Tidarfelagi.com

“እኔ ምን ሀብት አለኝ!? ሀብቴ የኢትዮጲያ ህዝብ ነው!”

“እኔ ምን ሀብት አለኝ!? ሀብቴ የኢትዮጲያ ህዝብ ነው!” የሚሎውን ኒጊጊር ከራዲዮ ዲንገት ስሰማ ተናጋሪዋ ያው አስቴር አወቀ ወይም አንዷ ቺስታ አርቲስት መስላኝ ነበር….ጪራሽ አንቺ ናሽ! ኢሱን ሲትገረፊ ታወጪዋለሽ! ….ዲምጹን ጨምሬ በጉጉት መስማት ቀጠልኳ….ያለሚኒም ሃፍረት አይኗንን ፊጢጥ አድርጋ ጀለሴ ቤሳቤስቲን የለኝም ብላ አረፈችው…(አቤት ግነት!አሁን በራዲዮ እየሰማ እንዴት ነው አይኗን ማፍጠጧን ያወቀው?!)….ሚን አይነት ቀዳዳ አርቲስት ናት ባየሱስ !ውሸት ስልችት ሲለኝ በኒዴት ራዶኔን ወደ ዛሚ ሲቀይረው ኢዛ ደግሞ ወ/ሮ አዜብ ስለተለያዩ ነገሮች እየተጠየቑ ነው)……
በል ቶማስ በቃህ!ስለ አርቲስቷ አንተ አወራህ ! ስለ ወ/ሮ አዜብ ቃለመጠይቅ ደግሞ እኔ ላውራላቸው….

እሺ ጋይስ ሰላም ናችሁ !?
ያው ቅዳሜም አይደል…እስቲ ገብስ ገብሱን እንጨዋወት።
ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ(ዛሚ) ከሰሞኑ በፌስቡክ የተፈጠረውን የወሬ እጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሟቹን ጠቅላይ ሚስት ቃለ መጠይቅ አድርገው ስስ ብልታቸውን የሚነካ ነገር አንስተው(“ስስ ብልት” የሚለው በፈሊጣዊ ጎኑ ይነበብ) “እንኩ የአዜብን ስጋ እንዳሻችሁ ዘልዝሏት” ብለው ከዋሻችን በር ላይ ጥለውልናል….አውውው…..ሃሃሃ…

ግን ወ/ሮ ሚሚ ከመጀመሪያው ወ/ሮ አዜብን ለምን ይሄን ጥያቄ መጠየቅ ፈለጉ?! ሰሞኑን ወ/ሮ ሮማን “”አበባዮሽ ብለው ካተረፉት ህዝባዊ ቅቡልነት(አንጻራዊ) እኚኛዋን ለማጠጋጋት በእልህ ተነሳስተው ይሆን!?
ወ/ሮ ሚሚ፡…”.ወ/ሮ አዜብ ድሃውን የኢትጲያን ህዝብ ግጠውታል ይባላል…እጅግ ከፍተኛ ሀብትም ቀግረዋል እየተባለ ይወራል እውነት ነው ?”(ቃል በቃል አይደለም )

ወ/ሮ አዜብ…..”አረ በናትሽ ሚሚዬ በስመአብ በይ!..ሆ….ሆ! እኔ ድንቡሎ አልነካሁም!..ዋአይ !ምን አይነት ወሬኛ ህዝብ ነው በናታችሁ! አንዳንዴ ሰው “አዜብ” ሲባል ያው ቤተመንግስትም ስለነበርኩ ነው መሰለኝ ከንግስት አዜብ(ማክዳ/ሳባ) ጋር የተምታታሁበት ይመስለኛል! እሷ ነች(ሳባን መሆኑ ነው) የሀገር ወርቅ አስጭና እስራኤል ሄዳ ዲቃላዋን ጭና የተመለሰችው .!.እኔ ለራሴ ቤሳቤስቲን የሌለኝ መናጢ ነኝ! አሁን ራሱ ስታዋሪኝ ኪሴ ውስጥ ሶስት መቶ ብር ብቻ ነው ያለው…እንደምታውቂው ደሞዝ ከወጣ 12 ቀን አልፎት የለ?!በዛ ላይ የበአል ወር ነው ያሳለፍነው…አሂሂሂ ተይኝ እስቲ ……(ይሄም ቃል በቃል አይደለም)

የዋሁ የኢትዮጲያ ህዝብ የጠበቀው መልስ፡ ….”አዎ ሚሚዬ ቀላል ግጨዋለሁ እንዴ !?….” ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” አይደል የሚባለው ከነተረቱስ።ይገርምሻል ስዊዝ ባንክ 2ቢሊዮን ….ማነው ይሄ ሲቲ ባንክ ደግሞ 1 ቢሊዬን ዩሮ እንዳቅሚቲ ጣል አድርጌአለሁ።በነገራችን ላይ እንትን ሞል የእኔ ነው..እንትን ፋብሪካ ደግሞ ከዛ ጉራጌው ጋር በሽርክ ነው የምንሰራው…ያ ደግሞ እንትን ኮንስትራክሽንም 90 ፐርሰንት ሼር የኔ ነው….እኛ ነን የህዳሴ ግድብን ግብአት ማቅረቡን ቀጥ አድርገን የያዝነው …..እንትን ውሃም የእኔ ነው… እንትን ሚጥሚጣ… እንትን ባጀጅ…..አሜሪካ የሚላከው እንትን እንጀራ…..እንትና የጀበና ቡና …እንትና አስመጪ …እንትና ላኪ ም የእኔ ነው….ከሳባዊ ጋር ራሱ ሼር ነን(ሎል)…” .እንዲሉ ጠብቆ ነበር። ይሄ የዋህ ህዝብ አንዳንዴ ደስ ይለኛል።

የድሮ ቃለመጠይቅ
ጋዜጠኛ ገነት፡ “ጓድ መንግስቱ ከ1968 እስከ 1972 ድረስ ባሉት ጊዜያት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ኢሃፓ፡ አናርኪስት፡ ቀልባሽ፡… ወዘተ እያሉ አስፈጅተዋል ይባላል።እውነት ነው?”
ጓድ መንግስቱ፡….” በጣም የሚገርም ወሬ ነው!እውነቴን ነው የምልሽ ገንዬ አንዳንዴ እንዲህ አይነት ነገሮች ስሰማ ብግን ነው የምለው! ማንም እንደሚያውቀው እኔ በባህርዬ ዝንብ እንኳን ብታርፍብኝ ላለመጉዳት ጭራ ራሱ አልጠቀምም..ዝምቧ ቀስ ብላ ተነስታ በራሷ ግዜ እንድትበር ነው እድሉን የማመቻችላት!በወቅቱ በእርግጥ ብዙ ወጣት ሞቷል… ግን ይህ በኮሌራም ሆነ በተስቦ ሊከሰት እንደሚችል ታሳቢ ማድረግ አለብሽ!”(ያው ይሄም ቃል በቃል አይደለም)
የዋሁ የኢትዮጲያ ህዝብ የጠበቀው፡” ኦው !እውነት ነው! ቀላል ጨፍጭፌዋለሁ እንዴ!…..ቁጥሩ እንደውም እንደሚገለጸው አይደለም! ይበልጣል ባይ ነኝ!…ይገርምሻል ይሄንን አበያ ወጣት እንደጎመን ነው ያጨድኩት!…ብዙ ደም ፈሷል..በቃ ምን አለፋሽ በአጭሩ ቫምፓየር በይኝ!”
በነገራችን ላይ ወ/ሮ አዜብ ላይ ለአመታት ጣት ተቀሰሯል…”የሚመለከተው አካል አንድ ግዜ እንኳን የማጣራት ስራ ሰርቶ ይሆን?” እላለሁ። አንዳንድ ደነዝ ኮካዎችም “አዜብ ሌባ !አዜብ ሙሰኛ! አትበሉ !ማስረጃ ካላችሁ አሳዩን” ሲሉ እያየን ነው….አንዳንዴ ግርም ይለኛል…..ከየት ነው ማስረጃ ምናቀርበው….!? ዊ ጀስት ፊል ዛት ሺ ኢዝ ኮራፕትድ …ናው ኢት ኢዝ አፕ ቱ ዘ አውቶሪቲ ቱ ኢንቨስቲጌት ፈርዘር…..ዋይ ዱ ዩ አስክ አስ ቱ ኢንጌጅ ኦን é ሱሳይዳል ሚሽን?!.”…ኦው !ለኮካዎች ነው ለካ የጻፍኩት… ጀለሶች ተርጉሙላቸው!ሎል….አንድ የጋምቤላ ተረት ትዝ አለኝ(ጋምቤላም ይድረሰው)…አንዴ የሆኑ የአይጦችን ግሩፕ አንድ ድመት እየለቀመ አስቸገራቸው አሉ።.ከዛ “እንዴት ይሄን ድመት መቆጣጠር እንችላለን?” የሚለውን ለመወያየት በዛውም ጥልቅ ተሃድሶ ለማድረግ ብለው ስብሰባ ዱቅ አሉ።ያው በተለመደው የጥልቅ ተሃድሶ ስርአት አንዱን አይጥ በሌላ አይጥ ቦታ ቀያየሩ፤ ምናምን፤ ከዛም ዋናውን ችግራቸውን በተመለከተ..የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦች መሰንዘር ጀመሩ…አንድ መለኛ አይጥ ተነሳና “እኔ የማስበው ዘዴ አለ…ወገኖቼ! ይሄ ድመት ከሌሎቹ የመደብ ጠላቶቻችን ለየት ባለ ሁኔታ እያጠቃን ያለው …ወደ ኛ ሲመጣ ፈጽሞ ኮቴው የማይሰማ በመሆኑ ነው…ስለዚህ አንገቱ ላይ ቃጭል እንሰርለት..ከዛ ሲመጣ ከሩቅ ይሰማናል!” አለ…..ባመጣው ዘዴ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተቀወጠለት…አይ ጭንቅላት! ምን አይነት “ወርልድ ክላስ ማይንድ ነው ያለህ ?” ተባለ… “አንተማ የሆነ የዴሊቨሪ ዩኒት ክላስተር አስተባባሪ መሆን አለብህ” ሁላ ተባለ…..አንድ ሼባ አስተዋይ አይጥ ግን ቀስ ብለው እየተንቋቁ ተነሱ….”ኦገኖቼ ሀሳባችሁ ጥሩ ነው!…ግን ከኛ ውስጥ ማን ጀግና ነው የድመቱ አንገት ላይ ቃጭሉን የሚያስረው!?…” ውይ…..ያ ሁሉ ደስታ ውሃ በላው!…..
ማነህ ጀለሴ “ስለአዜብ ስታወሩ ማስረጃ አያይዙ” ያልከው……ይሄ የ”ጋምቤላ” ተረት እና የአንተ ፖስት እንዴት እንደሚገናኙ እስከሚገባህ ድረስ እኛ ወደ ሌላ ጫዋታ እንሂዳ !?..ከቻልክ ድረስብን።
የበቀደሙን የወ/ሮ ሚሚ እና የወ/ሮ አዜብን ቃለ መጠይቅ ስሰማ ወ/ሮ አዜብ “አለሽ የተባልኩትን ሃብት የኢትዮጲያ ህዝብ ይረከበኝ!” ሲሉ እንዴት ሰፍ እንዳልኩ አትጠይቁኝ ….በቃ ጂቲፒ ሁለት ሊሳካ ነው ማለት ነው!? መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው ሀገራት ተርታ እንዲህ እንደዋዛ ገባን ማለት ነው !?…እንባ ቅርር እያለኝ በደስታ ስንሳፈፍ… “ግን ምንም የለኝም” ብለው ወሽመጤን በጠሱኝ።”አቦ ሙድ ትይዛለች እንዴ!ደሞዝ ብቻ ነው ያለኝ!? በቃ እሺ እሱንም ቢሆን አምጪው!” የሚል ስድ አይጠፋም መቼም! ሎል የወይዘሮዋ መልስና እና የወ/ሮ ሚሚ አጠያየቅ የባለቅኔውን የነጋድራስ ተሰማ እሸቴን ቆየት ያሉ ሁለት ቅኔዎች ነው ያስታወሰኝ….
“በኔ ለምንድነው የሚፈርደው ሰው
እጅ እግሬ ተቆርጦ “ማ ጣቴን” ሲያውቀው
ሃሃሃ ቅኔውን የምትችሉ ለማይችሉ ፍቱላቸው። ለወ/ሮ ሚሚ ስባሀቱም ጥያቄንም ከነጋድራስ ቅኔ እንዋስና ጨዋታችንን እንቋጭ
“እርስዎ የውጭውን በሩን ይዘጉታል
ሰው ሁሉ እቤቱን ውስጥ ውስጡን “ከፍቶታል” ”
በተረፈ ይመቻችሁ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...