Tidarfelagi.com

ዝፍታ

(ከከፍታ እና ከዝቅታ የተዳቀለ)
******
ከዝቅታ አንስተን ከፍታ መንበር ላይ የሾምነው በሙሉ
ተንከባሎ መውደቅ ሆነብን አመሉ
እዚህ ዝቅታ ላይ አብሮን የቆሸሸ፣
አብሮን የጠለሸ
አጣጥበን ብንሾመው ምነው ባንዴ ሸሸ?

ዝቅ ለለመደ ከፍታ ይከብዳል?
ብርድ ለለመደ ወበቁ ይበርዳል?
ሰው ባፈጣጠሩ ዝቅታ ይወዳል?
ታች ለለመደ ከፍታ ያወርዳል?
ነው ከከፍ በልጦ፣ “ዝቁ” ይወዳል?
ታዲያ በምን ሰበብ፣ የዝቅታ አንጋፎች ከፍታውን ጠሉ
ጠዋት ሰቅለናቸው ቀትር ላይ ዱብ አሉ
እዚህ እታቹ ላይ እድሜ እንዳልቆጠሩ
ምነው ከፍታው ላይ አንድም ቀን ሳያድሩ?
ይህን የጠየቁ
አንድ እውነት አወቁ
የዝቅታን ጠለል ከፍ አርጎ ለኖረ
ዝቅ ማለት የለም ከከፍ የከረረ፡፡

የራስ ናቸው፡፡ የማንንም ሃሳብ ለመፃፍ አልተከፈተም! የሚያስማሙንን ሃሳቦች እዚህ ካገኛችሁ እሰየው፡፡ ለመስማማት አንፅፍም፣ ለመፃፍ አንስማማም፡፡ ወዘተ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...