ከአስራ ሶስት እህት ድርጅቶቹ በአንዱ ውስጥ ጀማሪ የማርኬቲንግ ሰራተኛ ነሽ።
ድካሙ ብዙ፣ ደሞዙ ትንሽ ነው።
አግብተሻል።
የሁለት አመታት ባልሽ ከአመት በፊት ከስራ ከተቀነሰ ወዲህ ስራ ለማግኘት ሳያሳልስ ደጅ ቢጠናም አልሆነለትም። ብዙ ነገር አይሆንለትም። ግንባር ብቻ ሳይሆን ራእይም የለውም። የሚሰራውን ሰርቶ፣ የዘመኑ ወንድ እንደ ሚሮጠው ሮጦ ገንዘብ የመሰብሰብ፣ ቶሎ ሃብታም የመሆን እቅድ የሌለው ልፍስፍስ ቢጤ ነው።
ይሄ ያማርርሻል። ያንገሸግሽሻል።
ክፉኛ ያስጠላሻል።
ደሞዝሽ ለኮንዶሚኒየም ኪራይ ተከፍላ፣ ሆዳችሁን ሞልታ፣ ከታክሲ ተርፋ የወጣትነት ውበትሽን ለመንከባከብ የሚያስችል ርካሽ ኮስሞቲክስ እንኳን መግዛት ይሳናታል። በሃያ ሰባት አመትሽ ሰላሳ ቤት የገባሽ የምትመስይው ውበት አጥሮሽ አይደለም። ገንዘብ ጎድሎሽ ነው።
ይሄኔ ነው አቶ ይሄይስ፣ የአስራ ሶስቱ ድርጅቶች ባለቤት አንቺ የምትሰሪበት ቢሮ ለጉብኝት የመጣው። እንከን አልባ ሱፍ ግጥም አድረጎ ለብሷል። ጫማው እንደ መስታወት ያበራል። ጥፍሮቹ በጥራት ተከርክመው፣ ጠጉሩ በስርአት ተበጥሯል። ሽማግሌ ይሁን እንጂ ጥራት ያለው ሰው ነው ብለሽ አሰብሽ።
አንቺ አካባቢ ካሉት ባልደረቦችሽ እና አለቆችሽ ጭምር አጠር ያለ ወሬ አውርቶ አንቺ ዴስክ ጋር ሲደርስ ግን የባጥ የቆጡን እየቀባጠ ረጅም ጊዜ ይቆያል። ባልደረቦችሽ በግርምት ያፈጣሉ። ያፈጡብሻል። እንዳልገባሽ ሆነሽ በቆምሽበት ዴስክሽን እንደ ሰው እየዳበስሽ እርባና የሌላቸው ጥያቄዎቹን እየተሸኮረመምሽ ትመልሻለሽ። ሰው ሁላ አንቱ ሲለው አንቺ ግን በድፍረት አንተ እያልሽ ታወሪዋለሽ።
‹‹ማርኬቲንጌ እንዴት ነው? ብዙ ተወዳዳሪ ፈርኒቸር ቤቶች እየተከፈቱ ነው…እንዳታከስሪኝ.ወጥረሽ እየሰራሽ ነው?›› አይነት ጥያቄ ነው ቃላት እየለዋወጠ የሚጠቅሽ።
‹‹አዎ አቶ ይሄይስ›› ትያለሽ መልሰሽ መላልሰሽ።
በሁለተኛው ቀን ዋናው ቢሮ ትፈለጊያለሽ ተብሎ ይደወልልሻል። ማነው ፈላጊዬ ስትይ ‹‹አቶ ይሄይስ›. ትልሻለች ጸሃፊዋ።
እየገባሽ ባልገባው ሰው ሁናቴ አለችኝ የምትያትን፣ ውብ ታደርገኛለች የምትያትን በቢሮና በመጠጥ ቤት መሃከል ያለች አረንጓዴ ቀሚስሽን በዚያ የፈረደበት ጓደኛሽ አበባ ከዱባይ ባመጣችልሽ ‹‹አንድ ለእናቷ›› ጥልፍልፍ ጥቁር ሂል ጫማ ታደርጊና፣ ፊትሽን ከወትሮው በተለየ ትቀባቢና፣ ጠጉርሽን ያምርብኛል እንደምትይው ወደላይ ታሲዢና ከቀጠሮሽ አስራ አምስት ደቂቃ ቀድመሽ አቶ ይሄይስ ቢሮ ከች ትያለሽ።፡
ቢሮ እንደገባሽ በስርአቱ ጨብጦ ቁጭ በይ ይልሻል። ከቢሮው እና ከጠረጴዛው ትልቅነት የተነሳ ቦታው ሄዶ ሲቀመጥ በመሃላችሁ አምስት ሰው የሚያቆም ክፍተት አለ። ግን ያልብሻል። እጅሽን እንደያዘሽ፣ አንገትሽን እንደዳበሰሽ፣ በጡቶችሽ ጫፍ እንደተጫወተ ሁሉ ክፉኛ ያሽኮረምምሻል።
ሁለታችሁም የምታደርጉተን ታውቃላችሁ ግን ማስመሰል ላይ ብርቱ ናችሁ።
ወሬያችሁ ጭራ እና ቀንድ አልባ ይሆናል።
ስለ ስራ ያወራሻል። በቅርብ ጣልያን ሄዶ ስለመምጣቱ ይነግርሻል። ማርኬቲንግ የት እንደተማርሽ ይጠይቅሻል። ‹‹ቅድስተ ማርያም›› ስትይው ‹<‹ያንስሻል›› በሚል አይን አይቶ ውጪ ሃገር ስላሉ የማርኬቲግ አጭርና ረጅም ኮርሶች ይዘረዝርልሻል። ካምፓኒው ሊያስተምርሽ እንደሚፈልግ፣ አንደ ትልቅ ሃብት እንደሚያይሽ ያወራሻል።
ትሽኮረመሚያለሽ።
ትስቂያለሽ።
ትንሽ ትንሽ ታወሪያለሽ።
ከዚያ እንደ ቀላል ነገር የሃያ ሁለት አመት ሚስቱ እና የአራት ልጀቹ እናት በጠና መታመሟን እና የሚስትነት ግዴታዋን መወጣት ስላለመቻሏ ሳያዋርዳት- እንዲያውም እያዘነላት -ይነግርሻል።
ባለትዳር መሆኑ ላንቺ ዜና ስላይደለ የምትደነግጪው በመታመሟ ብቻ ነው። ለምን ይሄን ነገረኝ ብለሽ ታስቢያለሽ ግን አትጠይቂውም። ለምን አስቦኝ ነው ብለሽ አትጨነቂም። ይልቅ አንቺም ባለትዳር ስለመሆንሽ እንደ ዋዛ እንዲህ ብለሽ ትነግሪዋለሽ።
‹‹እኔ ካገባሁ ገና ሁለት አመቴ ነው….ሃያ ሁለት አመት ረጅም ነው››
በድንገት ወሬያችሁ ይቆማል።
ባለትዳር መሆንሽን ቀድሞ ያላወቀ ይመስላል። ርካሹ ወርቅ መሳይ ቀለበትሽ ለሃብታም አይኑ አይታየውም?
‹‹ግዴለም…እኔ ጓደኝነትሽን ነው የምፈልገው›› ብሎ ይስቃል። ውሸቱን ነው። በግራ እጁ ጢሙን እየነካካ ነው።
እሱ እንደዚያ ሲያደርግ አንቺ ያጠለቀውን ግብዲያ ሰአት ታያለሽ። ሲኤን ኤን ላይ ታይምለስ ተብሎ ሲተዋወቅ ያየሽውን-ሰአቱን በትኩረት ታያለሽ። በሆድሽ ስንት ብር ይሆን ብለሽ ትጠይቂያለሽ። የተከራየሽውን ኮንዶሚኒየም ሊገዛ እንደሚችል ትገምቺና ፈገግ ብለሽ ‹‹እሺ›› ትያለሽ።
ስለሚስቱ ማውራት ይቀጥላል። ስለ በሽታዋ። መሞቷ እንደማይቀር። ያልወሰድኳት ሃገር፣ ያላያት ሃኪም የለም። ከዚህ በኋላ ምንም መፍትሄ የለው ይልሻል። ብዙ ገንዘብ ወጣ፣ እሷም ተሰቃየች… ምናባቴ ላድርጋት ይልሻል። ማዘንሽን በፊትሽ ታሳይውና ‹‹ምናለ የእኔም ባል እንዳንተ በሆነ›› ትያለሽ። አቅደሽ ያወጣሻቸው ቃላት ናቸው።
ቦይ እንደቀደድሽለት ይገባውና ስለባልሽ ንገሪኝ ይልሻል።
ስራ እንደሌለው፣ ህልም እንደሌለው፣ ገንዘብ እንደሌለው ትነግሪዋለሽ። በገንዘብ መጨቃጨቅ እንዳማረረሽ ታወሪዋለሽ። በዚህ እድሜሽ ለሽሮ በርበሬ-ለቤት ኪራይና ትራንስፖርት መጨነቅሽን ትነግሪዋለሽ።
ከወንበሩ ተነስቶ ወዳንቺ ይመጣል።
ትከሻሽን በማይቀፍ ሁኔታ ይዳብሳል።
‹‹ሴክስ ራሱ ካደረግን ቆይተናል›› ትያለሽ። አሁን አቅደሽ ያወጣሻቸው ቃላት ናቸው።
ከዚያ ግን ነውር እንደሰራሽ- የማይባል እንዳልሽ ታነሺና ‹‹ወይኔ ምን ነክቶኝ ነው ገመናዬን ምዘከዝክልህ ግን? ብለሽ ትሽኮረመሚያለሽ።
‹‹እንኳን ነገርሽኝ…ደስ ነው ያለኝ›› ብሎ ትከሻሽ ላይ የነበረውን ቀኝ እጁን ወደ አንገትሽ ይወስዳል።
ግንኙነታችሁ እንደዋዛ፣ እንዲህ ይጀመራል።
(ይቀጥላል)
One Comment
oh