Tidarfelagi.com

‘ጉልባን’

“… ድል አውሪ በኦፊሻል ሙያው ‘ዳቦ ጋጋሪ’ ይባል አንጂ በድብቅ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ ትዝታ አንደርግራውንድ (ትን) የተባለ ድርጅት አባልና አነቃናቂ ነው።

የዚህ ድርጅት ስራው ከጥንት ጀምሮ በሀገሪቷ የነበሩ የኪነት ስራዎችን በፓይሬት ሬድዮ ለከተማው ህዝብ ማሰማት ነው። ለሰባት አመታት ለፀጋ መንግስት ዋና ሬድዮ ስቴሽን የድምጽ መሀንዲስ ሆኖ ሰርቷል። ዛሬም አልፎ አልፎ ለምክር ይጠራል። የምህንድስና ስራውን አቁሞ ዳቦ ጋጋሪነት እንዲገባ ያደረገችው ሚስቱ እንደሆነች የሚወራው ውሸት ነው። የራሱ ፍላጎት ነው። ወጣት መነኖችን በመመልመል መንግስት የሚያሰራጫቸውን የጸጉር ቅባቶችና ማጨጊያ መድሀኒቶች ለመነኖች ለመስጠት ሰርጎ ገቦች ያሰለጥናል። . . . .

መመልመያ ቦታዎቹ የህቡእ በርጫ ማረፊያዎች፡ እስር ቤቶች፡ ቨርቹዋል ደኖች ናቸው። ድል አውሪን አተኩሮ ላየው ይሄን ሁሉ ለመስራት የሚያስችል ብሩህነት እንዳለው ያስታውቃል። ካላዩት ግን በጫት የነበዘ፡ የመንገድ ቋንቋ የሚናገርና እዚህ ግባ የማይባል ሰው ነው።

ድብቅ ስራውን ለማኪያሄድ እንዲረዳው የሚጠቀምበት ስሙ ‘ጉልባን’ ይባላል። ጉልባን መባሉን የሚያውቀው ነቢያት ብቻ ነው። ስሙን የወሰደው ‘ጉልባን’ ከተባለ ከራሱ ዝነኛ ግጥም ነው። የ ትን አባል ከመሆኑ በፊት ለከተማው ብቸኛ ፓይሬት ሬድዮ አንዳንድ ግጥሞቹን ሲልክ በዚህ ስም ነበር። የመጀመሪያው የታወቀበት ግጥሙ ይሄ ነው።

አንቺ ስንዴ ነሽ እኔ ባቄላ
ተጣጠቢና እንበላላ

***
‘ጉልባን’ የተባለው የምግብ አይነት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ጋር የነበረው ቁርኝት ተላቆ፡ ስርአቱ ተዘርፎ፡ በቆርቆሮና በብልቃጥ እየታሸገ መሸጥ ከጀመረም በኋላ ስሙ አልተለወጠም። በ2060 አካባቢ ድል አውሪ ይሄን ግጥም በጻፈበት ሰሞን የወንድ ሀፍረት ‘ቄላ’ የሴት ሀፍረት ‘ስዴ’ ይባሉ ነበር። ድል አውሪ ‘ጉልባናችንን መልሱ!’ በተባለ መፈክር ዙርያ በሬድዮ ተቃውሞውን ይሰብክ ነበር።

***
ይወስዳል መንገድ፡ ያመጣል መንገድ

አዳም ረታ አንጋፋ የሀገራችን ደራሲ ነው፡፡

One Comment

  • haliya.temam@yahoo.com'
    haliya commented on April 19, 2017 Reply

    this is amazing adamyee

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...