Tidarfelagi.com

አንዳንዴ

ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮን ባቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ፤

እስከመቼ ድረስ
ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት

ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ
እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ።

አይሰለቺህም ወይ
መኖር በተጠንቀቅ
አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ ፤ በግንባርህ ውደቅ
አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
ርካህብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ ወድቆ ከመነሳት!

በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤ በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጉዋሙን ልቀቀው!

Bewketu Seyoum (Ge’ez: በዕውቀቱ ስዩም) is an Ethiopian writer and poet from Mankusa, northwest of Addis Ababa.

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...