…ሳጥናኤል ወ አጋንንት አስርቱ ትዛዛት..
ትእዛዝ ሶስት፦ እሄ ጦሙን እያደረ ፈጣሪውን ጥዋት ተነስቶ የሚያመሰግን ህዝብ ወደኔ ለማምጣት ብልሀተኛች ሁኑ።
ነፃ እናወጣችኋለን እያላችሁ ነፃ ሆነው እንዳይኖሩና ዘወትር ያልታሰሩበትን ገመድ ለመፍታት እረፍት አልባ ሂወት እንዲገፉ በማድረግ እረፍት ያገኙ ዘንድ ምግባረ እርኩሰትን እንዲፈፅሙ አድርጓቸው። ያኔ የፈጣሪያቸውን ጥበቃ ስለሚነፈጉ እንደበግ እየነዳችሁ ወደኔ ታመጧቸው ዘንድ ቀላል ይሆናል።
ትእዛዝ ፦አራት..እኔ ተሰሚነት እና ተቀባይነት ይኖራችሁ ዘንድ በምሰጠችሁ የርኩሰተ ጥበብ እየታገዛችሁ በመንፈሳዊና በስጋዊ ትምህርታቸው ደከም ያሉትን ወዳሉበት ተሰማሩ እያሳደዳችሁ ለጥሪያችሁ ቅርብ የሆኑትን መንፈሰ አጋንንት በመሳብና በመርጨት ለጥሜ ደማቸውን ለርሀቤ ስጋቸውን አቅርቡ የተመረጡትን ገብሩ።
ትእዛዝ አምስት፦ ግለ ችግር ያለባቸውን ችግራቸውን የምትቀርፉ መስላችሁ ቅረቧቸው። በትውልድ መሀል ችግር ለመፍጠርም ለችግሮቻቸው ደራሽ በመምሰልም የሚቀድማችሁ እይኑር ጉድለትና ችግሮቻቸው እወጥመድ መረባችሁ ውስጥ የምታስገቡበት ዋናው መሳሪያችሁ ይሁን።
ትእዛዝ ስድስት፦አይነ ልቦናቸው ሚስጥር ለመፈተሽ ያልበቃ ህፃናትን በእርዳታ ሰበብ እየመለመላችሁ የርኩሰት መንፈሴን ዝሩባቸው ያኔ አይነ ልቦናቸው ፈፅሞ በኔ የታወረ ይሆናል።
ጠንካሮቹ ደካሞቹን እንዳያበረቱ መደማመጥና መስማማት ይሳናቸው ዘንድ ልቦናቸው በኔ የታወሩትን ወስዳችሁ መሀላቸው በትኑ።
ትእዛዝ ሰባት፦ማንነቱን ያጣ ትውልድ ለማንም አይመለስምና ስራቸው ተነቅሎ እግሬ ስር ይወድቁ ዘንድ ስትጀምሩ ከመሰረቱ ይሁን።
የምትሏቸውን አምነው ይቀበሉ ዘንድ የነበራቸውንሁሉ አሷጧቸው።ከትንንሾቹ ከእድርእና ከእቁብ ጀምሮ እስከላይኛቹ ትልልቅ ድርጅቶች በብሄር ስም አደራጁ በብሄር ስም ተቋማትን ክፈቱ።
የጋራ ማንነታቸውን ለማጥፋት አንድ በሚያረጋቸው ሳይሆን በልዩነታቸው ላይ ጠንክራችሁ ስሩ።
ጥላቻን ዝሩ። ሰውን እንደንዋይ መንዝሩ። ወደ ጥፋት መንገድም ገፍትሩ።በምግባር አርኩሷቸው ያኔ ልቦናቸውን ለኔማደሪያ ይሆን ዘንድ ይከፍታሉ።
ትእዛዝስምንት፦የጥፋት ግዛቴንእኑሩ ግዜው ሲፈቅድ የምትገልጡትን መለያዬን በህቡ እመንገድ እንብሩ። በወጥመዴ ዳግምላይመለሱይገቡ ዘንድ የርኩሰት ማህተሜን በሚጠቀሙትነገር ሁሉም ስጥራዊ በሆነ መንገድ ቅበሩ።
ትእዛዝ ዘጠኝ፦ቤተ እምነቶች ላይ እጃችሁን አንሱ ለይታሁ አጥቁ ተለይታችሁ የተጠቃችሁም ምሰሉ
ትእዛዝ አስር፦በሚነበቡና በሚደመጡት ሁ ሉ ለይታችሁ አወድሱ ለይታችሁም አሳንስሱ።የታሪክ ስተትን በመጥቀስ ቂም በቀልን በመቀስቀስ ከዳር እስከዳር ይብዛ ብጥብጥና ትርምስ ።ትውልድ ከትውልድ ይናከስ።
ሳጥናኤል ወ አጋንንት በኢትዬጲያ ምድር ዘላለም ይንገስ። አሜን።
በፍርሀት መቆም ቢሳነይም አስርቱን ትዛዛት እንዳገባደድሁ ተዘንዶው በስተግራ ወዳለው ሌላ ዝርዝር ጥሁፍ ፊቴን መለስ ተማረጌ እዛ ተመሬት በታች ታለ ቤት ውስጥ ተየት እንደመጣ እንጃ ወደ ክፍሉ ንፋስ የመሰለ ነገር በፍጥነት ቲገባና ቀሚሴን ቲሰቅለው ደንግጬ ቀሚሴን ቁልቁል እየያዝሁ ወደ ጥሁፉ ፍቴን ትመለስ እመስታወቱ ውስጥ ያሉ መብራቶይ ጭጭጭጭ የሚል ድምጥ በማሰማት ተደረገሙ።
ምን ጉድ ነው ብዬ ቀና ተማየቴ የ የክፍሉም መብራት ጠፋና ጭለማ ወረሰይ። እየተደነባበርሁ ወደመውጫው ትሄድ ወደቅሁኝ ደጋግሜ የፈጣሪዬን ስም እያነሳሁ እጮህ ጀመር ተዛ ቡሀላ ማን ገፍትሮይ ያስወጣይ ቤት በኩል ልውጣ ታይታወቀይ እራሴን ተክፍሉ ውጪ አገኘሁት በልሁ እየጮኸ ይጣራል።
ግራ ቀይ የተወጠረበትን ገመድ ሊበጥስ እየታገለ “እህቴን ገደሉሽ!” እያለ ይጮኻል እኔን ዞሮ ማይት ትላልቻለ።
አይዞህ ወንድሜ ደና ነይ።ወይ ጉድ እሄ ነገር ተቤቱ መሰረት ጀምሮ ሆን ተብሎ ለዚሁ እርኩስ ተግባራቸው መዘጋየቱ ተአምር ሆነብይ በልሁ “ሰንዬ ኢትዬጲያ ውስጥ ተትምህርት ቤት በላይ እስር ቤት ተሰራተኛ በላይ እስረኛ በዝቷል የተባለው እኮ ህዝብ እውቅና ታይሰጣቸው እንደ እትዬ አይነቶቹ ጥቃቅንና አነስተኛ መንግስቶይ በየመንደሩ ተሽጠው ባላቸው ሀብት…
..ይቀጥላል