ሰይጣን ይሁን ራሴ ወይም ፈጣሪ ለሀጥያት በቀጠሩልኝ ቀን ከአለቃዬ ጋር ባለግኩ። ይኸው ነው ሀጥያቴ!
ጨው የሌለው አልጫ ወጥ አልጫ ወጥ የሚል ትዳር ውስጥ ፀጥ ለጥ ብዬ እንድቆይ ባለእዳ ያደረገኝ ሀጥያቴ ይኸው ነው!! ይኸው ነው ብዬ አቀለልኩት?
ካልጠፋ ቀን የዛን ቀን ስልኬ ባትሪ ጨርሶ ባሌ ሲደውል ስልኬ ዝግ ነበር። ካልጠፋ ቀን ስልኬ በዘጋ ቀን ስንት ቀን ባልተሰማኝ ያለፍኩት የአለቃዬ እጅ ሲነካኝ ንዝረቱን እንቢ ማለት አልቻልኩም። ካልጠፋ ቀን ባሌ የዛን ቀን ቢሮዬ ድረስ ዘለቀ። ምን የሚሏት ባላጊ ነኝ ግን? በዘመኔ ከባሌ ውጪ አንድ ሰው ብሞክር እሱንም የቢሮ ጠረጴዛ ላይ? እኔን ብሎ ባላጊ ! ቅሌቴ በዚህ አላበቃም።
ተያየን። ጠረጴዛው ላይ በግማሽ አካሌ ተጋድሜ ሰማይ የእኔን እግሮች ምሰሶ አድርጎ የቆመ ይመስል እግሮቼን ወደላይ ወጥሬ ሰድሬ አለቃዬ ከእግሮቼ መሃል ሆኖ ሲለፋ ባሌ በሩን ከፍቶ ሲገባ ተያየን። (አንባቢ ሆይ እዚህጋ ለምትስሉት ምስል እኔን ተጠያቂ እንዳታደርጉ። ሁኔታውን በምስል ለመከሰት ታስቦ እንጂ አንባቢን ክፉ ለማሳሰብ ያልታሰበ!)
ለወትሮ ጨዋ ነበርኮ። ካልጠፋ ቀን የዛን ቀን ጨዋነቱን እረስቶ ሳያንኳኳ ዘው ይላል? አፌን ከፍቼ ብዙ ቆየሁ። ድንጋጤው ይሁን የአለቃዬ ልፋት ወይም ሁለቱም አፌም ተከፍቶ አይኔም ፈጦ ብዙ ሰከንዶች አለፉ!! ባሌ ቀስ ብሎ እንደገባ ሁሉ ቀስ ብሎ ወጣ! አለቃዬ በድንጋጤ የተጋለጠ ንብረቱን ለመሸፋፈን ይተረማመሳል። (ይሄ ደግሞ የሚስቱን ምጣድ በቂጡ ነው እንዴ የሚያስስላት? እሱ የበጨጨ ቀይ ፣ ቂጡ የብረት ምጣድ ቂጥ የሚመስለው!)
ከአንድ ሰዓት በላይ ቢሮዬ ተቀመጥኩ። ተጎለትኩ። የማስበውን አላውቅም። ወደቤት እንደማልሄድ አውቀዋለሁ። አይኑን አላየውም። ግን ወዴት ነው የምሄደውስ? ብቻ አላወቅኩትም። ቦርሳዬን አንስቼ ወጣሁ። ደርቄ ቆምኩ። ባሌ እየጠበቀኝ ነበር። ልክ ምንም እንዳላየ፣ ድሮ እንደሚያደርገው ሁሉ ዘሎ ከመኪናው ወርዶ በሩን ከፈተልኝ። ልሩጥ? መኪና ውስጥ ልግባ? ምን ላድርግ ደረቅኩ!
“ወደቤታችን እንሂድ አይደል?” አለኝ ቁጣም ፍቅርም ፣ ልስላሴም ምሬትም ባለው ድምፅ። አሁንም ምን እንደምለው ግራ ገባኝ። መሮጥ ፈለግኩ። ማምለጥ ! መሸሽ። ገብቶታል። አጠገቤ ደርሶ እጄን ያዝ አደረገው። ሲመጣ እያየሁት ደርሶ ሲነካኝ በረገግኩ። አብሬው ተራመድኩ።
“ስንት ጊዜያችሁ ነው?” አለኝ በፀጥታ ሲነዳ ከቆየ በኋላ
“ምኑ? ማለቴ? ” ተንተባተብኩ
“ስታደርጉት የነበረውን ስታደርጉ ስንተኛ ጊዜያችሁ ነው?”
“የመጀመሪያችን”
“ትወጂዋለሽ? በፍቅር ትወጂዋለሽ? ከኔ በላይ ትወጂዋለሽ? ”
“ኸረ አልወደውም!” እያልኩት ለምን አይሰድበኝም? ለምን አይጮህብኝም? ለምንድነው ምንም እንዳላደረግኩ ተረጋግቶ የሚጠይቀኝ? እያልኩ አስባለሁ ።
“ፍቅራችን ይህን ማለፍ አይችልም?” አለኝ። ዝም አልኩ።
“ይህን ማለፍ የሚችል ፍቅር የለንም?” አሁንም ዝም አልኩ።
“ይችላል። በደንብ ይችላል!!” ራሱ መለሰ። ድምፁ ውስጥ አማራጭ የለውም።
እቤት ስንገባ አፉ ከመለጎሙ ውጪ ከዛ ቀን በፊት ከሚያደርገው ምንም ዝንፍ ያላለ አመሻሽ አመሸን። አስፈራኝ! ብዙ ክፉ ሀሳብ አሰብኩ። ለዓመታት አቅፌው የተኛሁት ባሌ እንቅልፍ ሲወስደኝ ሲጥ አድርጎ የሚገድለኝ መሰለኝ። እያበድኩ መሰለኝ! ባልጌያለሁ አይደል? ቅድም ባሌ ስባልግ አይቶኝ የለ? ወይስ ቅዠት ነው?
ልክ አይደለማ! ሚስቱ ስትማግጥ በዓይኑ አይቶ ምንም እንዳልተፈጠረ መሆን ምኑ ነው ልክ? ንዴቱ ይቅር እንዴት አላስጠላውም? ለምን ብሎ እንዴት አይጠይቀኝም? ጭጭ አለ። እያጎረሰኝ እራት በላን!! ሶፋው ላይ እግሮቹ መሃል አስቀምጦ አቅፎኝ የጀመርነውን ተከታታይ ፊልም አየን! እሱ አየ እኔ ዓይኔ ቴሌቭዥኑ ላይ እየተንቀዋለለ ቅዠት እሰፍራለሁ።
ከቅሌቴ በፊት
እንደአብዛኛዋ ኢትዮዽያዊ ሴት ዮንቨርስቲ ጨርሼ እስክወጣ “ወንድ ልጅ ኡፉ ነው።” ተብዬ ነው ያደግኩት። (ምኑጋ እንደሚፋጅ አልነገሩኝም) ይሄ ወንድ የሚሉት ፍጥረት ከአላማ የሚያስተጏጉል… ወደፊትሽን ሊቀጭ አሰፍስፎ የሚጠጋሽ አሰናካይ …. ከብልግና ውጪ ሀሳብ የሌለው ክፉ ፍጡር …. (እንደአላብዛኛዋ ሴት ያሉኝን አምኜ ወይም ፈርቼ ይሄን እርኩስ ፍጡር ስሸሽ አድጌ አላማሽ ነው ያሉኝን ትምህርቴን ተመረቅኩ)
ከዩንቨርስቲ ተመርቄ ስራ እንደጀመርኩ ያ ኡፉ ነው የተባልኩት ወንድ ድንገት በህይወቴ አንገብጋቢ ፍጥረት ሆኖ መጪ ሂያጅ “መቼ ነው የምታገቢው?” ይለኝ ገባ! እሱ በህይወቴ ስለሌለ ከህይወት ወሳኙ ክፍል እንዳመለጠኝ አይነት!!
ስሸሸው ኖሬ ኖሬ ስፈልገው ብቅል የሚል ያስመስሉታል!
እንደአብዛኛው ሀይማኖተኛ ቤተሰብ እንዳላት ኢትዮዽያዊ የባል መስፈርቱ “እግዜርን የሚፈራ” ተብሎ ተምሪያለሁ። 100 ሺህ እግዜርን የሚፈራ ወንድ ቢኖር ከነዚህ መሃል የኔን ባል የምመርጥበትን መለኪያ አላስተማሩኝም። … ከመቶ ሺወቹ የተገኘው … የቀደመ … ወይም ይሄን ገፍታሪ መኮሳተሬን የደፈረ…
መጣ! እግዜርን የሚፈራ …. እጅግ ደግና መልካም! ጨዋ የጨዋ ዘር …. አወቅኩት! ለመድኩት!! ወደድኩት!!
“የተባረከ! መሬት የሆነ ወንድ! እድለኛ ነሽ” ተባልኩ።
ቤተክርስቲያን ቆሜ በህመሙም በድካሙም በፎከቱም ….. ላልለየው ብዬ ቃል ገባሁ። ውብ ነበር። የመጀመሪያዬ …. የመጨረሻዬ … ህይወቴ .. ዓለሜ … ተባባልን!! ኖርን ኖርን ኖርን ….. ሁለት ዓመት …..
የወደድኩት ባሌን ሳይሆን ትዳርን እንደሆነ ገባኝ … እንዴት? አላችሁ? እሱን ላላገባችሁ እና ለፍሬሽ አግቢዎች አብራራለሁ ያገባችሁ (ቢያንስ 5 ዓመት የሆናችሁ) ገብቷችኃል።
“ልጅ እንውለድ አይደል ፍቅሬ? ” አልኩኝ የሆነ ቀን
“ልጅ መውለድ እንደማልችል አልነገርኩሽም እንዴ?” አለኝ ልክ ውይ የላክሽኝን ቲማቲም ሳልገዛ ረስቼ መጣሁ እንደሚባለው ዓይነት ቅልልል አድርጎት።