Tidarfelagi.com

ይበለኝ

በቀደምለት፤አልጄዚራ ያማርኛ ክፍል ጋዜጠኛ ከኔ ጋር አጭር ቃለመጠይቅ አድርጋ ነበር፤ በሁዋላ ግን ቃለ መጠይቁ ከባህላችን ጋር ስለማይጣጣም ልናቀርበው አንችልም የሚል ኢሜል ላከችልኝ፤ ለማንኛውም ሙሉ ቃለመጠይቁ ይህንን ይመስላል፤

“የት ነው የተወለድከው?”
-ሆስፒታል
“የትውልድ አገርህ ማለቴ ነው”
-ማንኩሳ ሚካኤል

“በልጅነትህ የሚያስደስትህ ነገር ምን ነበር? ”

-ከትምርት ቤት መቅረት

“ስነ ፅሁፍ ላንተ ምንድናት?”

-ስነፅሁፍ

“በቀን ውስጥ ምን ያክል ሰአት ትተኛለህ?”

-በቀን አልተኛም

“ታጨሳለህ?”

-አልፎ አልፎ

“ምንድነው የምታጨሰው?”

-ሰንደል!

“ተደምረሃል?”

-አዎ ተመርምሪያለሁ

“ተደምረሃል ወይ ነው ያልኩህ?”

– ነገርኩሽ!ተመርምርያለሁ፤ እናም፤ ከመጠነኛ የጆሮ ችግር በቀር ሁለመናየ ጤነኛ እንደሆነ አረጋግጫለሁ፤

“ዶክተር አብይን እንዴት ታየዋለህ?”

-በቴሌቭዥን

“የየትኛውፓርቲ ደጋፊ ነህ?”

-የኢህአዴግ

“ኢሀዴግን በምንድነው የምትደግፈው?”

-በባላ

“ምን ያዝናናሃል?”

-ፓርክ ውስጥ መናፈስ

“የዚህ አመት እቅድህ ?”

-አለመታፈስ!

“እስቲ የሚያስቅ ወይም የሚያስደስት ገጠመኝ ካለህ ንገረኝ፤ህዝብ የሚያነበው ስለሆነ የብልግና ቃል ባይኖርበት ይመረጣል፤”

እሺ፤

እንደምታቂው፤ የሴት መብትን በማክበር አሜሪካን የሚደርስባት የለም፤እና ብዙ ያገራችን ዲያስፖራ ወንዶች ፤ፈረንጅ ሴት ለመጀንጀን በጣም ይፈራሉ፤ ብዙዎች ያሜሪካን ህግ ለማክበር ሲሉ በሁለተኛ ዙር ድንግልና ውስጥ ለመኖር ይገደዳሉ፤

አንድ ቀን አንድ ባልንጀራችን፤ እንደምንም ተደፋፍሮ አንዲት የፈረንጅ ኮረዳ በጥቂት እንግሊዝኛ እና በብዙ የምልክት ቁዋንቁዋ ጀንጅኖ ቤቱ አመጣት፤ ጥቂት ሲስማት እና ሲደባብሳት ቆይቶ ልብሱዋን ለማውለቅ ሲሞክር “ገና አስራ አምስት አመቴ ነው፤ ሁለት ሺ ዶላር ካልሰጠኸኝ ደፈረኝ ብየ ፖሊስ እጠራብሃለሁ” ብላ ቀወጠችው፤ በጣም ደንግጦ ለኔና ለሌሎች ጀለሶቹ ከዚህ ጉድ አውጡኝ ብሎ ደወለልን፤ እኛም ፤በጥድፍያ፤ መጠነኛ ጎፈንድ ቢጤ አዘጋጅተን ሁለት ሺ ብር ከሰበሰብን በሁዋላ ለልጂቱ ሰጥተን ገላገልነው፤
ከዚያ በሁዋላ ጉዋደኛችን አይናችንን ለማየት አልደፈረም፤ ዞር ስንልለት፤ ሰባት የእንቅልፍ ክኒን በመዋጥ ራሱን ለመግደል ሞከረ፤ይሁን እንጂ ሙከራው አልተሳካም፤ላራት ተከታታይ ቀን እንቅልፍ ተኝቶ ነቃ፤ እና ላራት ተከታታይ ቀን የስራ ገበታው ላይ ባለመገኘቱ ከስራ ተባረረ፤ራሱን ለመግደል ከመሞከሩ በፊት ትንሽ ማስታወሻ(suicide note ) ፅፎ ትራሱ ላይ አስቀምጦ ነበር፤ እንዲህ ትላለች፤

ይበለኝ! ይበለኝ! እሰይ ምናባቴ!
ያገሬን ሴት ትቸ ፤ነጭ ልነጭ ማድባቴ
መዘዞ ናት ብየ፤ መዘዜን ማጨቴ
ደሞ እንደቀናው ሰው፤ ያንን መላጨቴ
ቸኩሎ መዳራት፤ለማንም ላይበጂ
እኔን ብሎ በጂ!

Bewketu Seyoum (Ge’ez: በዕውቀቱ ስዩም) is an Ethiopian writer and poet from Mankusa, northwest of Addis Ababa.

One Comment

  • solomon215mekonnen@gmail.com'
    ሰለሞን መኮንን commented on June 16, 2019 Reply

    አሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...