ጉልባን ከተፈተገ ሰንዴ ከባቄላና ከሽምብራ ጋር ተቀቅሎ የሚዘጋጅ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በእለተ ሐሙስ የፀሎት ቀን ወደ ስቅለተ አርብ ለመሸጋገሪያ በምዕመናን የሚቀመስ መንፈሳዊ ቁርስ ነው። ታሪኩን ለማስጠር ያህል ነው እንጂ ይህ ቁርስ ጥንት እስራዔላውያን ከግብጽ ባረነት ወጥተው የቀይባህርን ከተሻገሩበት ረጅም ጉዞ ጋር የተያየዘ መንፈሳዊ ታሪክ አለው። አጉል ባህል ወይም አጉል እምነት አይደለም።
መወገድ ያለበት ዘመናዊ የሆንን እየመሰለን ሳናነብ ሳናመዛዝን የሰው ድርጊት ተከትለን ገደል እየገባን የኖርንበት አጉል ባህላችን ብቻ ነው።
ዛሬ ደግሞ የድንግል ልጅ ጌታ የሐዋርያቶቹን እግር አጥቦ የትህትናን ታላቅነት በተግባር የመሰከረበት የመጨረሻው የማዕድ ስርዓት የተደረገበት ዕለት ነው። መልካም ፀሎተ ሐሙስ ይሁንላችሁ።
–ታላቁ ትህትና–
ብጸልይ ብዘምር ቅዳሴ ብመራ
ትዕንግርት ባሳይ ታዓምር ብሰራ
በመላዕክት ቋንቋ በልሳን ባወራ
ሺ ግዜ በስግደት ብደፋ ብቃና
ምን አልባት ቢጎድለው ትንሽ ትህትና
ዋጋ ቢስ ነው ከንቱ የእኔም ክርስትና።
/ኤዱዋርዶ ባይሮኖ/
One Comment
ብጾም:ብሠግድ:ለ እኔው:
ሄጄም:ከ ደጃፋ:
በ ነቅዓ:ጥበብ:
ቢሠብክ:ጳጳስ:ካህናቱ:
እኔነቴን:የማውቅ:
ከ ፈጠረኝ:በታች:
ለ አሽሙር:ስብከታቸው:
አይገደኝ:ፍንካች:
ባባቴም:በ እናቴም:
ሌላ:የለኝም:አማራጭ:
ዘ ራዶዖም