በልጅነቴ አጎቴ በአንድ ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰጠኝ የ5 ብር ወረቀት ላይ የሚታዩት ሰው ለዘመናት የእጅ ስራ ስዕል እየመሰሉኝ ስኖር ቆይቼ በቀደም ዕለት አንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ ይህን ምስል ልኮ እስከ ዛሬ ድረስ በህይወት የሚገኙ ግልሰብ መሆናቸውን ከገለጸልኝ በኋላ ሙሉ ታሪካቸውን እና ስማቸውን አጣርቶ በድጋሚ እንደሚልክልኝ ቃል ገብቶ ደምጹ ጠፋ እኔም ምን አልባት እናንተ ስለእኝህ ታሪካዊ ሰው የምታወቁት የተሟላ መረጃ ሊኖራችሁ ይችላል በሚል እምነት ይህን ስም እና ታሪክ አልባ ምስላቸውን ለጥፊዋለሁ።
እንፈልጋቸው ከዛም ስናገኛቸው ተባብረን የአቅማችንን ያህል አዋጥተን አንድ ነገር እንሸልማቸው እንዲሁም በቃል የተያዘ ይረሳል የተጻፈ ይወረሳል እንዲሉ ታሪካቸውንም ጽፍን ወደ ትውልድ እናስተላለፍ እንጂ እንዳለፈው ጊዜ እነዚህ ውድ ታሪክ ሰሪወቻችን እስኪሞቱ ድርስ እየጠበቅን ነብስ ይማር RIP በሚለው ቃል ብቻ አንለፋቸው።
ጥንት እነአበው ቀጣይ ትውልዳቸውን ሲመክሩ…. የቆምክበት ምድር አባቶችህ የወደቁበት ትቢያ ነውና ውለታቸውን ከቶ አትዘንጋ… ይላሉ።
One Comment
በጣም ጥሩ ነዉ