ቄራ ነው”። አለይ። እቤቱ ግድግዳ ላይ ተትንሿ ቢላ ዥምሮ እስከ ላይኛው ግዥራ ፣ተትንሿ መቀስ ዥምሮ እስተ ትልቁ የጥድ ማኸርከሚያው መቀስ ፣ ማዋለጃ የሚመስል ባለ ጎማ አልጋ፣ተበልሁ ጀርባ በስተቀኝ 2 ተከፋች የቀብር ሀውልቶይ ቲኖሩ በስተግራ ደሞ አንዱ ጥቁር መጋረዣና አንድ ቀይ መጋረዣ እበራቸው ላይ የተንጠለጠለ ክፍሎይ አሉ። እነኛ ጥቁር እና ቀይ መጋረዣ የተሰቀለባቸው ክፍሎይ ምንድን ናቸው በልሁ!? ” ሰንዬ እኔን በጥቁሩ መጋረዣ በኩልም አይደል ወይህ ያመጡይ” አለይ። እንዴት በልሁ በየት በኩል? ” አይ ሰንዬ እትዬ ምን ተማምነው ጥለውን የሄዱ ይመስልሻል ?እሄ ተዚህ ግቢ ጎን ያለው ግዙፍ ግቢ እትዬ ላሽከሮቻቸው የሰሩት ቤት ቲሆን ተመሬት በታች ውስጥ ለውስጥ ተዚህ ቤት ጋር ይገናኛል ያን ቀን ጋደም ባልሁበት በለሊት የትዬ ግቢ ከውጭ በቁልፍ ቲከፈት በመደናገጥ ማነው ብዬ ብድግ ተማለቴ እንኳን ተቅርብ ተሩቅ ለማየት የሚቸግር ፓውዛ አይኔ ላይ ቦግ አረጉብይ። አይኔ የጠፋ መሰለይ አይኔን ይዤ ወደ ምድር እያየሁ በህግ አምላህ ትላቸው ሁለት እጄን ጠርንፈው እየደበደቡ ቀጥሎ ወዳለው ጊቢ ወሰዱይ ተዛ ለአንደኛው ” ካሁን ቡሀላ ሁለቱንም ግቢ በትኩረት ተከታተል ” ብለው ትዛዝ በማስተላለፍ እኔን እየጎተቱ ወደ እቤቱ አስገቡይ ተዛ ውስጥ ለውስጥ ወዲህ እንዳመጡይ እትዬ ተላይ አንቺ ተመጣሽበት ቁልቁል ቲወርዱ አየኋቸው ተዛ ቡሀላማ ምኑን ልንገርሽ?። ቲለኝ ደርቄ ቀረሁ በሰማሁት ነገር የማምለጥ ተስፋዩ ቲማሽሽ ተሰማይ። በልሁ ይብሱን ተስፋ እንዳይቆርጥ እራሴን አበርትቼ እሺ ተጎኑ ያለው ቀይ መጋረዣ የተጋረደውስ ትለው “እሱስ ምን እንደሆነ እንጃ ” ልየው በልሁ?”ተይ ሰንዬ ይቅርብሽ!” ፈጣሪ ታለ ምህንያት ምንም ነገር አያደርግም ምናልባት እሄን ተአምር ለኔ የሚያሳየይ አንድ አላማ ቢኖረው ነው አልሁና በልሁን ተይ ቢለይም በቀስታ ወደ ክፍሉ ተጠጋሁ። መጋረዣውን ገለጥ ታረገው ተበልሁ ፊት ተነነብሱ የሚገላበጠው ዘንዶ እይህ ክፍል ውስጥ ቁመቱ ተኔ ቁመት በሚልቅ በመብራት ውስጡ ባጌጠ መሀሉ መስታወት ጠርዙ ወርቅ በሆነ ትልቅ ፍሬም ውስጥ ፎቶው ተቀምጧል። የክፍሉ ግድግዳ ዙርያውን አንድ አይን ባላቸው የተለያዩ የሴት እና የእባብ ፎቶዋች ተሞልቷል። ወደ ክፍሉ መሀል ገብቼ ትቆም በቁሜ እሰይጣናች አለቃ እሳጥናኤል ቤት ውስጥ ያለሁ መሰለይ። እመስታወቱ ውስጥ ተዘንዶው ፎቶ ግራ እና ቀኝ ፅሁፍ ስለተመለከትሁ ጠጋ አልሁና ማንበብ ጀመርሁ ተላይ በደማቁ እንደ ርእስ የሰፈረው..
መልእክተ ሳጥናኤል ወ አጋንንት አስርቱ ትዛዛት!
ይላል ወረድ ብሎ ደግሞ …ጠላቶቼ መፃፍ ቅድስ እና ቁራን ሲያነቡ ወዳጆቼ መፅሀፈ እርኩሰትን በመንፈስ አስነብባችሁ ዘንድ ቀጣዩቹን አስር ትዛዞቼን ፈፅሙ።ያኔ ምድራዊ ሀብት ሁሉ በእጃችሁ ይገባል። ይላል። ቀጠልሁ።ዝቅ ትል..
ትእዛዝ አንድ፦ በሀማኖቷ የጠነከረች ሀገረ ኢትዬጲያ ለዘመናት ፈትናኛለች ከአለም ትንሽ ተከታይ ያለኝ እዚች ሀገር ነውና ምድራዊ ግዛቴ ደም እንዳይጠማ በሰው ደም የሚያድጉ አትክልቶቼ በደም እጦት እንዳይጠወልጉ ከጥግ እስከ ጥግ ከመላ ምድሪቱ ለኔ የሚሰሩ ሰዎችን መልምሉ።
ትእዛዝ ሁለት፦ እዝነ ህሊናቸው ማድመጥ የተሳነው ሰዎች ሲበዙ በምድር የሰዎች ፍጭት እና ሞት ይበዛልና የእልቂት መንገዶቼን ከላይ ማር እየለወሳችሁ አብላቸው ሰውን ወደ እንስሳነት የምቀይርበት መንገዶቼን ተጠቅማችሁ ለዘር ተቆርቋሪ መስላችሁ በዘር አጫርሷቸው። ለሀይማኖታችሁ እስከሞት ድረስ የቆማችሁ በመምሰል በሀይማኖት አባሏቸው።ለትውልድ መንደራችሁ ተቆርቃሪ ተሟጋች መስላችሁ ለመፍትሄው ጠላቴ ሰላምን ሳይሆን ግብረ ነግሬን ተጠቅማችሁ በጥፋት መንገድ አጋድሏቸው።
የቆምሁባቸው እግሮቼ ቲንቀጠቀጡ ታወቀይ እዚህ ላይ የተጣፈው ትዛዝ በተለቭዥኑ ታየሁት የሀገሬ ምጥ ጋር አንድ ትለሆነብይ እስከመቼ ነው ዝም ብለህ የምታየን ብዬ እየጮሁ ሽቅብ ተንሰቀሰቅሁ።በልሁም ድምጤን ሰምቶ ምን ሆንሽብይ እያለ ማልቀስ ቲጀምር አይ ምንም አልሁና እንባየን ጠርጌ ቀጠልሁ..
ትእዛዝ ሶስት…
ይቀጥላል