Tidarfelagi.com

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስመልከት ስለፍቅር እንሰብካለን

በፊት … ስለፍቅር ሳላነብ በፊት… ፍቅር በሶስት ይከፈላል ብዬ አስብ ነበር። ሰዎች… ነገ ምን እንደሚፈጠር ሳናውቅ ማውራት የምንችለው ስለምን እንደሆነ የማናውቅ ፍጡራን መሆናችንን ማመን ታላቅ ጥበብ እንደሆነ የገባኝ ግን ዘግይቶ ነው። በዘገይም አብሮ የገባኝ እውነት ምስክር መሆኔን አውጃለሁ። ይህንን አምኜም ስክሬ አሳክራሁ 😜

ስለነገ ነገ ላይ ደርሰን እስክናወራው ዛሬ ስለፍቅር እንዘፍናለን። ባልኩ ጊዜ እኔን ብሎ የመጣ ሰው ሁላ በአንድ ድምፅ እንዲህ ሲል ተሰማኝ፦

“አትዘፍንም! ጃ ያስተሰርያልን ዝፈን!”

“እና እናንተ ያላችሁኝን ካልዘፈንኩ አትወዱኝም?” ስል ጠየኳቸው።

“አዎ!!” ሲሉ በመስማቴ አፈርኩ። ተሸማቀቅኩ። ይህ ሁላ ህዝብ፣ ፍቅር ምን እንደሆነ ሳያውቅ ነው ክርስትናን የተቀበለው? ስል ተሸማቀቅኩ።እስከዛሬ ድረስ ዘፋኝ ነኝ ብዬ አምነው ነበር። አሁን ግን ፖለቲከኛ አድርጎ ህዝብ እንደተቀበለኝ ተረዳሁ። ህዝብ የፈለገውን ማለት ካልቻልኩ እኔ ማለት ፖለቲከኛ መሆኔን የዘነጋሁ እንደሆነ ዘግይቶም ቢሆን ገባኝ።

ቂም ለማንም አልበጀምና ወደፍቅር ጉዞ
ዳይ

ፍቅር… ያው ፍቅር እንደሆነ እንደኔው የደረሰባችሁ ትረዱኛላችሁ በሚል ዛሬ የምናወራው ስለፍቅር ነው፦ 😜
እኮ ፍቅር ምንድነው?!

ተክለሐዋርያት ተክለማሪያም ስለፍቅር እንዲህ ይላሉ፦

“ሰው ምንም የተማረ ቢሆን ምዕራባዊ አውሮፓን ካልጎበኘ የአውሮፓን ስልጣኔ በትክክል ለመረዳት አይችልም። ዕውቀቱም ሙሉ አይሆንም። ምዕራባውያን እኛን ሩስያኖችን ከግብዞች፣ ከገልቱዎች ይቆጥሩናል። ለዚህም ምክንያት ይገኝላቸዋል። እነሱ ከኛ በፊት መሰልጠናቸው በታሪክ ላይ የታመነ ነው። አሁንም ቢሆን ከኛ በፊት መሰልጠናቸው አያጠራጥርም። ነገር ግን እንዴት ነው የሰለጠኑት? አንጎላቸውን፥ አንደበታቸውን፥ እጆቻቸውን፥ አኗኗራቸውን አሰልጥነዋል። ልቡናቸው ግን ወደጨካኝነት ተዛውሯል። ሃይማኖታቸውን፥ ፍቅርን፥ ቁም ነገርን ትተዋል። ነውርን ንቀዋል። ቅሌተኛነት አያስጠይፋቸውም።

ይህ ሁሉ ያረጀ ፈሊጥ ይመስላቸዋል። ፈጣሪን ክደዋል፤ ማቴሪያሊስቶች ሆነዋል። እምነታቸውንና ተስፋቸውን በነዋይ ላይ ብቻ አድርገዋል። ዕውቀት የሚያስፈልጉት ለምድራዊ ኑርዋቸው ማደላደያ የጥበብና የዘዴ ማከናወኛ መስሪያ እንዲሆናቸው ነው እንጂ ለልቡናቸው ነፍሳዊ ሃይል እንዲሰጣቸው አይደለም። ዕውቀታቸው የስሌት፤ የሒሳብ ነው። ጥቅምን ለመፍጠሪያ ነው። ጥቅምን እየፈጠሩ ወዲያውም ችግርን ይፈጥራሉ። ነጋዴዎች ናቸው። ሁሉንም ለገንዘብ ይለውጡታል። ጥበባቸው ሁሉ ወደ ጥፋት የሚወስድ ነው። ሁሉ ምዕራባውያን የሚገሰግሱት ከሌሎች ሕዝቦች በፊት፥ ለሌላው አጥፊዎች ራሳቸውም ጠፊዎች ለመሆን ነው።”

(ኦቶባዮግራፊ፤ ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ። ገፅ 139- 140

አነሳስቶ ላስጀመረኝ… አስጀምሮ ላስጨረሰኝ…
ምሥጋና ይገባዋል!

One Comment

  • Meliyo commented on January 28, 2019 Reply

    በጣም አመሰግናለሁ ደስ ይላል

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...