“ወጣቶች ፖለቲካ ውስጥ ተንጋግተው የገቡበት ሁኔታ ባብዛኛው በእኔና በሳል በሆኑ ሰዎች ግምት (ወይም በገባቸው ሰዎች ግምት) በአገራችን የሰፈነው ጭቆና አስከፊ ሆኖ መላወሻና መንቀሳቀሻ ጠፍቶአቸው ሳይሆን በረቀቀ ፕሮፓጋንዳ ግፊት መሆኑ ነው።
ፕሮፓጋንዳ አዲስ ፍጡር አይደለም፡ ድሮም ነበረ። ዛሬ የፈረሰውን የሰለሞናውያን ስርወ መንግስት እዚህ ያደረሰው የአንድ ሰው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ያውቃሉ? ታምሪን የተባለ ነጋዴ ለሳባ ስለ ሰለሞን ጥበብ ነጋ ጠባ ይነግራታል። በዚህ ምክኒያት ሰለሞንን በአይኗ ሳታየው ወደደችው። ክብረ ነገስት ‘ከፍቅሯም ብዛት የተነሳ ታለቅስ ነበር፡ ለመንግስቱም (ለሰለሞን መንግስት) ልትገዛ ፈፅማ ትሻ ነበር’ ይላል።
ደካማ ትሁን አትሁን ወይም የዞረባት ቁሌታም፡ እንርሳውና መጀመሪያውኑ ኢየሩሳሌም ሄዳ አርግዛ እንድትመጣ ቀስቃሽ ምክኒያት የሆናት የነጋዴው የታምሪን ጥዝጠዛ ነው። ጥዝጠዛ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ይሄን ክብረ ነገስት ውስጥ ሳነብ እስቅና እገረም ነበር። አንዳንዴ ነገር ነገር ሲለኝ ሰለሞን ብዙ ቁባትና ሚስት ስላለው ሳባ በእነሱ ቀንታ እንደ ማንኛዋም ርካሽ ሴት ሻሞ ልትገባ ያሰበች ይመስለኛል እላለሁ። የራጉኤሉ ቄስ ጎርጎሪዮስ በዚህ አተረጓጎሜ ሰድቦኛል። ‘እርጉም’ ብሎ።”
መረቅ