በአንዲት እርጉም ቀን ልቤ ፅድቅ ሻተ; ከመፅሐፍህ መሃል “ግራህን ቢመቱ ቀኝ ስጥ” የሚል ቃል ለነብሴ ሸተተ; እልፍ ጠላቶቼ መንገዴን ተረዱ; በእፀድቃለሁ ሰበብ መስከኔን ወደዱ ; መጡ ተሰልፈው:- ግራዬን ነገሉ; ከቀኙም አንድ አሉ ወገሩኝ ደጋግመው ክንዳቸው እስኪዝል; ሁሉን ዝም አልክዋቸው ፅድቅህማንበብ ይቀጥሉ…
አንበሳ ዙሪያችን ሚዳቅዋ ልባችን!
አንበሳ ዙሪያችን ሚዳቅዋ ልባችን! (የአንበሳ ልብ ቢጠፋ፣ በአንበሳ ጫማ ሮጦ የማምለጥ ሀገራዊ ጥበብ) ********* እስቲ ዙሪያችሁን ተመልከቱት? ሁሉ ነገር አንበሳ ነው!! ተረታችን ሲጀምር፣ “አንድ አንበሳ ነበረ…” ብሎ ነው፡፡ አውቶብሳችን አንበሳ ነው፡፡ ጫማችን አንበሳ ነው፡፡ ዘፈናችን “ቀነኒሳ አንበሳ”፣ “አንበሳው አገሳ” …ማንበብ ይቀጥሉ…
ውይ መፅሐፍ ቅዱስ…
1. “ወደ እኔ የሚመጣ ሊከተለኝም የሚወድአባቱንና እናቱን፣ ሚስቱን እና ልጆቹን፣ወንድሞቹንና እህቶቹን፣ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀመዝሙሬ ሊሆን አይችልም” ሉቃ. 13፣33 እንደው ይቅርታ አድግልኝና እየሱስ፣ እንኳን እናትና አባቴን አሁን ታይፕ የማደርገውን ፅሁፍ እንኳ ትቼ ልከተለህ አልችልም፡፡ ካንተ በፊት እናትና አባቴን…ማንበብ ይቀጥሉ…
የእንባ አውራ ጎዳኖች
ይሄውልሽ እምዬ፡- በሆዴ የያዝኩት የብሶቴ ክምር ብዙ ሲናገሩት-አብዙት ሲፅፉት፣ መስሎሽ ባዶ `ሚቀር- እንዳትታለዪ ይብሱን ነው `ሚያድግ፣ እጅጉን ነው `ሚንር ይቀለኛል ብዬ በነገርኩሽ ቁጥር፡፡ ከወደቁ ኋላ መፈረጋገጡ፣ ውጤቱ መላላጥ እንደሆን አውቃለሁ ግን ከዝም በላይ አይጎዳኝምና ስሚኝ ነግርሻለሁ! እዚህ ካንቺ ግቢ፣ እዚሁማንበብ ይቀጥሉ…
የሴቶች ካቴና!
ይህች ፅሁፍ ባለፈው ዓመት “በአዲስ አድማስ” ጋዜጣ ላይ ወታ ነበር፡፡ በጊዜው ትንሽ ተነካክታ ስለነበር ኦርጅናል መልኳን እንዲህ አቅርበናል፡፡ የሴቶች ካቴና! ሰልችተውኛል፡፡ አንዷ ከአንዷ በቁመት፣ በመልክ፣ በሰውነት ቅርፅ ቢለያዩ እንጂ በአዕምሮ አንድ ሆነውብኛል፡፡ ብዙ ሴቶችን አይቻለሁ፡፡ ያው ናቸው፡፡ ለፍቅር ስሱ ነኝ፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
እኛ ማን ነን…!
አውቀን የተኛን ነን፡፡ ቢቀሰቅሱን የማንሰማ! ከከተሳካልን ቀስቃሾቻችንንም አሰልችተን የምናስተኛ! …ሰውነታችን ጣምኖ ጮማ ከምንቆርጥ ይልቅ፣ ያለምንም ልፋት የምናገኛትን ጎመን እየላፍን፣ “ጎመን በጤና” የምንል ዘመናዮች ነን፡፡ ታሪክ ዳቦ አይሆንም ብለን፣ ታሪክ የማይሆን ዳቦ እየገመጥን ያለን በልቶ አደሮች ነን፡፡ ነፃታችንን ከባርነት እግር ስርማንበብ ይቀጥሉ…
ስለ ሴቶች
ተከርክሞ የተገረበ፣ ቧልትና ቁምነገር!! “ስለ ሴቶች“ ( ስለ ወንዶች ደግሞ እነሱ ይፃፉ) ከአፈጣጠር እንጀምር፤ በኔ እምነት፣ ሴቶች የተፈጠሩት፣ ወንዶች በተፈጠሩባት ቅፅበት ነው፡፡ እንደ መጥሐፉ ከሆነ፣ ሴት የተፈጠረችው ሁለተኛ ነው፡፡ በደንብ ካየነው ግን እኩል ነው የተፈጠሩት፡፡ ወንድ ሲፈጠር፣ እንትን ነበረው አይደል?ማንበብ ይቀጥሉ…
ለሀገሬ፣ ለሃይማኖቴ፣ ለአላማዬ አልሞትም!!!
ለምን ዓላማ እና ለማን ዓላማ ለመሞት ዝግጁ ናችሁ? ለአላማ መሞት አሪፍ ነገር ነው አይደል? አዎ! አሪፍ ነው ለብዙኀኑ- በግሌ ለኔ አይደለም፡፡ በያዝኩት ነገር ምክንያት ሞት ከመጣብኝ፣ ምላሴን አውጥቼበት ላሽ እላለሁ እንጂ፣ የሞኝ ጀብደኛ ሞት አልሞትም፡፡ በመሰረቱ አላማ የለኝም ቢኖረኝም ሙትልኝማንበብ ይቀጥሉ…
ሞት እኩል ይሆናል ሕይወት
ሞት = ህይወት ‘‘የሞት እንቆቅልሽ የሚመስጠን፣ የማይቀር፤ ነገር ግን የማናውቀው ነገር በመሆኑ ነው’’-(አፍሮጋዳ) የ“አምላክ” ትልቁ ጥበቡ ሞትን መፍጠሩ ነው- ለኔ! እያንዳንዱ ሃይማኖት እግሩን ያቆመው በሞት ላይ ነው። ሞት ባይኖር የሰው ልጅ፣ በአምላክ አማኝ አይሆንም።ሃይማቶች እግር ይከዳቸዋል። …ዘር ካልሞተ/ካልበሰበሰ ፍሬ አይሆንም።ማንበብ ይቀጥሉ…
የማንን ሃሳብ፣ በማን ጭንቅላት እያሰባችሁ ነው?
የማንን ሃሳብ፣ በማን ጭንቅላት እያሰባችሁ ነው? ( ብዙ ጭንቅላቶች ቢኖሩም፣ ብዙ ሀሳበች የሉም) የሰው ልጅ አሳቢ ፍጡር ነው ቢባልም አብዛኛው ግን አይደለም፡፡ ብዙሃኑ ታስቦ ያለቀ አሳብ እራሱ ላይ ጭኖ የሚሄድ መንገደኛ ነው፡፡ ግቡ መሄዱ እንጂ መድረሱ አይደለም፡፡ “ለምን” የሚባል ጥያቄማንበብ ይቀጥሉ…
ሀገሬ ታማለች!
ታማሚ የመሆንሽን እውነት፣ ስታውቂው፣ ሳውቀው ሳይርቀን፣ ለምን ነው፣ ይህ አባይ ቃልሽ እውነቱን የሚደብቀን? ልንገርሽ አይደለ እውነት…. እንዳንቺም ታማሚ የለ በምድር የተስተዋለ አንድነት ቁስል ሆኖበት ልዩነት ደዌ ፀንቶበት፣ መንገዱን ለሞት ያበጀ ፍፃሜን በራ ያወጀ እንዳንቺም ታማሚ የለ፣ በምድር የተስተዋለ፡፡ ግራሽን ለመታማንበብ ይቀጥሉ…
ላኩኝ የማይል ደብዳቤ!
አምላክ ሆይ! ይህንን የምፅፍልህ፣ ከአመት ለማታልፍ ፍቅረኛ በውሸት በኮሹ፤ በቆሸሹ ቃላት ከምቸከችከው ውዳሴ ከንቱ የተሸለ መሆኑን አምኜ ነው፡፡ የእውነት አምላክ ነህና የምትወደው እውነትን ነው፡፡ ስለዚህ እቅጭ እቅጯን እናወጋለን፡፡ ሃሳቤን ለሰዎች ባወጋቸው በአንተ ያምኑ ይመስል፣ ደም ስራቸውን ገትረው፣ ዐይናቸውን አፍጠው ይከራከሩኛል፡፡አንተማንበብ ይቀጥሉ…
ከመሄድሽ ወዲያ…
ከመሄድሽ ወዲያ… በምን አይነት እርጉሚት ቀን እንደሁ እንጃ፣ በምን ኀይል አንደበቴ መታዘዝን እንዳገኘ… “ሂጂልኝ!” አልኩሽ፤ “ሂጂሊኝ፣ ከቤቴ ውጪ! ተይኝ!” አልኩሽ፡፡ ትዝ ይለኛል፣ ዐይኖችሽ ውስጥ የነበረው ግርምት እና ድንጋጤ! መልስ እንኳ አልሰጠሸኝም፡፡ ሄድሽ! ግን…… የዐይን እርግብግቢት ታህል እንኳን ካልቆየች መሄድሽ በኋላ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ኢንጂነሩ!
ምን አባቴ አቀበጠኝ ቀድሞውንስ? ምን ስሆን ያልሆንኩትን አወራሁ? ይሄው ለደቂቃ በተናገርኳት ነገር ለሳምንታት እየተሳቀኩ ነው፡፡ ሰፈር ሰላም ብዬ ከቤቴ ወጣ ብል፣ የሆነ ድምፅ ከኋላዬ “ኢንጂነር” ሲል ያሾፍብኛል- ኢንጂነር! “ሌባ! …ሌባው” ከመባል በላይ ያሳቅቀኛል፡፡ ህፃናት፣አዋቂዎች፣ የሰፈር ውስጥ ተራቢዎች፣ተመርቀው ስራ ያጡ ሰፈርማንበብ ይቀጥሉ…
የወንዶች ዓለም!
እንደ መፀሐፉ፣ እንደ ዘፍጥረት ቃል፣ የሰው ዘር መፈጠር፣ በአዳም ይጀምራል- ከአዳም ይለጥቃል፣ የአዳምን ብቻነት፣ አምላክ አስተዋለ፣ ረዳት እንድትሆን፣ ከገዛ አጥንቱ፣ “ሴት ብፈጥርስ” አለ፡፡ እዚህ ጋ፣ አስተውሉ፤ እግዜር ለሴት ብሎ፣ አፈር አላቦካም፣ ከአዳም ተስተካካይ፣ ጊዜን አልወሰደም፣ ብቻ ከግራ አጥንቱ፣ ወሰደ ፈጠራትማንበብ ይቀጥሉ…
ሶስት ሚስቶቹን ለምን ፈታ ካሉ…!
በመጀመሪያ ወንደ ላጤ ነበርኩ፡፡ በሰውም በሴጣንም ምክር፣ ትዳር ለመያዝ ቆረጠኩ( ፈጣሪ ምክር አይወድም መሰል ምንም አላለኝ)! …. እናም ነገር በሶስት ይፀናል ብዬ ሶስት ጊዜ አገባሁ፡፡ ፍቺም በሶስት ይፀናል ብዬ፣ ሶስት ጊዜ ፈታሁ፡፡ መቼም ሶስቴ አግብቼ፣ ሶስቴ መፍታቴ ከማመንዘር ፍላጎት የመነጨማንበብ ይቀጥሉ…
* አልገባኝም አያገባኝም!*
በወግ ደረጃ የመጀመሪያ ወጌ ናት እቺ፣ በትክክል ከተፃፈች አምስት ዓመት ያልፋታል( ከአንዳንድ ቃላት ለውጥ በቀር) እነኋት እራሷ…… * አልገባኝም አያገባኝም!* ^ ^ ^ ከሀገራችሁ ቁስል ይልቅ የአንድ እንግሊዛዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ስብራት የሚጠዘጥዛችሁ የሀገሬ ልጆች ሆይ! እንዴት ናችሁልኝ? ይሄ “ሜስ”ማንበብ ይቀጥሉ…
ንባበ ህሊና ወከባቢ
ያለሁበት መኪና(ተስፈኛ አንባቢዎች <ያለሁበት ባቡር> ብለው ማንበብ ይችላሉ) ያለቅጥ ይበራል፡፡ ይሄን ሹፌር፣ ‘ስምህን ሳጅን አሰፋ መዝገቡ ይጥራው!’ ብሎ የረገመው አለ? እላለሁ በውስጤ፡፡ `ኸረ ባክህ ቀስ በል` ይላሉ ካጠገቤ የተቀመጡት ሴቶች፡፡ በመስታዎት ውስጥ ውጭውን ማስተዋል ጀመርኩ፡፡ ………… በቀኙ የአስፓልት ዳር፣ መንገድማንበብ ይቀጥሉ…
ከዳ-ተኛ
ጓዴና እኔ፡- አብረን በላን፣ አብረን ጠጣን በሱ ስቃይ አቃሰትኩኝ በህመሙ አልጋ ያዝኩኝ በእኔ መሰበር እሱ አነከሰ እኔ ላይ ሲዘንብ አካሉ ራሰ፡፡ ጥርሴ ቢመታ የሱ ወለቀ እኔ ለወደኩ፣እሱ ደቀቀ፡፡ ኦፕራዎን ሲያደርገው ዶክተር የራሱ ነበር/ ወይስ የኔ ሆድ የሚተረተር ስንቱን ተካፈልን ስንቱንማንበብ ይቀጥሉ…
ይድረስ ለኢትዮጵያ -ዎቼ
1. ኢትዮጵያ አንድ (ለፍቅረኛዬ(ፍቅረኛዬ ለነበርሽው)) ኪያዬ፣ ማነው ጎበዝ ሰካራም የሰከረባትን ቅፅበት ይህቺ ናት ብሎ መነገር የሚችል? -ማንም! እኔም ባንቺ ወይንነት ስሰክር የሰከርኩባትን ቅፅበት አላስታውሳትም፡፡ በጣም መስከሬን ግን አውቃለሁ፡፡ አንቺ ግን በኔ ስካር፣ በኔ መንገዳገድ እና መኮለታተፍ ያ የሚያምር ሳቅሽን ትስቂብኝማንበብ ይቀጥሉ…