ጣሊያንኛ የማይችለው፣ የውጫሌ ስምምነት ተርጎሚ!( የውጫሌ ስምምነት)
እዚህ ጋር አንድ ስላቅ አለ። የውጫሌ ስምምነት ተርጓሚ የነበሩት( የተባሉት?) ግራዝማች ዮሴፍ ንጉሴ አማርኛ እና ፈረንሳኛ እንጂ ጣሊያንኛ አይችሉም ነበር። ታዲያ እንዴት ጣሊያንኟውን ተረጎሙት? የጣሊያንኛው ቅጂ በሮም ተዘጋጅቶ እንደመጣና ግራዝማች ዮሴፍም ለጣሊያኖች በብር በመገዛታቸው እንደሆነ የሚገልፁ አሉ። የውጫሌ ውዝግብ ሲነሳም አንቶነሊ ተወቃሽ አድርጎ ያቀረበው ግራዝማቹን ነው። ምኒሊክ ግራዝማች ዮሴፍን ከመቅጣት ወደ መከላከል ማዘንበላቸው መልካም ሊባል የሚችል ነው። የጣሊያኖችን የማናቆር ስሜት ከማርካት ባለፈ ፋይዳ አይኖረውም ነበር። በነገራችሁ ላይ አንቶሎኒ እዚህ በነበረበት ወቅት ከተለያዩ ሴቶች የወለዳቸው ልጆች ነበሩት። በትኗቸው ነበር የሄደው። የአንቶነሊ ዘሮች አሁን የት ይሆኑ? የልጅ ልጆቹስ የት ይሆን ያሉት?….
በወቅቱ ጣሊያንኛን ጨምሮ የተለያዩ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው አልፍሪድ ኢልግ ወደ አውሮፓ መሄድ ለችግሩ ቶሎ አለመታወቅ እንደ ምክንያት ይታያል።
የውጫሌ ስምምነት ከተፈፀመ በኋላ ትቁር መልከ የታያቸው አለቃ አጥሜ “አንቀፅ 17”ን እንዲመረምሩ አስቀድመው ነግረዋቸው ነበር። ምኒሊክም አማርኛውን አስመረመሩ። አማርኛው ላይ ምንም ችግር ስላጡበት አለቃ አጥሜን አሳሰሯቸው። ከዓመት በኋላ ግን ልክ መሆናቸውን ሲያውቁ ሹመት ሰጧቸው..