እኚያ ጓደኞችህ ጴጥሮስ ወይ ዮሀንስ
ናትናኤል ፊሊጶስ
ቀራጩ ማቲዎስ
ሌሎቹም በሙሉ
ጌታ ሆይ እኔ እሆን? እኔ እሆን? ሲሉ
አይደለም ሲባሉ
የእነሱ እናቶች በደስታ ሲዘሉ
ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ
ከደሙ ላይ ነክሮ ምልክት ሲያደርግህ
ዐይኗ ምን አነባ ልቧ ምን ታዘበ
ከናንተ አንደኛው ዲያቢሎስ ነው ሲልህ እግር እያጠበ
ከየት ነው ትዕግስቷ
የእናትህ አንጀቷ
የመቻል ፅናቷ
ምናለች ይሁዳ ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ
ምልክት ሲያደርግህ
እንደ ማሪያም አለቀሰች
ለኔ ስትል ብላ ወድቃ ተማፀነች
ወይንስ ለልጇ ያንተ እናት ጨካኝ ነች
ምናለች እናትህ ታማኝ ነው ስትል ይሁዳ ያለችህ
የሰው ልጅ ይሰቅሉታል
ሰቅለው ይገድሉታል
ቢገድሉት ይነሳል
ግና ላሰቀለው
ግና ላስገደለው
ወዮለት ለዛ ሰው
ብሎ ሲናገርህ
ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ
ከደሙ ላይ ነክሮ ምልክት ሲያደርግህ
እናትህ መለሰች
እንዲህ ተናገረች?
እውነት ነው ጌታ ሆይ ባይወለድ በተሻለው
ግና እንድወልደው እናቱ እንድሰኝ ማሕፀኔን ብትፈታው
በአርኣያ በአምሳልህ ሰው አርገህ ብትሰራው
የወለድኩስ እኔ የፈጠረው ማነው
ብላለት መለሰች
ወይንስ ምን አለች
ምን አለች እናትህ?
አንተን ሲጠቁምህ
ምልክት ሲያረግህ!!
ሶልያና ከተሰኘው የግጥም CD ላይ የተወሰደ
2 Comments
እናቴ፡እሺ፡እናቴ፡ከልቤ
አስደናቂ