ጠበቃ:— የተከበረው ፍርድ ቤት ተከሳሽ አስቀድሞ በግልፅና በአፅኖት እንደተናገረው ከደንበኛዬ ድርጅት የመዘበረውን 120 ሺህ ዮሮ ለፍቅረኛው ጉች ጉች ያለ ጡት ማሰሪያነት ተጠቅሞበታል። የቀረቡት ማስረጃዎች እንደሚያመላክቱት በእጁ የሚገኝ ውድ ንብረት የፍቅረኛው ጡት ብቻ ነው።
ዳኛ:— ምን እያመላከትክ ነው?
ጠበቃ:— ይሄ ሰው ለደንበኛዬ ሊከፍለው የሚችለው ቤሳ ቤስቲን ካሽ የለውም። ምንም አይነት በስሙ የተመዘገበ ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ ንብረት የለውም።
ዳኛ:— ወደ ነጥብህ (ዳኛው የሚቀጥለው ነጥብ ያጓጓቸው ይመስላሉ)
ጠበቃ:— የምለውማ ጡቱ ሀቃችን ነው። ማለቴ የደንበኛዬ ሀቅ ነው።
የነገሩ አዝማሚያ ያላማራቸው ዳኛ መዶሻቸውን መቱና የደቂቃዎች እረፍት ሰጡ።
ደንበኛ:— ያምሃል እንዴ እኔ ጡት ምን ያደርግልኛል? ገንዘቤን ነው የምፈልገው! ምን የሚያህል የሚስቴን ጡት እቤቴ………
ጠበቃው: —(ሳያስጨርስው ቡፍ ብሎ) እሱን ነገር ደፍረህ ጡት አልከው? ጓዳ እቃ እያጠበች ‘እኔ እስክመጣ ድረስ እየጠባህ’ ብላ መኝታ ቤት የምትልክልህን ጡት ደፈር ብለህ ጡት አልከው?
ደንበኛ:— እርግጥ ሚስቴ ጡቷ ትልቅ ነው። ቢሆንም ወደዋለሁ። ደግሞ በባለቤቴ እንድታላግጥ አልፈቅድልህም። ደሞ ጡት እንደሆነ ጡት ነው።
ጠበቃው:— ጡት ሁላማ ጡት አይደለም … … አሁን ማን ይሙት አናን እንኳን መቶ ሀያ ሺህ ዮሮ ሆጭ አድርጋ ጡቷን አሰርታ አይደለም። በስፖንጅ ጡት ማስያዣዎቿ በዛ ዳሌ ስትመናቀር ሻፍጄባት አላውቅም ልትል ነው?
ደንበኛ:— አላውቅም። ፀሃፊዬ ከመሆኗ ውጪ ዳሌዋም ጡቷም ትዝ ብሎኝ አያውቅም። ደግሞ ገና ስትቀጠር ጀምሮ የአንድሬ ፍቅረኛ እንደሆነች አውቅ ነበር። እንዴት በሌላ አስባታለሁ?
ጠበቃ:— ችግርማ አለ! ……
ደንበኛ:— አሁንም ቢሆን እኔ አናንም ሆነ ጡቷን አልፈልግም! ገንዘቤን ነው የምፈልገው!
ጠበቃው:— ጥሩ! ሰውየው ሊሰጥህ የሚችለው ቤሳቤስቲን የለውም። …… ምንም አታገኝም። …… የሁለት ወር የሰራተኞች ደመወዝ ዕዳ፣ የሁለት ወር የድርጅት ኪራይ ዕዳ፣ አሁን ደግሞ ለእኔ መክፈል የሚኖርብህ እዳ… … ምንም የለህምኮ ነው የምልህ?
ደንበኛ:— እና ምን አድርግ ነው የምትለኝ?
ጠበቃ:— ቢያንስ ዕዳህን ቀንስ… … አንተ የአናን ጡት አትፈልገውም። እኔ እፈልገዋለሁ!! …… ያለብህን እዳ ከፈልክ ማለት አይደል?
ዳኛው ጉሮሯቸውን ጠራርገው………
አቶ አንድሬ የድርጅቱ አስተዳደር ሆነህ ከተቀጠርክበት መስሪያ ቤት 120 ሺህ ዮሮ ያለአግባብ በመውሰድ ለፍቅረኛህ ጡት ማሰሪያነት መጠቀምህን ተናግረሃል፣ ፍቅረኛህ ፍርድ ቤት ቀርባ ይሄን ልትመሰክርልህ ትችላለች?
ደንበኛ:— አይመስለኝም ጌታዬ! ፍቅረኛዬ ከድታኛለች!
ዳኛ:— ጡቷን ካሰራህላት በኋላ ነው የከዳችህ?
ደንበኛ:— አይደለም ጌታዬ ቅድም ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳሁት ፍቅረኛዬ ትንንሽ ጡቶቼን አልወዳቸውም። ካፈቀርከኝ ጡቴን አሳድግልኝ አለችኝ።
ዳኛ:— እሱን ሰማን!!
ደንበኛ:— ተውበው የተሰሩ ጡቶቿን ለመዳበስ እድል አጊንቻለሁ። ትልልቅ ጉች ጉች ያሉ ሆነውላታል። ቤቴንና መኪናዬን ስጦታ ከሰጠኋት በኋላ ነው የከዳችኝ!!
ጠበቃ:— ቅልጥ!!!!
(ጠበቃው ዝም ብዬ ሳስበው Gemechu ይመስለኛል)