Tidarfelagi.com

አለቃ ታዬ

One of the first Black African Scholar who taught at Western/European University – Aleqa Taye Gebre-Mariam (1861–1924)

Aleqa Taye was a lecturer at Berlin University. He taught Amharic and Geez. Born in Begemidir, Ethiopia in 1861, he was educated at a Swedish mission school. He has authored countless dictionaries and books. He has even written a book in Swedish called, “en Teologisk strid infor Ras Mengescha”. Here is his amazing story in Amharic.

አለቃ ታዬ ልደት 1853 ዐ.ም. በዘመነ ወንጌላዊ ሉቃስ 20 ወአሀዱ ለህዳር ነው ይህም አፄ ቴዎድሮስ በነገሱ በሰባተኛው አመት ነው። በአውሮጳ አቆጣጠር ግን በ1861 እ.ኤ.አ. በኖቬምበር ወር ሰላሳኛው ቀን ተወለዱ ። በጣና ሀይቅ በስተምስራቅ በምትገኘው ልዩ ስምዋ ይፋግ ተብላ በምትታወቀው መንደር የተወለዱት አለቃ ታዬ በልጅነታቸው ወራት ወላጆቻቸውን በማጣታቸው የእናታቸው ወንድም ትግራይ ይኖሩ ስለነበር አጎታቸውን ፍለጋ ወደ ትግራይ ያመራሉ ትግራይ እንደደርሱ አጎታቸውን ስላጡዋቸው ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ አቅደው ምፅዋ ደረሱ ምፅዋ ይገኝ በነበረው የስዊድናውያን ሚስዮን ት ቤት ውስጥ መፅሀፍ ቅዱስን ማጥናት የጀመሩትም ያኔ ነበርእምኩሉ በተባለው በዚህ ት/ቤት ለብዙ አመታት የወንጌልን ቃል ከተማሩ በህዋላ ወደትውልድ አገራቸው ጎጃም ተመለሱና የግእዝ ቅኔ ት/ቤት ገቡ ቅኔውን ከሙሉ አገባቡ ጋ አሳምረው ከዘረፉ በህዋላ አለቃ የሚለውን ከፍተኛ ማዕረግ አግኝተው እንደገና ምፅዋ በመመለስ በተማሩበት ት /ቤት በመምህርነት አገለገሉ ።

በዚህ ጊዜም “መፅሀፈ ሰዋሰው ” የተሰኘውን የመጀመርያ መፅሀፋቸውን ፅፈዋል አለቃ በህይወት ዘመናቸው ከደረሱት መፅሀፍቶቻቸው ዋናዋናዎቹ እስካሁን ድረስ የሚገኘው በስዊድንኛ የጻፉት ‘ en Teologisk strid infor Ras Mengescha” ( A theological debate before Ras Mengesha ወይም ነገረ መለኮታዊ ክርክር በራስ መንገሻ ችሎት ) እና በእጅ ፅሁፋቸው የተዘጋጀ አብዛኛው ማጣቀሻው በግዕዝ የሆነው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ወይም የፅንሰ ሀሳብ መዝገብ ናቸው ።

እንደገና ወደ ትውልድ መንደራቸው የተመለሱት አለቃ ታዬ በወቅቱ ቤጌምድርን ይገዙ በነበሩት በራስ መንገሻ አቲከም ዘንድ ሞገስ በማግኘታቸው በ1891 ወደ አጼ ምኒልክ ላኩዋቸው ። ለንጉሱም የበኩር ስራቸው የሆነውን መፅሀፈ ሰዋሰውን በገጠ በረከትነት ሰጡ ንጉሰ ነገስቱም የግል ፀሀፌያቸውን ጠሀፌ ትዕዛዝ ገብረስላሴን ባልደረባ አድርገው ሰጡዋቸው ። በነገስታቱ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ በማግኘታቸው የቀኑ አንዳንድ የቤተ ክህነት ሰዎች አለቃ ታዬ ትምህርቱን የቀሰመው ከሚስዮናውያን ነው በሚል ሰበብ ብቻ ክስ ያበዙባቸው ስለነበር ይህኑኑ ጉዳይ ለአፄ ሚኒልክ አመልክተው የሚከተለውን ደብዳቤ ተቀበሉ

“…….ሞዐ አንበሳ ዘዕምነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ሚኒልክ ስዩመ እግዚአብሄር ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ : አለቃ ታዬ ገብረማርያም የሚባል ምጥዋ የነበረ ሀይማኖቱን እኛ መርምረነዋልና ማንም አንዳች አይበለው በሀይማኖት ነገር ። በህዳር ወር በስድስተኛው ቀን 1891 አ .ም በወረኢሉ ከተማ ተፃፈ ።….”

ከዚህ በህዋላ ወደ ቤጌምድር ተመልሰው ስራቸውን ቀጠሉ ቢሆንም አሁንም የታዬ ሀይማኖት የፈረንጅ ነው ንጉሱ ሳያውቁ ነው ማህተም የሰጡት የሚሉ ከሳሾች በመነሳታቸው ተከሰው ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ፊት ቀረቡ ። ነገሩ እየከረረ መጥቶ ንጉሰ ነገስቱ ፊት ድረስ ደረሰ ንጉሱም አለቃንም ጳጳሱንም ገስጸው ነገሩን ካበረዱት በህዋላ ወደ ቤጌምድር መልሰው ላኩዋቸው ወድያውኑም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ደረሳቸው

‘ ሞዐ አንበሳ ዘዕምነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ሚኒልክ ስዩመ እግዚአብሄር ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ይድረስ ከአለቃ ታዬ እንደምን ሰንብተሀል ከጀርመን መንግስት ተልከው የመጡ ሰዎች ወደ ሀገራቸው ለመሄድ በጎጃም በኩል ወጥተዋል ነገር ግን በኢትዮጵያ ቕዋንቅዋ የተፃፉ የጥንት መፅሀፍት በአገራችን አሉ ያንን የሚያውቅ ብልህ ሰው ይሂድና እንዲመለከት ይሁን ብለውኛል አንተ የዚያን ሀገር ባህል ለምደከዋልና እናንተ ዘንድ በደርሱ ጊዜ አንተም ከነሱ ጋ አብረህ ሂድ መጋቢት 9 ቀን 1897 አ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ተፃፈ ።

ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ የህይወት ታሪኬ በሚለው መፅሀፋቸው ይህኑኑ ሁኔታ እንዲህ ገልጠውታል …..

የጀርመን መንግስት የግዕዝ ቅዋንቅዋ የሚያስተምር አንድ ሊቅ ይሰጠኝ ብሎ አፄ ሚኒልክን በለመነ ጊዜ ስመጥሩውን ሊቅ አለቃ ታዬን መርጠው ሰደዱዋቸው …በጀርመን መንግስት ሶስት አመት ሙሉ የግዕዝ ቅዋንቅዋ አስተምረው ኒሻን ተሸልመው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አጼ ሚኒልክም ኒሻን ሸልመው የአባታቸውን አገር ሰጥተው ወደ ቤጌምድር ሰደዱዋቸው ታዬ በአውሮፓ ቆይታቸው ብዙ ሀገራትን ጎብኝተዋል።

አለቃ በጀርመን ቆይታቸው ከአፄ ሚኒልክ ጋ እየተፅፅፉ በግዕዝ የተፃፉትን መፅሀፍት ከመሰብሰብና ከመመርመር በተጨማሪ አማርኛንና ግዕዝን በበርሊን ዩኒቨርሲቲ አስተምረዋል። አለቃ ታዬ የጀርመን ቆይታቸውን ሲገለፁ “…ከአገር ናፍቆት በቀር የጎደለብኝ ነገር የለም። ለጥበባቸው ፍፃሜ የለውም ። በየእለቱ አዲስ ነገር አያለሁ ። አዲስ ነገር እሰማለሁ ። ጃንሆይ ከአገርዎ ልጆች ወደ አውሮፓ ሰደው ቢያስተምሩ መልካም በሆነ። የያጆንና የሞሮኮ መንግስት ሰው እየሰደዱ አስተማሩ ….ይህን አይቼ ለአገሬ መንግስት ቅንአት እንደ እሳት በላኝ ፣ምንኮ አደርጋለሁ ? አዝኘ ወደ መቃብር እወርዳለሁ ፣ የጃንሆይ ብር እንዲሰለጥን የፊተኛውን ብርና አሞሌ ያጥፉ ፣እኛ ሀበሾች በመንፈሳዊና በስጋዊ ጥበብ ወደፊት የማንገፋበት ምክንያት ምን ይሆን ብሎ ለሚጠይቅ ህዝቡ ሁሉ ባይማርና የወንጌልን ስብከት ብብዙው ባይሰማ እውነተኛ እውቀትና አፍቅሮ ቢፅ ትህትና ቢጠፋ ነው ፣ባገራችን ጥቂት እውቀት ያላቸው ሰዎች በመከበር ፈንታ ስለሚሰደቡና ስለሚዋረዱ ስለሚጠቁም የሚያውቁትን ጠቃሚ የጥበብ ስራ ትተው በቦዘን መኖርን መረጡ የአዳምን ልጆች ሁሉ የፈጠረ አድልዎ የሌለበት አንድ ልኡል እግዚአብሄር ነው ላንዱ ወገን ህዝብ ሙሉ ላንዱ ጎደሎ ልብ አልፈጠረም እንዲህ ከሆነ ስለምን ያውሮፓና የእስያ ልጆች ካፍሪካ ክፍልም ጥቂቶች ብልሀተኞች ሲሆኑ እኛ ሀበሾች መፅሀፍ ቢማሩ ኮቸሮ ለቃሚ ፣ብርና ወርቅ ቢሰሩ ቀጥቃጭ ቡዳ ፣እንጨት ቢሰራ አናጢ እንጨት ቆርቅዋሪ ፣ቆዳ ቢፍቅ ጥንበ በላ ፋቂ ፣እየተባለ ስም እየተሰጠው ስለሚሰደብ የጥበብ ስራ ጠፋ ፣ስልዚህ ጉዳይ ጃንሆይ አስበው እንዲህ ያለው ነገር በአዋጅ እንዲከለከል ሰዎች እንዲከበሩ ቢያደርጉ በሌላ መንግስት ስምና መልክ በተቀረጸ ገንዘብ ከመገበያየት በጃንሆይ መልክና ስም ገንዘብ እንዲወጣ ቢያደርጉ ነፅ መንግስትም ራሱን የቻለና የተምዋላም ይሆናል ።

ይህ ደብዳቤ ከተፃፈ ከአራት ወር በህዋላ በጃንዋሪ 1908 አጼ ሚኒልክ የትምህርትን አስፈላጊነትና የስራን ክቡርነት ያካተተውን አዋጅ አወጡ ።

ከጀርመን መልስ በህዋላ የኢትዮጵያን ሶስተኛውን የክብር ኮኮብ ኒሻን የተሸለሙት ታዬ በቤጌምድር እንደገና ታላቅ ተቃውሞ ተነሳባቸው ….የአገሩ ገዢ የነበሩት ንጉስ ወልደጊዮርጊስም የሚከተለውን ደብዳቤ ሰደዱላቸው …. የተላከ ከራስ ወ /ጊዮርጊስ ይድረስ ከአለቃ ታዬ እንዴት ሰንብተሀል ? እኔ እግዚአብሄር ይመስገን ደህና ነኝ ዝም ብለህ ተቐመጥ ስንልህ እንደዚህ ያል ትምህርት ከየት ነው ያመጣከው ? በምን ተጣላኝ እንዳትል ? በ 1903 ህዳር 24 ተፃፈ

አለቃም ሀይማኖታቸው ተዋህዶ መሆኑንና የተፈጠመባቸውም ግፍ መሆኑን በመግለፅ ደብዳቤ ፅፈው ላጼ ሚኒልክ መልስ ላኩ ንጉሱም የተወሰደባቸው መሬት እንዲመለስላቸው ትዛዝ ሰጡ ። ሁኔታው ያልተዋጠላቸው የቤተ ክህነት ሰዎች ታዬ ፀረ ማርያም ነውና አገር መግዛት አይገባውም የሚል ሌላ ክስ አመጡ ነገሩ የሀይማኖት ጉዳይ በመሆኑ ወደ ግብፃዊው ፓፓስ ዘንድ ነገር ተመራና ጥር 24/1903 በዋለው ጉባኤ አለቃ ፈለቀ የተባሉ የቤተክህነት ወኪል ከሳሽ ሆነው በመቅረብ፣አለቃ ታዬ ለስዕልና ለመስቀል አይሰግድም፣በሞቱ ቅዱሳን አማላጅነት አያምንም ፣ዝክርንና ምፅዋት የሞተ ሰውን ሊያፀድቅ እንደማይችል ይናገራል ፣የልማድ ፆም ዋጋ እንደሌለው ይናገራል ፣ቀናትን አያከብርም ሲሉ የክሱን ጭብጥ አስረዱ በቀረቡት ክሶች ላይ ከፍተኛ ክርክር ተደርጎ ጳጳሱ ከመሳፍንቱና ከባልደረቦቻቸው ጋ በመሆን አለቃ ታዬን ከገሰፁ በህዋላ በነፃ ቢለቁዋቸውም በነፃ መለቀቃቸው ያበሳጫቸው ካህናት የንጉሰ ነገስቱ ባለ ሙሉ ስልጣን እንደራሴ ለነበሩት ለራስ ተሰማ አቤት በማለታቸው ያለ ህግ ወደ ታላቁ ወህኒ ቤት እንዲገቡ ተደረገ።

ከጥቂት ጊዜ በህዋላ ተፈተው በቁም እስር እንዲቆዩ ተደርገው በ1912 አ.ም. ለመንግስት አማካሪነት ተመርጠው መስራት ጀምረው ነበር።

ምሁሩ አለቃ ታዬ ነሀሴ 15 ቀን 1916 አ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...