የሰው ልጅ ትልቅ ሃይማኖት የመፍጠር ፎንቃ ያለው፣ሃይማኖታዊ ፍጡር ነው።እንደውም ሰውን ከእንስሳ የሚለየው ሃይማኖት ነው። ማሰቡ እንዳንል፣ጭንቅላቱን ለኮፍያ ማስቀመጫ ብቻ የሚያውል፣ ለሂውማን ሄሯ ማደላደያ የምታውል አይጠፉም። ግምቱን ነው።
እንደ ፍሮይድ ሳይንስ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሃይማኖትን ይተካዋል የሚል ግብ አይመቴ መላምት አልሰጥም።ሰው ሃይማኖተኛ ፍጡር ነው።በሱ ቅር አይለንም። ተዉ ቢሉትም ያጠብቀዋል እንጂ አይለቅም።እኛም እሱን ተፋተናል።
አሁን አሁን ችግሩ ያለው ሃይማኖተኝነት ላይ አይመስለኝም። ፈጣሪ የተባለው አካል አረዳድ ላይ ነው።የትኛውም ሃይማኖት ላይ ዘልቀህ ብትገባ አማልክት የተባሉት ተራ የሰው ልጅ ድርጊት የሚያስጨንቃቸው፣ ሽራፊ ስህተቶች የሚያስነቅሏቸው፣ መጠነኛ በጎነት የሚያስደስታቸው ናቸው።
የሙሉ ጊዜ ስራቸው የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ታዳሚ ሆነው የተሳሉ ናቸው። በመጨረሻ ዱላ እና ሽልማታቸውን ይዘው ይመጣሉ።ያጠፋውን ወደ ሲኦል፣ በ«ፅድቅ» ደጃፍ የተመላለሰውን ጀነት ይሸልሙታል።
በተለያየ ሃይማኖት ውስጥ ያየኋቸው ፈጣሪዎች የሚከተሉት ያመሳስሏቸዋል።( ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን ከመጥቀስ ተቆጥበናል ሃሃሃ)
1) ፍፁም ጭካኔ፣ፍፁም ምህረት
ስህተት ሰርተህ ሲያጠፉህ፣በቁምህ በእሳት ቢያነዱህ ቅም አይላቸውም።ዘላለም እሳት ውስጥ ሊያቃጥሉህ ፍቃደኛ ናቸው።ካንተ የሚጠበቀው ሰፍረው ካስቀመጧት ትእዛዝ ብቻ ሸውረር ማለት ነው።
በዛው ልክ ፍፁም መሃሪ ናቸው ትባላለህ። ሁለቱን ባህሪ እንዴት አጣጥመው በፍቅር እንደሚያስጉዙ እንጃ! ፍፁምነት ማለት አንዱም ይሄ ይመስላል። ዘይትና ውሃህን አዋህደው ማዝገም 🙂 ፍፁም ቸር ግን ሲኦል በሰዎች አጥንት ማገዶነት ሲነድ የሚኖር መቅጫ ቦታ እንደሆነ ሲነግሩህ ቅር የማይላቸው ዓይነት። እውነት ነው፣ፍፅምና ይጠይቃል።
2) የሙሉ ጊዜ ትኩረታቸው ሰው ነው።
ከሰው ውጪ ትኩረት ያላቸው፣የራሳቸው ህይወት ያላቸው አይመስልም።They are obliged to hover over human matters,humanly. poor Gods 😉 ቢቆጡ በሰው ወይ ለሰው ነው። ሚናቸው፣ ለሚገባው ህይወትን ማቅለል፣ለጠገበው ደሞ ከመርግ ድንጋይ ማክበድ ነው።ከክርስቶስ ልደት ብዙ ዓመታት በፊት ኢፒኩረስ የተባለ ሰው፣ «አማላክት የራሳቸው ህይወትና ፍላጎት አላቸው።በሰው ተራ ፍላጎት ዙሪያ ሲጨነቁ አይኖሩም» ብሎ ነበር። ወይም ብሏል ተብለናል። የሰማው የለም ማለት ይቀላል።
3) አምጡ ባይ ናቸው።ለድርጊታቸው ምላሽ ይሻሉ።
ፈጠሩ ይባልና፣ ለመፍጠራቸው ውለታ የእድሜ ዘመን ተንበርካኪ፣ ለቁጣ ምላሻቸው ተብረክራኪ ይሻሉ። ምስጋና፣አምልኮ፣እድሜህን፣አገልግሎትህን ብትሰጣቸው ይወዳሉ።ይህን ካልሰጠህ አትወደድም። ምንም አታገኝም። የእነሱ ልጅ አይደለህም።መስዋእት ይፈልጋሉ።ገንዘብ ይፈልጋሉ። እንደ ደላላ ላሳለጡት አገልግሎት፣የሚጠብቁት አለ።
4) የትኞቹም ላለህ የአዕምሮ ንቃት አይሸልሙህም።
ለመታዘዝህ እና ለመንበርከክህ እንጂ ዊዝደም ምናምን ብትል ውደም ብለው ነው የሚያባሩህ። ከሰው ልጅ ጥበብ፣የፈጣሪ ሞኝነት ይበልጣል ይሉሃል ሲሻቸው። ዌል ሞኝነት እንዳላቸውም ማወቅ ደግ ነው ሃሃሃ
ሌሎች ብዙ ባህሪያትም አንድ ያደርጓቸዋል። “ለምን አንድ ሆኑ?”ካሉን የሰው ልጅ ኤክስፒሪያንስ ውጤት ስለሆኑ በሚለው የዊልያም ጀምስ ሃሳብ ተስማሚ ነን።
። ።
ከዚህ የተሻለ አምላክ ቢኖረው የሚጠላ ያለ አይመስለኝም። ከቀጪነቱ ይልቅ አስተማሪነቱ፣ ከወየውላችሁ ይልቅ ወይ ባይነቱን የሚጠላ አይኖርም።
በእሳት አነድሃለሁ ከማለት ይልቅ፣«ስትስት በመልካም መንገድ እነዳሃለው» የሚል አምላክ ይበልጥ ራሽናል ነው።
እናንተ ለኔ የተመረጣችሁ ህዝቦች ናችሁ ብሎ በራንደም ሳምፕሊንግ ከሚመርጥ አምላክ ይልቅ፣ ሁሉን በእኩል የሚያይ፣በእኩል የሚያፈቅር አምላክ ተናፋቂ ነው።ስታደርግ ጠብቆ «አታድርግ ያልኩህን አደረክ» ብሎ ጥፋ ከፊቴ፣ውጣ ከቤቴ የሚልን ሳይሆን፣ መሳሳትህን የሚያቀና አምላክ ነበር አስፈላጊው። ማውቅህን የሚያተጋ። ፍለጋህን የሚያነጋ ነበር መሆን የነበረበት።«ቃሉን ጣስኩ» በሚል ፀፀት የሚያነድህ ሳይሆን፣በፍቅር የሚያለመልምህ አምላክ ነበር ዋናው።ችግሩ ገበያው ላይ ያን ዓይነት አምላክ ብቅ አይልም። ትንሽ አምላክ የቸገረው ምእመን ብናገኝ የምንሰጠው አምላክ እንዲህ አይነት ነበር። ሰዉ ከየት ይምጣ፣ በተሳሳተው መንገድ ጠፋ 🙂
4 Comments
Ere alen, gebeyawun becha tekom argen enji tegteltelen enemetalen,…
ከሰው ልጅ ጥበብ፣የፈጣሪ ሞኝነት ይበልጣል ሳይሆን የሰው ልጅ ትልቅ ጥበብ ለፈጣሪ እንደሞኝነት ነው የሚባለው ፡፡ ደሞ የሰው ልጅ ራሱ ነው በራሱ ላይ እሳት የሚጭረው ራሱን በራሱ ነው ለሞት እንዲመጭ የሚያረገዉ
ሳይህ የተበከልህ ትመስለኛለህ?በዚህ ትንሽ አእምሮህ ፈጣሪ መተቸት ጀመርህ? አስተካክለህ እንድታስብበት ነው ያተፈጠረልህ?
ፍልስፍናህ ወንዝ ባያሻግርም እንደ ኢትዮጵያዊው ዘርዓ ያዕቆብ ቢሆን ይመረጣል።አደራህ እንደ ውሾቹ ፍራንሲስ ቤከን ሁነህ ሀገርህን እንዳትነክስ
በተረፈ ቀጥልበት።