እስቲ አንድ ጊዜ ከታች ያለውን ምስል በትኩረት ተመልከቱት ጓዶች ! ቦንብ ነው! ቦንብ ምንድን ነው? ዊክፒዲያ ቦንብ? << በቅጽበት በውስጡ በሚፈጠር ኢነርጅ በዙሪያው ባለው አካባቢ ላይ ጭስ፣ ጨረር፣ ከፍተኛ ሙቀት፣ ተቀጣጣይ ነገር ወይም ተፈነጣጣሪ ጠጣር ነገሮች በመርጭት ውድመት የሚያስከትል የጦር መሳሪያ ሲል ይተነትነዋል!! እኔ ግን ከቅዳሜ ጀምሮ ሰለቦንብ ሳሰብ የተለየ ሃሳብ በለጭ አለብኝ ! እንድናገር ይፈቀድልኝ ? አመሰግናልሁ!
ቦ ን ብ በተለይም ምስሉን ከታች የምተመለከቱት ቦንብ የሞት ሳይሆነ የኢትዮጲያ ምሳሌ ይመስለኛል! ተመልከቱት አሰራሩን የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች ተገጣጥመውና ተያይዘው የፈጠሩት አስፈሪ መሳሪያ ነው ! ብረቶቹ የራሳቸው ጠንካሬና ቅርጽ ቀለምና ማንነት(ምንነት) አላችው! ይሁንና በራሳቸው የብረት ቁራጭ በጋራ ግን ማንንም የሚያርዱ ፣ ዝም ቢሉ ጥላትን ሰርዓት የሚያስይዙ ቢፈነዱ መሬት ይሚያርዱ በበጎም በክፉም ክንዳቸው የበረታ እምቅ ሃይል!!
ለምሳሌ አንድ ክፉ ሰው አንዷን የብረት ቁራጭ ብቻ ይዞ መስቀል አደባባይ ቢሄድና <<ይሄን ህዝብ በዚች የብረት ቁራጭ ጭጭ አደርገዋለሁ ዘራፍ>> ቢል ህዝቡን በፍንዳታ ሳይሆን በሳቅ ይገድለዋል! ቦንቡን ይዞ ዘራፍ ቢልስ ? ባይልም እንደው ይዞ ቢገኝ? ማንም ሊስቅ እና ሊያላገጥ አይችልም ! ብረቶቹ ብረት በቻ አይደሉማ!! እንደዛ ነው የአንድነት ሃይል !!!
ጓዶች ቦንብ ዝም ብሎ የማይፈነዳው በውስጡ ለፍንዳታ በቂ የሆነ ኬሚካል ሰለሌለ አይደለም !! እነዚህን የብረት ቁረጥራጮች እንዲህ በአንድ ላይ ያቆማችው ቦንቡ ውስጥ ያለው ኬሚካል በሰላም ሰለተቀመጠ ነው! ሰላሙ ከላይ በምታዩት ቀለበት የሰላም ቃልኪዳን ታሰሯል! ቀለበቱ ሰላም እስከሆነ ድረስ ቀለበቱን ማንም ነቅሎ እስካልወረወረው ድረስ ፣ቀለበቱን ደሙ በጥላች የፈላ ወይም የቀለበቱ መነቀል ምን እንደሚያስከትል ያልገባው እሰካልነቀለው ድረስ ቦንቡ ውስጥ ምንም አይነት አፍራሽ ሪአክሽን አይኖርም፣ እሳት አይጫርም ፣አንድነቱን ይሚበታትን ሃይል ከውስጥ ወደውጭ አይገፋም!! ብረቶቹም ጠላት እንደፈራቸው ወዳጅም እንደታመነባቸው ቦንብ እንደሆኑ ይቆያሉ!!
አገርም እንዲሁ ነው! በተለያዩ ህዝቦች አንድነት ተመስርተን የምንታፈር የምንፈራ ሉዓላዊ አገር ሉዓላዊ ህዝቦች ነን!! የፍቅር ቃልኪዳናችን እንደቦንቡ ቀለበት ሁሉ ፍቅራችን ነው ፣መከባበራችን ነው! እኩልነት ነው! ያልተበታተነው የምንበታተንበት ምክንያት በውስጣችን ሰላልነበረ ዓይደለም ! የአንድነት ቀለበታችን በውጭም በውስጥም ሃይል ሰላልተነቀለ የሚበታትነን የዘር ፣የሐይማኖት እና ወዘተ ኬሚካል ሪአክት እንዲያደርግ ሰላልፈቀድንለት ነበር!! አያችሁ ቦንብ በህጻን እጅ ከገባ ቀለበቱን መጫዋቻ መስሎት ሊነቅለው ይችላል ለዛ ነው ሰልጣንም የበሰለ ሰው ይሚሻው!! ቦምብ በጀብደኛ እጅ ከገባ በጀብዱ ቀለበቱን ነቅሎ ጠፋት ይሆናል ! ለዛ ነው ስልጣን ለጀብደኛ ሊሰጥ የማይገባው ! ሰልጣን ማለት ይችን ቀለበት በከፊለም ሆነ በሙሉ ሳይነቀል ውስጥ ያለው በሁኔታዎች የተፈጠረው አጥፊ ሰው ሰራሽ ልዩነት ወደፍጹም አንድነት እንዲመጣ ለሚተጋ መሪ ቀለበቱን አደራ ብሎ ውክልና መስጠት ነው!!
ይህ ቀለበት በመናናቅ በራስ ወዳድነት በማን አለብኘነትንና ስግብግብነት የተነቀለ ቀን ውስጣችን ጥላቻ ሪአክት ያደርጋል ! ጥላቻ ደግሞ ማንንም አንድ አያደርግም !! የጥላቻ ሃይል ፍንዳታ የሚፈጥር ኔጌቲቭ ኢነርጅ ነው! ባለፈው ቅዳሜ የፈነዳውን ቦንብ ዛሬ ላይ ማንም እንደማይፈራው ሁሉ እንደአገር ከተበታተንን ከተለያየን በኋላ ማንም አይፈራንም አያከብረንም እንኳን ለሌላ ለራሳችን እንስ ያልን <<ነበር>> እንሆናለን! አንዴ የፈነዳን ቦንብ ማንም አይፈራውምና!!
4 Comments
ግሩም ነው ! ኢትዮጲያዊነት በፍቅር ሲፈነዳ እንደ አደይ አበባ የሚያምር ከራሱ ተርፎ ምድሩን ሁሉ የሚያስጌጥ እንጂ እንደ ቦንብ በጥላቻ ፈንድቶ አካባቢውን ሁሉ የሚያጠፋ… እራሱ ቀድሞ ፈራርሶ ሌሎችን የሚጎዳ …ከአንድ ጊዜ ፍንዳታ በኋላ ግን ማንም ቁርጥራጩን እያነሳ የሚጫወትበት ተራ ብረት እንዳይሆን … ተግተን ለመስራት ጊዜው አሁን ነው !!!
Alex have you lost some new issues beyond this contemporary cliche?
Hello, Jemaludin I’m not understand what u are talking and thinking about , pleas make it brief ?
አቦምሳ