ጋሼ ከታሰሩ ቡሀላ የትዬ ነገረስራ ሁሉ ያስፈራል ያስጨንቃል አሁን ለታ ለስንት አመት ግድግዳው ላይ የተሰቀለው ሰአት የለመደውን ቆጠራ ቀጥሏል ቃ….ቃ……ቃ…. ቃ ይላል ወድያው እትየ ተፈዘዙበት አለም ተመለሱና ” እሄ የግድግዳ ሰአት ድምፁ ሊያሳብደኝ ነው አውርጄ ሳልከሰክሰው አውርጂና አጥፊልኝ! አሉኝ የጆሮዬ ታንቡር እስቲላቀቅ እያምባረቁብኝ።የታዘዝኩትን ፈፀምኩ።
“እሄውልሽ እህት አለም ሰንዬ”
ወዬ በልሁ…
“ወጣም ወረደም እንደወንድምነቴ የምመክርሽ አሰናብቱኝ የሚል ቃል ታፍሽ እንዳይወጣ ነው”
እኔ እንጃ በልሁ እኔ በጣም ከብዶኛል የሳቸው ሁኔታ የቤቱ ጭር ማለት ብቻ…
“ደሞ ቤቱ ምን ሆኖ ነው ጭር ያለው ጋሼ ስለታሰሩ ማለትሽ ነው?”
ኧረ ምን የጋሼ መታሰር እትዬ ምን ያህል ሚድያ መከታተል ይወዱ እንደነበረ ታውቃለህ?እንዲያ በተለቀቀ ዘፈን ሁሉ ተነስቼ ካልጨፈርኩ እንዳላሉ ሌላው ቢቀር አንተን እንኳን ስንቴ ነው ና ያገርህ ዘፈን መጣ እያሉ በስክስታ ሲንጡህ የከረሙት አሁን ድምጡንም ምስሉንም ላይናቸው ጠሉት እንደው ይገርማል እኮ ቁጭ ብለን በሰላም ፕሮግራም እየተከታተልን ብቻ ዜና እንደጀመረ ድንገት ልውጥውጥ አሉልህና ጆሮአቸውን በሁለት እጃቸው ግጥም አርገው “የዚህን ቴሌቪዥን ድምጥ መስማት ጨርቄን ሊያስጥለኝ ነው ተነሽ አጠፋፊና ነቃቅለሽ እዛው ካርቶኑ ውስጥ አስገቢልኝ ፡ ደነገጥኩ…
እንዴ እትዬ የምሮን ነው ስላቸው አፈጠጡብኝ እንዳሉት አደረኩ ታድያ እስተመቼ በዚህ ሁኔታ ዘልቀዋለሁ
“አሁንም እደግመዋለሁ ሰንዬ ምንም ይሁን ምን አርፈሽ መቀመጡ ነው ላንቺ ሚበጀው..እስካሁን እምልሽን ካላመንሽኝ አንድ ነገር ልንገርሽ …ልጅቱ እዚህ ቤት ተቀጥራ ስትሰራ እንዳንችው ትቀርበኝ ነበር ድህነትን መልክ ቢያሸንፈው በሳ በተሸነፈ ነበር ምን ዋጋ አለው ልትወጣ እንደሆነ መጥታ ስትነግረኝ ተይ ይቅርብሽ አልኳት በጄ አላለችም። ልቀቁኝ ልሂድ አለቻቸው ።
ከአንድ ቀን ቡሀላ ለቀቀች ተባልኩ ተሶስት ቀን ቡሀላ ለትዬ ሶኬት ላበጅ ወደ ትልቁ ቤት ገባሁ እትዬ ሰው ሊሸኙ ወጣ እንዳሉ ምን እንደመራኝ እንጃ ዘው ብዬ ተልጅቱ ማደርያ ስዘልቅ አንድ አፉ የታሰረ ነጭ ማዳበርያ ጥግ ላይ ቆሞ ተመለከትኩ ጠጋ ብዬ ቋጦሮውን ትፈታው ወጣች የተባለችው ልጅ ልብስ እና ጫማ ነው ። ጠላትሽ ክው ይበል ክው ብዬ ቀረሁ እሄው እስተዛሬ አእምሮዬም ጤነኛ አይመስለኝም” ሲለኝ ። በድንጋጤ ይሁን በፍርሀት ካጠገቡ ተፈናጥሬ ምንም መልስ ሳልሰጠው ወደ ቤት ስመለስ ” አደራ ሰንዬ ያወገነው በኔና ባንቺ ይቅር ” አለኝ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ እራሴን መሆን ተሳነኝ
ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ ወደ ዋናው ቤት ስዘልቅ ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ የጣላቸው እትዬ አሁንም አልተነሱም ወደ ክፍሌ ገብቼ አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩና ከዚህ ቤት የምጠፋበትን መንገድ ማስላት ጀመርኩ።
አረፋ አረፋፍደው የተነሱት እትዬ ፊታቸው የተዝረከረከ ማድቤት መስሏል። ተጣጥበው እስቲወጡ ቁርስ አቀረብኩ ከመተጣጠቢያ ቤት ሲወጡ ወደ ቤት መግቢያውን ዋናውን በር ከውስጥ ቆለፉና ቁርሳቸውን ከጠረጴዛው አንስተው በጃቸው እንደያዙ ፈንጠር በሏ እተቀመጠችው ሶፋ ላይ ተቀመጡ።
ሁለት ጉርሻ እንደጎረሱ ተግቢ ውጪ የመሂና ክላክስ ሰሙና ተነምግባቸው ተነስተው የመስኮቱን መጋረጃ በመግለጥ ወደ ግቢው ከተም በሪ ሲያጮልቁ ድንገት አጠገባቸው ያለው የቤት ስልክ ጮኊባቸው በስልኩ ደንግጠው ሰሀኑ ከነምግቡ ከእጃቸው ላይ ወደቀ ተንደርድረው አጠገቤ ደረሱ።
ተፋጠጥን ቃል ማውጣት ተሳናቸው መሰል በአንገት ምልክት ስልኩን እንዳነሳው አዘዙኝ አነሳሁ …ሀሎ…ሀሎ..
ይቀጥላል