Tidarfelagi.com

ድንግልና ድንግል ነው?

ብር አምባር ሰበረልዎ ጀግናው ልጅዎ” ይባላል:: ጉድ እኮ ነው:: ስስ ስጋ የሰበረው የዓለምን ሪከርድ ከሰበረው እኩል ይዘፈንለታል::
ወንድ የጀግንነት እጩ; ሴቷ የጀግንነት ማሳያ መዋጮ አድርጎ ይነግረናል:: አሁን ድንግልና ለሴቷ ምኗ ነው? ለሰው ልጅ ምኑ ነው? ምን ይጨምርለታል ምን ያጎድልበታል? ምን አይነት ሰካራም ተፈጥሮ ነው ሴት ላይ ማረጋገጫ ማህተም አኑሮ ወንዱን ባላየ የሚያልፈው? ለምንድነው ሴቷ ወንድ የተባለ ፍጡር ፊት ሞገስ ለማግኘት ድንግልና የሚባል መከልከልን ይዛ የምትዞረረው?
ከወንዱ ለይቶ ይሄን ሸክም ያሸከማት ማነው? ክብረ ንፅሕና አላት ይባልላታል…ወሲብ ቆሻሻ ነገር ሆኖ ነው አለማድረግ የሚያኮራው? ለማነው ድንግል ሆና የምትቆየውስ?
ማሕበረሰቡ እግሯ መሀል ምን አገባው?
ሲያስቅ እኮ! ድንግልና ውስጣዊ ስስ አካላትን መከላከያ የስጋ ግድግዳ እንጂ ሌላ አይደለም:: ቢሆንስ ሴት የወንድ አደራ እቃ ነች?

አንዱ እንዲህ አለኝ “ከድንግል ሴት ጋር ወሲብ ማድረግ መድረክ አይቶ ከማያውቅ አማተር ጋር መድረክ ላይ ወጥቶ የራስን ውብ እንቅስቃሴ ማበላሸት ነው……”

እኔ እጠይቃለሁ…
እውነት ግን ድንግልና እራሱ ድንግል ነው? ህግ አውጥተው ህግዋን ወሰደ ቢሉኝ ትርፌ ምንድነው? የማነውስ ድንግልና? የወንዱ? የሴቱ? ለወንዱ ወይስ ለሴቱ? ይሄንንም የምር አርጉት አሏችሁ ደግሞ…

የራስ ናቸው፡፡ የማንንም ሃሳብ ለመፃፍ አልተከፈተም! የሚያስማሙንን ሃሳቦች እዚህ ካገኛችሁ እሰየው፡፡ ለመስማማት አንፅፍም፣ ለመፃፍ አንስማማም፡፡ ወዘተ

2 Comments

  • ወንድማገኝ commented on June 11, 2017 Reply

    fb

  • ሀብታም commented on April 24, 2018 Reply

    በጣም ምርጥ ነው

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...