ተከርክሞ የተገረበ፣ ቧልትና ቁምነገር!!
“ስለ ሴቶች“
( ስለ ወንዶች ደግሞ እነሱ ይፃፉ)
ከአፈጣጠር እንጀምር፤
በኔ እምነት፣ ሴቶች የተፈጠሩት፣ ወንዶች በተፈጠሩባት ቅፅበት ነው፡፡ እንደ መጥሐፉ ከሆነ፣ ሴት የተፈጠረችው ሁለተኛ ነው፡፡ በደንብ ካየነው ግን እኩል ነው የተፈጠሩት፡፡ ወንድ ሲፈጠር፣ እንትን ነበረው አይደል? ያው ብልት እንበለው እንደፈረደብን፡፡ እና ሴት የማትፈጠር ከሆነ፣ ብልቱ ምን ሊሰራለት ተንጠለጠለ? መቼም ሲደብረው እንዲጫወትበት አይደለም…ሎል!
ስለዚ ወንድ ሲፈጠር ሴት እንደምትፈጠር እርግጥ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህችን ሀሳብ ቀጥሎ ያለችው ግጥም የምትሸከማት መሰለኝ…እንግዲህ ይሄ፣ የአዳም እንትን functional ነው ብለን ስናምን ነው(ነውም)
ሰው ከመሰራቱ በፊትም፣ እንስሳት ሴትና ወንድ ሆነው ቀድመው ተሰርተው ነበር፡፡ ስለዚህ ሴትነት ቀድሞ የሚታወቅ ፅንሰ ሀሳብ ነበር፡፡ እና ለሰው ጊዜ ሴት ለምን ኋላ ተፈጠረች? እንጃላቷ፣ ሞኝነቷ! ብለን እንለፈው ይሆን?
የሆነስ ሆነና ሴት ተፈጠረች፡፡ በለሱን በላችና አስባረረችን፣ ሟችም አደረገችን-የተባረከች! የሴት ልጅ ተወዳዳሪ የሌለው ጥቅሟ ሞትን ማምጣቷ ነው፡፡ በመሰረቱ ህይወት የተጀመረው ከሞት በኋላ ነው፡፡ ከዛ በፊት ዝም ብሎ….. ዝም ነገር ነው! ሞት ከሌለ ህይወት ምኑ ህይወት ይባላል( ካልተግባባን በቅርብ ቀን ስለ ሞት በምፅፋት ፅሁፍ ላይ እንግባባ ይሆናል)፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያውን የሞት ፊሽካ የነፋችው ሄዋን ናት፡፡ የአዳም ረታ `ሕማማትና በገና` ላይ ዳዊት የሚባለው ገፀ ባህሪ እንዲህ ይላታል፤
“…. ያቺ ሴት፣ ያቺ ቂልና ቀልቃላ ሴት፡፡ያቺ ሄዋን የምትባል ሀጠራው“
እኔ ግን እምጵጵጵዋዋ! እላታለሁ፡፡
*እኩልነት*
››››››››››››‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹
ሴት ከወንድ እኩል አይደለችም! እንኳን ሴት፣ ወንድ ከወንድ ጋርም እኩል አይደለም፤ ሴት ከሴትም እንዲሁ፡፡ ሁለት የተለያዩ ነገሮች በፍፁም እክል ሊሆኑ አይችሉም፡፡እኩል እድል በመስጠት እንጂ በእኩልነት አላምንም( ሁለቱም ሰው ናቸው! አለቀ ደቀቀ!!)
“ኮከብ እም ኮከብ ይኄይስ እም ክብሩ!“
“The worest form of inequality is to make unequal things equal” -እንዲል ኦቦ አርስቶትል፡፡
እና ማን ይበልጣል?
የመጀመሪያዋ ሴት( ሊሊቱ ሳትሆን ሄዋን) ጠያቂ ነገር ነበረች፡፡ ለምን? ትላለች፡፡ እፀ በለሱን አትብሉ ሲባል፣ለምን? ብላ ጠየቀች፡፡ ውጤቱን ማየት አማራት( curiosity ነበራት) አዳም ነፎ-ጅላንፎ ነገር ነበር ያኔ፡፡
የዛሬዋ ሴት ግን የመታወቅ እንጂ( በወሲብ)የማወቅ ጉጉት ያላት አይመስልም፡፡ የድሮው አዳም “አንቺ ነሽ ሞትን ያመጣሽብኝ!“ ብሎ እየነዘነዘ ነፈዝ ሳያደርጋት አልቀረም፡፡ ሀጠራው አዳም! ሃሃሃ
ዛሬ ማን ይበልጣል ካላችሁ፣ ዙሪያችሁን ማየት ነው፡፡ በነገራችሁ ላይ ሁሉም ሴቶች ማለት ይቻላል፣ ከወንድ እኩል አለመሆናቸውን ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም፣ ሁሉም `ከወንድ እኩል ነን` ይላሉ፡፡ አሃ….. እኩል ከሆኑ እኩል ነን ማለትን ምን አመጣው?
ጅቡ አህያዋ ሮጣ እንዳታመልጠው ስለሰጋ፣
“አንቺ አህያ አንዴ ነይ አልበላሽም!“ አላት አሉ፡፡ አህያዋ ጠየቀች፤ “ አያ ጅቦ፣ መምጣቱን መጣለሁ፣ አልበላሽምን ግን ምን አመጣው?“ ……..እና እኩል ነኝን ምን አመጣው?
የሴቶች ውስብስብነት!
‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ ›››››››››››››››
ሲግመንድ ፍሩድ፣ ሴቶችን ለሰላሳ አመታት አጥንቶ ነበር፡፡ በውጤቱ ግን ምንም! ምንም! ባዶ ኪስ!…..የገዛ ሚስቱን እንኳ ማወቅ ያልቻለ ሰው ነበር፡፡ ህልምን አጥንቶ፣ “ interpretation of dreams“የሚል ድንቅ መፅሐፍ የፃፈ ሰው፣ የ “psychoanalisis“ ጠንሳሽ የነበረው ሰው፣ “totem and taboo“ የሚል ጥልቀቱን የሚያሳይ መፅሐፍ የፃፈ ሰው፣ የሳይኮ ቴራፒ ህክምና ጀማሪው ስው፣ የ `penis envy` እና `castration anxiety`…ሌሎችንም ፅንሰ ሀሳቦች ያስተዋወቀ ሰው፣ ለሴት ሲሆን ግራ ገባው! ምስኪን!! እንዲህም አለ፤
“ The great question that has never been answered, and which i have not yet been able to amswer, despite my thirty years of research into the feminine soul is `what does a women want?“
ሴቶች የፍልስፍና ማጠንጠኛ ሆነዋል፡፡ ብዙ ተመራማሪዎች ባህሪያቸውን ለማጥናት ደፋ ቀና ብለዋል(ነውም መሰለኝ)፡፡ በየሀገሩ የስነ ፅሁፍ ጭብጥ ሆነዋል( `አንዲት ሴት አይቼ ደስ ካለችኝ ስለሷ ፅፋለሁ` ያለኝ አንድ ታዋቂ ገጣሚ አለ፡፡ … አሁን እራሱ፣ ሬድዮንህን ብትከፍት፣ ስጋ ቤት በር ላይ ያለህ ይመስል `ጭኗ፣ ባቷ፣ ሽንጧ፣ መላላጫዋ፣ ጨጓራዋ…. ምናምን ተብሎ ሲዘፈን ትሰማለህ፡፡ ሃሃሃ ሞክሪው እስቲ)
እኔ ግን አምናለሁ፣ ሴቶች እንዲህ አልገባ ያሉት ለራሳቸውም ውስብስብ ስለሆኑ ነው፡፡ ወይም አንድ ተውኔት ላይ እንደሰማሁት፤
“ ሴቶች ሲያቅፏቸው እንጂ፣ ሲፈላሰፏቸው ሆረር ናቸው“ ( እኔ አይደለሁም!)
ሴቶችን ይበልጥ አንድ የሚያደርጋቸው (በኔ እምነት) አጣጥለሃቸው ካወራህ፣ እኩል መንጫጫታቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ስለድንግልና አጣጥለህ አውራ እስቲ፡፡ ከወንድሞቿ ውጪ ከወንድ ጋር ከሰላሳ ደቂቃ በላይ አውርታ የማታውቀውም፤ ስለድንግልና ጥቅም ከማወቋ በፊት፣ ያባረረችውም እኩል ይጮሁብሃል፡፡ “ክብራችን ነው፣ አርማችን ነው፣ መለያችን….!“ ጣ ጣ ጣ….. ቷ…. ቷ…. ቷ… ያዘንቡብሀል፡፡
ካምፓስ እያለን፣ `አቻ ለአቻ ውይይት` ተብሎ ይሄ ጉዳይ ከተነሳ….. በለው ነው እንግዲህ፡፡ ውጪ ያቀፍናቸው ሴቶች ጭምር ድንግል ነን ሲሉን እንሰማለን፡፡ ጌጣችን ነው፣ ጉትቻችን ነው እያሉ ያደክሙናል፡፡ ባለኝ እምነት፣ ቤቲ የቦልቷ እንኳን እዚህ ውይይት ላይ ዛሬ ብትሳተፍ `ድንግል ነኝ፣ በእሱ ደግሞ ኮራለሁ!… ሀብቴ ነው` እንደምትል አጠረጥራለሁ…..
ስለ ድንግልና ካነሳን አንድ ወዳጄ የነገረኝን ነገር ጣል አድርገን እንለፍ፡፡ በነ ደርጉ ጊዜ ነው፡፡ አንዱ መሬት ቆፍሮ አጓጉል ነገር ሲሰራ ተያዘ አለ፡፡ እና ፍርድቤት ቀረበ፡፡ እድሜ ልክ ተፈረደበት፡፡ ቅጣቱ የተበየነበት፤ “ ድንግል እናት ሀገርን በመድፈር“ በሚል ነበር፡፡ ( የዛሬዎቹን ደፋሪዎች ማን ይሆን የሚፈርድባቸው)
– ሴቶች ገላቸው ስስ ነው፡፡ ስሜታቸው ስስ ነው፡፡ ስስነታቸው ተጠቅመው፣ ሻካራነታችንን ድራሹን ያጠፉታል( አይ ጥበብ እላለሁ! ብዙ ባይጠቀሙበትም)
-ስሜታቸውን ይደብቃሉ፣ ስሜታቸውን ግን ይናገራሉ( ገዳዳ ነገሮች እኮ ናቸው፤ ሎል ብለናል)
-በቀጥታ አይጠይቁህም፣ የሚፈልጉትን ግን ያገኛሉ፡፡
– አይስማሙም፡፡ ፉክክራቸው አይጣል፡፡ ሴቶች እንዳይጣሉ ከመጠበቅ ወይ የማይመጣ ሰው፣ ወይ ድንበር መጠበቅ ይቀላል፡፡
– ለኛ ሲሉ ምንም ይለብሳሉ፣ ከዛ ፋሽን ይሉታል፡፡ “እራቁታቸውንም“ ይሄዱልናል፡፡
– ብዙዎቹ ደግሞ(በፍፁም ሁሉንም አይነካም! ወይም እራሳቸውን የሚያውቁትን አይመለከትም) ለገንዘብ ሲሉ ገላቸውን ከብርህ
ስር ይጥሉልሃል፡፡የባሰባቸው ደግሞ ቢግብራዘር ላይ፣ ቢግ ቦንብ ይዘውልህ ይመጣሉ፡፡… `ጥሩ ምግብ በልቼ፣ ጥሩ ሆቴል፣ ጥሩ እንትን ማድረግ ስችል፣ ከደሃው ጋር ፍቅር ብዬ ጀመሪ፣ እንትን እያልን በመሃል አቋርጦ፣ ስለ ኑሮ ያስብብኝ ወይ“ የምትል ልጅ አውቃለሁ፡፡ ታየኝ እኮ ተክሎ ስለ ኑሮ ሲያስብ…
– ከወደዱህ ይሞቱልሃል፣ ከጠሉህ ይገድሉኋል( ቀላል እውነት)
– ትልቅ የተፈጥሮ ሀይል አላቸው( ወንዱን አሻንጉሊት የሚያደርጉበት) ግን አይጠቀሙትም፤ ወይ አያውቁትም፡፡ ወንድ እኮ ሞኝ
ነገር ነው( ሞኝ ብልጥ)….. እንኳንም አላወቁት፡፡
አንድ ስሟን የማላስታውሳት ሴት ምን አለች፤ “ ሴት በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ! ምክንያቱም ወንድ ብሆን ኖሮ የማገባው እነሱኑ ነበር፡፡“ በለውውው!
በነገራቹ ላይ ሴት ልጅ እናት ስትሆንና እናት ከመሆኗ በፊት አንድ አደለችም፡፡ አንዱ እንደውም፣ “ እናት ለልጇ ፆታ የላትም፤ መላዕክ ናት፡፡“ ብሎኛል፡፡ እስማማለሁ፡፡ ሴቶች እናት ሲሆኑ፣ ወደ መላዕክነት ያድጋሉ፡፡( ክንፍ ግን አይኖራቸውም)
“ፆተኝነት“
ኢትዮጵየያን ከዘረኝነት ቀጥሎ ምን ያሰጋታል ከተባለ `ፆተኝነት` ነው፡፡ ለሌስቢያኒዝም መሰረት ከሆኑት አንዱ፣ መረን ለቀቅ ፆተኝነት ነው፡፡ ሴቶቹ እንደ ወንድ መሆን ሲያምራቸው፤ ወይም በወንዱ የስሜት ቁጥጥር ስር መሆን ሲያቅታቸው….
ሁለቱም የተለያየ የተፈጥሮ አዝማሚያ አላቸው፡፡ ያን አስታርቆ መኖር ሲቻል፣ `ውይ ሴቶች፤ ውይ ወንዶች` እየተባባሉ መዳረቅ ያስቀኛል፡፡ ሴቶች በቀደመ የህብረተሰቡ አኗኗር፣ ምክኒያት ያጡት ነገር አለ- አይካድም፡፡
ያ የሚሟላላቸው ግን፣ ከእኛ ከወንዶቹ እየተነጠቀ አይደለም( አንጀታቸው የተቃጠለ ወንዶች)
“ ኀፍረትን እና ክፋትን ከምታመጣ ሴት ደግነት፣ የወንድ ክፋት ይሻላል፡፡“ ( መፅሐፈ ሲራክ 42፣ 14) …..ሃሃሃ ልል ነው፡፡
እንዴ! በምን ተአምር ነው፣ ክፋት ከደግነት የሚሻለው፡፡ ደግሞ እኮ፣ `የወንድ` ተባለ እንጂ፣ የክፉ ወንድ ይሁን የበጎ አልተገለፀም፡፡ የክፉ ወንድም ክፋት፣ ከደግ ሴት ደግነት ይበልጣል ማለት ነዋ! ጉድ በይ ሴት( ወንዱም በል፣ ምናል ብንተባበር)
እንግዲህ፣ ጭቆና አለ ከተባለ አንዱ ጨቋኝ ኀይማኖት ይመስለኛል፡፡ እስልምናው፣ ክርስትናው፣ ……ናው፣ ….. ናው….. ያሉት ኀይማኖቶች( የግሪክ ሐተታ ተፈጥሮዎች ሳይቀሩ) ሴት ላይ ሸውራራ አመለካካት ነው ያላቸው፡፡ ይሄን ግን ሴቶቹም ተቀብለውት ስለሚኖሩ፣ በማያገባን ጥልቅ አንልም፡፡
ለማንኛውስ ከሴትነትም፤ ከወንድነትም ሰው መሆን ይበልጣል( አቋም!!!!!!!!!……….)
ሴቶችዬ ግን እንወዳችኋለን እሺ! ያለናንተ ህይወት ቢኖር ኖሮ፣ `ህይወት ትረስት` ኮንዶምን ማን ይጠቀመው ነበር( ሃሃሃሃ…. ቅንፍ ውስጥ ተደብቄ ልሳቅ እንጂ)
በሉ ወደ ባሎቻችሁ…. የሌላችሁም ወደሌላቸው ሂዱ ወይም ወደ እኔ ኑ…. ይሄን ቁምነገር ብላቹ ማንበባቹ ግን እያሳቀኝ ነው…..
3 Comments
ለዛ የለዉም
Arif
አዝናኝ