ይሄውልሽ እምዬ፡- በሆዴ የያዝኩት የብሶቴ ክምር ብዙ ሲናገሩት-አብዙት ሲፅፉት፣ መስሎሽ ባዶ `ሚቀር- እንዳትታለዪ ይብሱን ነው `ሚያድግ፣ እጅጉን ነው `ሚንር ይቀለኛል ብዬ በነገርኩሽ ቁጥር፡፡ ከወደቁ ኋላ መፈረጋገጡ፣ ውጤቱ መላላጥ እንደሆን አውቃለሁ ግን ከዝም በላይ አይጎዳኝምና ስሚኝ ነግርሻለሁ! እዚህ ካንቺ ግቢ፣ እዚሁማንበብ ይቀጥሉ…
የሴቶች ካቴና!
ይህች ፅሁፍ ባለፈው ዓመት “በአዲስ አድማስ” ጋዜጣ ላይ ወታ ነበር፡፡ በጊዜው ትንሽ ተነካክታ ስለነበር ኦርጅናል መልኳን እንዲህ አቅርበናል፡፡ የሴቶች ካቴና! ሰልችተውኛል፡፡ አንዷ ከአንዷ በቁመት፣ በመልክ፣ በሰውነት ቅርፅ ቢለያዩ እንጂ በአዕምሮ አንድ ሆነውብኛል፡፡ ብዙ ሴቶችን አይቻለሁ፡፡ ያው ናቸው፡፡ ለፍቅር ስሱ ነኝ፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
እኛ ማን ነን…!
አውቀን የተኛን ነን፡፡ ቢቀሰቅሱን የማንሰማ! ከከተሳካልን ቀስቃሾቻችንንም አሰልችተን የምናስተኛ! …ሰውነታችን ጣምኖ ጮማ ከምንቆርጥ ይልቅ፣ ያለምንም ልፋት የምናገኛትን ጎመን እየላፍን፣ “ጎመን በጤና” የምንል ዘመናዮች ነን፡፡ ታሪክ ዳቦ አይሆንም ብለን፣ ታሪክ የማይሆን ዳቦ እየገመጥን ያለን በልቶ አደሮች ነን፡፡ ነፃታችንን ከባርነት እግር ስርማንበብ ይቀጥሉ…