀጥሉ…
ይወለዱና በፈረንጅኛ የሸበረቁ
ይወለዱና በፈረንጅኛ የሸበረቁ ከ”ኦ ማይ ጋድ” ውጭ ፀሎት አያዉቁ ይወለድና ምሁር የሚባል ባህር ተሻግሮ ታሪክ ያርማል ይወለድና ለዕለት አሳቢ ሆኖ ይቀራል ኪራይ ሰብሳቢ ይወለድና ኒዎሊበራሉ ጠረ-ልማት ነው ካገሩ ሁሉ ይወለድና እልፍ ሞዛዛ ግብር አይከፍል ወይ ቦንድ አይገዛ ይወለድና የEtv አይነቱማንበብ ይቀጥሉ…
አድዋ ለኤርትራውያን ምናቸው ነው?
አድዋ ለኤርትራውያን በደል ነው። ከቀሪው ኢትዮጵያ መቀያየሚያቸው ነው። የሀዘን ትዝታቸው ነው። ብዙዎቻችን ግን ይህን አምኖ ከመቀበል ይልቅ የምክንያት ጋጋታዎች ስናበጅ እንታያለን። ታሪክን በአርትኦት ልናርም? በምክንያት ልናቀና?…. ይቻለናልስ? እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የአድዋ ድል የሚያስደስተኝ፣ መንፈሴን የሚያግለኝ ቢሆንም፣ እንደ ግለሰብ የምኒሊክ የአመራር ጥበብማንበብ ይቀጥሉ…
የውጫሌ ስምምነት
ጣሊያንኛ የማይችለው፣ የውጫሌ ስምምነት ተርጎሚ!( የውጫሌ ስምምነት) እዚህ ጋር አንድ ስላቅ አለ። የውጫሌ ስምምነት ተርጓሚ የነበሩት( የተባሉት?) ግራዝማች ዮሴፍ ንጉሴ አማርኛ እና ፈረንሳኛ እንጂ ጣሊያንኛ አይችሉም ነበር። ታዲያ እንዴት ጣሊያንኟውን ተረጎሙት? የጣሊያንኛው ቅጂ በሮም ተዘጋጅቶ እንደመጣና ግራዝማች ዮሴፍም ለጣሊያኖች በብርማንበብ ይቀጥሉ…
ሄይይ…. ንቃ አንተ!
አንተ! ንቃት መሃል የተኛህ! ጩኸት መሃል የምትናውዝ! ቀውጢ መሃል የምታንኮራፋ ንቃ!! እዛ… በዘረኝነት ጠባብ አልጋ ላይ ተኝተህ የምትናውዝ ንቃ! እንደምን እንቅልፍ ወሰደህ ብለህ ስንደነቅ ደንገጥ እንኳን ሳትል እንክልፍህን መለጠጥ?? ኸረ ንቃ!! የመታከት አየር እየሳብክ፣ መታከት የምትተነፍስ አንተ ንቃ! አይንህን ግለጥ!ማንበብ ይቀጥሉ…
ራስ ወሌ ቡጡል
ራስ ወሌ ቡጡል ( ከደረስጌ እስከ አድዋ) እንግዲህ ስለ ወሌ ቡጡል ጥቂት ብናወራ ምን ይለናል። ድስ ይለናል ላሉ ቀጠልን… ለቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ ነው። እናቱ የውብዳር ይባላሉ። አባቱ ሰኔ 22/ 1845 ራስ አሊ ከቴዎድሮስ ጋር ባደረጉት የአይሻል ጦርነት ቆስለው ሞተዋል። ከአባቱማንበብ ይቀጥሉ…
ድንግልና ድንግል ነው?
ብር አምባር ሰበረልዎ ጀግናው ልጅዎ” ይባላል:: ጉድ እኮ ነው:: ስስ ስጋ የሰበረው የዓለምን ሪከርድ ከሰበረው እኩል ይዘፈንለታል:: ወንድ የጀግንነት እጩ; ሴቷ የጀግንነት ማሳያ መዋጮ አድርጎ ይነግረናል:: አሁን ድንግልና ለሴቷ ምኗ ነው? ለሰው ልጅ ምኑ ነው? ምን ይጨምርለታል ምን ያጎድልበታል? ምንማንበብ ይቀጥሉ…
አንድ ጨለምኛ ግጥም፣ ለአንዲት ጨለምተኛ ሀገር
*** አንቺ ሃሳበ ብዙ፣ አንቺ ጓዘ ብዙ አቅም የሚፈትን፣ጉልበት የሚያጣምን ከህይወት ዋጋ ይልቅ በሞት ከሚያሳምን ከዚህ ትግል ጉዞ የሚገላግሉ- ልጆችሽ እያሉ የት እንዲያደርስሽ ነው ሰርክ መባተሉ? “ሁሉ ነፃ አይደለም፣ ውደቁ ተነሱ ቆፍሩ አፈር ማሱ” የሚሉ ቂሎችን ከጆሮሽ አርቂ ለማይረባ ነገርማንበብ ይቀጥሉ…
ማነሽ ?!
ከእለታት በአንዱ፣ በቅዱስ እርጉም ቀን መንገድ ያገናኘን ድንገት የተያየን አንቺ አልፈሽኝ ስትሄጅ፣ እዛው ያስቀረሽኝ! …ላይሽን ሸፍኖት ጥቁር ጨለማ ጨርቅ ዐይንሽን ብቻ እንጂ፣ ሌላሽን የማላውቅ ማነሽ አንቺዬዋ? ማንነትሽ ማነው? አቅል እያሳተ፣ መንገድ የሚያስቀረው? ወንድን እንዳታስት ትጀቦን፣ ትሸፈን-ይሉትን የሰማሽ አይታይ አካልሽ ውዴማንበብ ይቀጥሉ…
“ከገዳይ ጋር ፍቅር”
አይጥ የድመቱ ነገር ግራ ገብቷታል። በተደጋጋሚ ፍቅሯን ልታሳየው ብትሞክርም ሊገባው አልቻለም። ከጉድጓዷ ስትወጣ አምራ እና ተኳኩላ ትወጣች። ድመቱ እንደ ሁል ጊዜ ከጉድጓዷ ፊት ለፊት ሆኖ ታገኘዋለች። አማላይ እንቅስቃሴ ልታሳየው ትሞክራለች። በፍቅር ዓይን ታየዋለች። እሱ ፍንክች የለም። እንዲህ መውደዷን ልታሳየው እየሞከረችም፣ማንበብ ይቀጥሉ…
የሕዝብ ችኩል ምን ይነክሳል?
…… ወሩን ሳስበው ፆም ነው፡፡ፆም ስለሆነ፣ አንድ ሆቴል ገብቼ ቅቅል በላሁ፡፡ …..ቅቅል የበላሁት ስላማረኝ ብቻ አይደለም የበላሁት፣ ፆም ስለሆነም ነው፡፡ ብዙዎች ከሚያደርጉት በተቃራኒ ማድረግ ደስ ስለሚለኝ ነው፡፡ ለነገሩ እውነቱን እናውራ ከተባለ፣ ቅቅል አልበላሁም፡፡ በዚህ ቅቅል ኑሮ፣ ቅቅል መብላት እራስን መቀቀልማንበብ ይቀጥሉ…
ማሞና ማሚቱ
<<ማሞና ማሚቱ በሉ ዳቦ ቆሎ ሮጡ ወደቁ ተነሱ በቶሎ>> /ቃላዊ ግጥም/ ማሞና ማሚቱ፣ ጠኔ እየጣላቸው፣ ነብስ የሚያነሳቸው ሌሎች እኮ አይደሉም፣ እኔና አንተ ናቸው፡፡ ቶሎ እየወደቅን ቶሎ የምንነሳ ቀለባችን ቆሎ ኑሯችን አበሳ ማሞና ማሚቱ፣ እኛ ነን አትርሳ፡፡ ከህይወት ግብግብ፣ እየሮጡ ገብተውማንበብ ይቀጥሉ…
ህዳሴው የማይነካቸው፣ ህዳሴውን የማይነኩ የሰፈሬ ወጣቶች
አንዳንዴ በግድ መገረብ ያለባቸው ፖስቶች አሉ ብለው እናምናለን። አምነንም እንገርባለን… ******* ህዳሴው የማይነካቸው፣ ህዳሴውን የማይነኩ የሰፈሬ ወጣቶች (ይሄ ፓስት ህዳሴው ትክክለኛ ነው፣ አይደለም ብሎ አይነታረክም) ‹‹‹‹‹‹ ››››››› እዚህች ሰፈር ነው ያደኩት፡፡ አድጌ “እግሬን ከመፍታቴ” በፊት ዓለም ከዚህች ሰፈር አትበልጥም ነበርማንበብ ይቀጥሉ…
ዝፍታ
(ከከፍታ እና ከዝቅታ የተዳቀለ) ****** ከዝቅታ አንስተን ከፍታ መንበር ላይ የሾምነው በሙሉ ተንከባሎ መውደቅ ሆነብን አመሉ እዚህ ዝቅታ ላይ አብሮን የቆሸሸ፣ አብሮን የጠለሸ አጣጥበን ብንሾመው ምነው ባንዴ ሸሸ? ዝቅ ለለመደ ከፍታ ይከብዳል? ብርድ ለለመደ ወበቁ ይበርዳል? ሰው ባፈጣጠሩ ዝቅታ ይወዳል?ማንበብ ይቀጥሉ…
ጎሬ-ቤቶች!
(ፀሀፊው፣ እኔ) ***** ጎረቤታሞች ናቸው፡፡ ከአጠራቸው ውጪ ግን ምናቸውም አይገናኝም። የአንዷ ኑሮ ቅንጦት የሌላኛዋ እጦት ነው፡፡ ያችኛዋ የምትበላው የላትም። ይህችኛዋ የማትበላው የላትም። አንድ ቀን… ያቺ የድህነት አቅም ማሳያዋ ሴት….ወሰነች! “የምበላው አጥቼ፣ ገርጥቼ ነጥቼ ከምሞት… አንድ ቀን እንኳን ጀመበር እስክትጠልቅ አጊጬ፣ተውቤማንበብ ይቀጥሉ…