Tidarfelagi.com

ሰው ሳይቀና ሀገር አይቀናም

አንድ ሰው ራሱን በዘር መግለፁ ችግር ያለው አይመስለኝም። ችግሩ ዘረኛ መሆን ላይ ነው።ዘረኛ መሆንም ሃሳብ እንጂ ተግባር እስካልሆነ የከፋ ችግር አይሆን ይሆናል። ግን፣ዘረኝነት በልብ ይዘው የሚቆዩት ብቻ አይደለም። ካልወጣ፣ ሌሎች ካልጠላ፣ አጋጣሚውን ሲያገኝም ካልደቆሰ አስችሎት አርፎ መቀመጡን እንጃ!

አንዳንድ አስተሳሰቦች ትክል ናቸው። ስሜት ይሆናሉ። የፈለከውን የምክንያት ጉጠት አምጥተህ እስኪያልብህ ብትለፋ አይነቀሉም። ዘረኝነት ከነሱ አንዱ እየሆነ መሰለኝ። ተው ባሉት ቁጥር እየወፈረ እንጂ እየተስለመለመ አይሄድም። አሁን አሁን እያሳዘነ ሊያስቀን ጀምሯል። ጆርጅ ካርሊን ትዝ ይለኛል። ባንድ መፅሐፉ፣ «The planet is fine, the people are fucked» ይላል። እዚህም የሚታየኝ ያ ነው። the country is nice, the people are fucked.ትንሽ ምርጦች ቢኖሩም ተከልለዋል፤ተከልክለዋል! በእግረኞች ሀገር ፣ክንፋሙ ሞኝ ነው።ከፉ ዝቅ፣ ዝቁ ከፍ ነው።

ጌታው፣ አንተ በአቋም ይሁን በዘር ተለያየተህ በመጠዛጠዝህ ምድር ምንም አታጣም። ከ13 ቢሊዮን ዓመት በፊትም እዚሁ የነበረ ምድር ነው። ያለሰውም ይዘልቃል። ስንቱ ፕላኔት፣ ጋዝ እየተፋ ህዋ ውስጥ ይሽከረከራል።
ተፈጥሮ ኖርክ አልኖርክ ግዷ አይደለም። የተስማማው ይዘልቃል። ያልተስማማው፣ ለትውልዱ የበቀል አዝመራ እያስታቀፈ ወደ ከርሰ መቃብሩ ቻው።
ጨከን ማለት ያስፈልጋል። ህይወት አንዴ ነው። የማውቀው ሲኦል የደቡብ ኮርያን ነው። እና አንዳንድ ገነት የሚባል ስም የወጣላቸው ሴቶች።በተረፈ ህይወት እዚችው ምድር ላይ ነው የምታልቀው። ከሞትክ ሞትክ ነው። ተፈጥሮ ካንተ ሞት የሚያጣው የለም። ምናልባት ቢያተርፍ ነው። አፈሩን ያለማበታል። ላደሩለት ጌታ እና አቋም ተባድኖ መከሳከስ ታሪካችን ነው። ወደ ግራ፣ ወደ ቀኝም ስታይ «የፀብ ድግስ» ሲደገስበት የኖረ ሀገር ነው። ከእልፍ ታዳሚ ጋር። ለእኛ ምን ተረፈ… የዘመን ህመም! እዛው ድህነት ውስጥ መልመጥመጥ። ከበሬ እርሻ ያልወጣ ግብርና ይዘን፣ እንደ በሬዎቹ ካልተዋጋን ማለት! ተስማምተህ ብታቀናው ስንት የሚቀና ነበር። ሰው ሳይቀና፣ ሀገር አይቀናም። ይቅናን በሚል ባዶ ምኞትም የሚለወጥ የለም።

ተው ተው ማለት ዋጋ አልታይ እያለኝ ነው። ተስፋ መቁረጥ ነገር። እንቢ ያለ ከመከራው ይመከራል። ታሪክ እየሳቀበት፣ አንገቱን በሀፍረት ደፍቶ ወደ መሬቱ እስኪከተት መደማመጥ ጠላቱ ናት። ዐይንህ አጠገብ በየደቂቃው በሚያድግ ዓለም ስር፣ «ተግተን እንነስ» የሚልን አንሰን እስክንጠፋ ካላየ አይገባውም እና መጠበቅ ነው። የባይሆን ጥልቅ ምኞት ቢኖረንም በምኞት አይሆን!!
አሁንም the planet is fine,the people are fucked. more specifically the country is fine, the people are fucked.

የራስ ናቸው፡፡ የማንንም ሃሳብ ለመፃፍ አልተከፈተም! የሚያስማሙንን ሃሳቦች እዚህ ካገኛችሁ እሰየው፡፡ ለመስማማት አንፅፍም፣ ለመፃፍ አንስማማም፡፡ ወዘተ

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...