የተቀሸቡ ፎቶዎች ፤ ቁጥር 1
የሆነ ጊዜ ላይ የራስ አሉላ አባነጋን ፎቶ ፍለጋ ወደ ጉግል ተሠማራሁ ። ጉግል ሁለት የማውቃቸውን ፎቶዎችና አንድ አዲስ ጨምሮ አቀረበልኝ። አዲሱ ምስል ”አሉላ አባ ነጋ በወጣትነቸው ዘመን “የሚል መግለጫ አለው። ፎቶው “አረና ትግራይ “ተብሎ ለሚጠራ የፌስቡክ መታወቂያ ፎቶ(ፕሮፋይል ፒክቸር) ሆኖ መቆየቱን መገንዘብ ቻልኩ። ፎቶውን ባየሁት ቁጥር ከሽማግሌው አሉላ ጋር አልመሳሰልልህ እያለኝ ስቸገር ነበር፡ ፡ እርጅና ይህን ያክል ሰውን ይለውጣል እያልሁ ተክዣለሁ።
ፎቶው ላይ የሚታየው ፊት የ ራስ አሉላ አባነጋ ሳይሆን የስመ ሞክሼው ያንድ የሽዋ መስፍን ገጽታ እንደሆነ የተገነዘብኩት በቅርቡ ነው። ደ ካስትሮ የተባለ የጣልያን አሳሽ ወደ ሸዋ ብቅ ብሎ ከተዋወቃቸውና ፎቶ ካነሣቸው ሰዎች ያንዱን ምስል መጽሐፉ ውስጥ አካቶታል። ከታች በጣልያንኛ ከተጻፈው መግለጫው እንዲህ ይላል” ፊታውራሪ አሉላ፤ የአርሲ ገዥ የደጃዝማች ሉልሰገድ ልጅ(የሸዋ መስፍን)”
ምን ለማስተላለፍ ፈልጌ ነው 🙂 ሞኝና ጉግል ያስያዙትን አይለቅም። በጥንታዊ ፎቶዎች ላይ የሌለ መግለጫ(caption)ሰጥተን ወደ መረጃ ቋት በከተትናቸው ቁጥር ብዙ ሰው ልናሳስት እንችላለን።
“በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ ” ይላሉ የቤት ሠራተኞች ሲተርቱ፡ ፡ ለመሆኑ በራስ አሉላ ዝና ሲወደስ የከረመው ፊታውራሪ አሉላ በግሉ ምን ፈጽሞ ይሆን? እያጣራን ነው። አንገቱ ላይ ያሠረው ጨሌ ሻሜ ይባላል። ሻሜ ብዙ ጠላት ገድሎ ጀብድ የሠራ ጀግና ብቻ የሚያጠልቀው ነው።
ድሮ ለጀግና ሲዘፈን፤
በተወለደ ባስር ዐመቱ
አፈሰሰበት፤ ሻሜ ባንገቱ
ይባል ነበር።
ራስ አሉላ በተጭበረበረ ፎቶ መታወሱ ቢያሳዝንም በጀግና መወከሉ ያጻናናል፡;
2 Comments
dess yelal dess yelal
+251930833641