Tidarfelagi.com

ራሴው ማበዴ ነው

“ተሳፋሪዎቻችን ይህ የበረራ ቁጥር 206 ነው… … ” ጭንቅላቷ እየሸወዳት እንደሆነ የማውቀው እንዲህ ማለት ስትጀምር ነው። በግልቡ እብደቷ እየጀመራት ነው ማለት ነው። እናቴ ናት!!

ይሄን ሀረግ ማለት ከጀመረች ትርጉሙ የዛሬ 20 ዓመት ወደ ኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆስተስ የነበረችበት ዘመን ላይ ናት… … ማርጀቷን አታውቅም፣ እኔንም አታውቀኝም ፣ ባሏ እሷን ትቶ ጓደኛዋን እንዳገባ አታውቅም ፣ ንብረቷን እንደተቀማች አታውቅም ፣ ጡቶቿ እንደተቆረጡ አታስታውስም ………… አንዳንዴ ራሷንም አታውቅም ~ ሰው ካላያት ራሷን ትጎዳለች። እብደቷ ሲነሳባት መከራዬ ናት። ምሬቴ ናት። ስቃዬ ናት። …… ጥለሻት ጥፊ ጥፊ ይለኛል። ጭንቅላቴን በቅውሰቷ ትዋጀዋለች። ብገላገላት የምታስመኘኝ መንቻካ አሮጊት ትሆናለች። መድሃኒቷን አትውጥልኝም፣ እንድነካት አትፈቅድልኝም ፣ አምናኝ እንቅልፏን አትተኛም…… ከየት የምታመጣው እንደሆነ የማይገባኝ ጉልበት አላት…… ታጠፋበታለች። እንደእኔ የምትጠላውና የምትፈራው አይኖራትም።

“የማላውቅሽ መስሎሽ? ቅናታም መርዘኛ! …… መድሃኒቱን በምግብ ለውሰሽ ልታበይኝ? አንድዬን ልትወስጂብኝ? እኔ አይናለም በህይወት ሳለሁ ቤቴ ሊፈርስ?” ትለኛለች ያገኘችውን እቃ እየወረወረችብኝ። አንድዬ የምትለው አባቴን ነው። የድሮ ባሏን።

“ማነሽ ደግሞ አንቺ? ወደ ቤቴ ውሰዱኝ… …… ኡኡኡኡኡ… … መድሃኒት ሊያበሉኝ ነው።……”

ዶክተሯ መጥቶ መርፌዋን እስኪወጋት በሷ እብደት እኔ አብዳለሁ። ስትረጋጋልኝ እብዷ እናቴን ከጠባቂ ጋር እቤት አስቀምጬ እወጣለሁ። …… ያበደች እናት እንደሌላት፣ አንዲት የኑሮ ሰበዝ እንዳልጎደለባት ፣ እንደደላት ሴት ሁኜ…… አዘውትሬ እንደምለብሰው ሙሉ ልብሴን አጊጬ ወደ ስራዬ እሄዳለሁ።

“ ኪዳነ ምህረት ምን በደልኩሽ? ምነው ጌታዬ ስቃዬን ቆለልክብኝ? ምናለ ብትገላግለኝ?” ስትል ደግሞ ትርጉሙ ወደ አሁን ተመልሳለች ማለት ነው። ያሳለፈችውን ስቃይ እያስታወሰች መታመም ጀምራለች ማለት ነው። እብደቷ ሲተዋት ታስለቅሰኛለች። ሆዴ ኩርምትምት ይልላታል። እንዳሰቃየችኝ ታውቀዋለች። ላበደችባቸው ቀናት እንግልቴ ስትከፍለኝ ጡት የለሽ ደረቷ ላይ ለጥፋኝ ታባብለኛለች። ምን መስማት እንደምትፈልግ አውቃለሁ።

“እማ በህይወት እስካለሽ አልተውሽም። ምንም ብታደርጊ እችልሻለሁ።” እላታለሁ። አትመልስልኝም። ብቻ ጨምቃ አቅፋኝ ትንሰቀሰቃለች። የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል መግባት ሞቷ ነው። ትለምነኛለች። ሁለቴ ገብታ ታውቃለች። ይብስባታል እንጂ አይሻላትም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰውነቷም እየደከመ ህመሟም እያዛላት ነው። ትናንትና የሚሚን የሰርግ መጥሪያ ወረቀት ካየች ጀምሮ የበረራ ቁጥሯን መቁጠር ጀምራለች።

ሚሚ አባቴ ከሌላ ሚስቱ የወለዳት እህቴ ናት። ሰርጉን እኔም እናቴም እንደማንሄድ ያውቃሉ። ለምን እንደማይተውን አላውቅም። ባገኙት ሰበብና አጋጣሚ እኔና እናቴ ሰላም እንዳይሰማን ይታትራሉ። እማዬን ለማረጋጋት እማይኮነውን ሁሉ እየሆንኩ እንፈራገጣለሁ። በሚሚ ሰርግ ጉዳይ ግን ከእማዬ ይልቅ እንዳላብድ መጠበቅ ያለብኝ እኔ ነበርኩ። ምክንያቱም ሚሚ የምታገባው የልጅነት ፍቅረኛዬን ነው። የሰርግ ወረቀቱን ለእኔ አምጥተው የሰጡበት ምክንያትም እንደእናቴ እንዳብድላቸው ነው። ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ……

እኔ በሙያዬ ጠበቃ ነኝ። ……… በአንድ ቅሌታም ከፍተኛ ባለስልጣን ኬዝ ሰበብ ስሜ በሀገሪቷ የናኘ ጠበቃ…… አስታወሳችሁትኣ? አያቱ ከሚያክሉ አሮጊቶች ጋር የሚወሰልተው ሰውዬ…… አዎን ለደፈራቸው የ70 ዓመት ምስኪን አሮጊት የቆምኩት እና ያስፈረድኩበት እኔ ነበርኩ። ያ መርገምት ካርቱሚስት በአንደኛው ሳምንታዊ ጋዜጣ ላይ ጥርስ የሌላት ድዳም እና ምላሷ ከፒያሳ እስከመገናኛ የሚደርስ አሮጊት አድርጎ የሳለኝ… … አዎን እኔ ነኝ። ……… አሁን ማን እንደሆንኩ አወቃችሁኣ?

“ቢሮሽ ሰው እየጠበቀሽ ነው።” አለችኝ ወይኗ ገና ከመግባቴ።

“ደህና አደርሽ ወይኗ።” ብዬ እየተጣደፍኩ ስገባ

“አባትሽ ነው። አባቷ ነኝ ነው ያለው። አባት እንዳለሽ አልጠረጠርኩም ነበር። ……” አለኝ ፍትህ።

“አባትሽ?” ተንደርድሬ ቢሮዬ ገባሁ። ደንግጦ ተነሳ። በዓይኔ ካየሁት እንኳን ሰባት ዓመት ሆኖኛል። ምናባቱ ሊሰራ ነው አሁን የሚፈልገኝ? ጭራሽ ቢሮዬ ድረስ?

ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሁለት)

One Comment

  • smenehmaths@gmail.com'
    ስሜነህ commented on October 10, 2017 Reply

    በቀን ውስጥ ምን ያህል ተጨማሪ ሰዓት ብታገኝ ደስ ይልሃል?
    ተጨማሪ ሰዓት ማግኘት የምትፈልገው ለምንድን ነው?
    □ ከጓደኞቼ ጋር ለመሆን
    □ ለመተኛት
    □ ለማጥናት
    □ ሌላ ․․․․․
    ጊዜ በፍጥነት እንደሚጋልብ ፈረስ ነው፤ በአግባቡ ልትጠቀምበት ከፈለግህ እንዴት
    እንደምትቆጣጠረው ማወቅ አለብህ። ጊዜህን በአግባቡ መጠቀም ከቻልክ ያለብህን ውጥረት
    መቀነስ፣ በትምህርት ጥሩ ውጤት ማምጣት እንዲሁም ወላጆችህ ይበልጥ እምነት
    እንዲጥሉብህ ማድረግ ትችላለህ። “ቢሆንማ ጥሩ ነው፤ ግን ይህን ማድረጉ የመናገሩን ያህል
    ቀላል አይደለም!” ትል ይሆናል። እርግጥ ነው፣ በዚህ ረገድ አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች
    ሊገጥሙህ ይችላሉ። ይሁንና እነዚህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ልትወጣቸው ትችላለህ። እስቲ
    አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት።
    ተፈታታኝ ሁኔታ #1፦ ፕሮግራም ማውጣት
    እንቅፋት የሚሆንብህ ነገር። በፕሮግራም መመራት የሚለውን ነገር ገና ስታስበው መፈናፈኛ
    እንደምታጣ ይሰማህ ይሆናል! ማንኛውንም ነገር ባሰኘህ ሰዓት ማድረግ እንጂ እያንዳንዱን
    ነገር በፕሮግራም ማከናወን አትፈልግ ይሆናል።
    ይህን ማድረግ ያለብህ ለምንድን ነው? ንጉሥ ሰለሞን “የትጕህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ
    ያመራል” በማለት ጽፏል። ( ምሳሌ 21:5 ) ሰለሞን ሥራ የሚበዛበት ሰው እንደነበር ምንም
    ጥርጥር የለውም። ባለትዳርና የልጆች አባት እንዲሁም ንጉሥ ነበር። ዕድሜው እየገፋ ሲሄድም
    ፕሮግራሙ ይበልጥ እየተጣበበ የመጣ ይመስላል። አንተም ጊዜ እንደሚያጥርህ ይሰማህ
    ይሆናል። ይሁንና ዕድሜህ እየጨመረ ሲሄድ ሕይወትህ ይበልጥ በሥራ የተወጠረ መሆኑ
    አይቀርም። እንግዲያው ከአሁኑ በፕሮግራም መመራትን ብትለምድ የተሻለ ነው!
    እኩዮችህ ምን ይላሉ? “በቋሚነት ፕሮግራም ማውጣት ከጀመርኩ ስድስት ወር ገደማ
    ይሆነኛል። ይህን ያደረግኩት ጊዜዬ በጣም የተጣበበ ስለነበር ነው፤ በፕሮግራም መመራቴ
    ሕይወቴን ቀላል ለማድረግ ጠቅሞኛል።”—ጆዪ
    “ላደርጋቸው ያሰብኳቸውን ነገሮች በዝርዝር መጻፌ ፕሮግራሜን እንድከተል ረድቶኛል።
    ማከናወን የሚኖርብኝ ተጨማሪ ነገር ሲኖር ደግሞ እኔና እናቴ ሁሉንም ነገር በዝርዝር
    እንጽፋለን፤ ከዚያም ተረዳድተን ግቦቻችን ላይ መድረስ የምንችለው እንዴት እንደሆነ
    እንነጋገራለን።”—ማለሪ
    ምን ሊረዳህ ይችላል? እስቲ ነገሩን በዚህ መልክ ለማሰብ ሞክር፦ ከቤተሰብህ ጋር ወደ
    አንድ ቦታ ልትጓዙ አስባችኋል እንበል። ሁሉም የቤተሰብ አባላት የየራሳቸውን ሻንጣ የመኪናው
    ዕቃ መጫኛ ውስጥ ዝም ብለው ቢያጉሩት ምን የሚፈጠር ይመስልሃል? ቦታው የሚበቃ
    ላይመስል ይችላል። ታዲያ ምን ማድረግ ትችላለህ? ሁሉንም ሻንጣዎች ካወጣህ በኋላ
    መጀመሪያ ትላልቆቹን ሻንጣዎች አስገባ፤ ከዚያም ትናንሾቹን ሻንጣዎች የቀረው ቦታ ላይ
    ማስገባት ትችላለህ።
    ከጊዜ ጋር በተያያዘም ተመሳሳይ ዘዴ መጠቀም ትችላለህ። ጊዜህን ያን ያህል አስፈላጊ ባልሆኑ
    ነገሮች ካስያዝክ ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ጊዜ ለማግኘት ልትቸገር ትችላለህ። በጣም
    አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በቅድሚያ አከናውን፤ ይህን ካደረግህ በኋላ ሌሎች ነገሮችን
    ለማከናወን ምን ያህል ጊዜ እንደሚተርፍህ ስታይ መገረምህ አይቀርም!— ፊልጵስዩስ 1:10
    ልታደርጋቸው የሚገቡ ከሁሉ በላይ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?
    ․․․․․
    አሁን ደግሞ የጻፍካቸውን ነገሮች ይበልጥ ቅድሚያ ሊሰጠው ከሚገባው ጀምረህ በቅደም
    ተከተል አስቀምጣቸው። አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች በቅድሚያ የምታከናውን ከሆነ ያን ያህል
    አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮችን ለማከናወን የሚያስችል ብዙ ጊዜ ታተርፋለህ።
    ምን ማድረግ ትችላለህ? የቀን መቁጠሪያ ያለው በኪስ የሚያዝ ማስታወሻ ደብተር አዘጋጅተህ
    ማከናወን ያለብህን ነገሮች ቅድሚያ ሊሰጠው ከሚገባው ጀምረህ በቅደም ተከተል ጻፋቸው።
    የቀን መቁጠሪያ ባለው ማስታወሻ ደብተር ፋንታ ከዚህ ቀጥሎ ከቀረቡት አማራጮች መካከል
    አንዱን መጠቀምም ትችላለህ።
    □ የሞባይል ስልክ የቀን መቁጠሪያ
    □ አነስ ያለ ማስታወሻ ደብተር
    □ የኮምፒውተር የቀን መቁጠሪያ
    □ ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ የቀን መቁጠሪያ
    ተፈታታኝ ሁኔታ #2፦ ፕሮግራምህን በጥብቅ መከተል
    እንቅፋት የሚሆንብህ ነገር። ከትምህርት ቤት እንደተመለስክ ቴሌቪዥን እያየህ ትንሽ ዘና
    ማለት ትፈልግ ይሆናል። ወይም ደግሞ ፈተና ኖሮህ ለማጥናት አቅደህ ሳለ ጓደኞችህ ‘ሲኒማ
    እንግባ’ የሚል መልእክት ላኩልህ እንበል። ‘ፊልሙ የሚታይበት ሰዓት ሊለወጥ አይችልም፤
    ጥናቴን ግን ማታ ስመለስ ልደርስበት እችላለሁ። በዚያ ላይ ደግሞ ፈተና ላይ በደንብ
    የምሠራው ባለቀ ሰዓት ሳጠና ነው’ ብለህ ታስብ ይሆናል።
    ይህን ማድረግ ያለብህ ለምንድን ነው? አእምሮህ የበለጠ ንቁ እያለ ብታጠና የተሻለ
    ውጤት ልታመጣ ትችላለህ። ደግሞስ ያለብህ ውጥረት ሳያንስ ሌሊቱን በችኮላ ለማጥናት
    በመሞከር በራስህ ላይ ለምን ሌላ ውጥረት ትጨምራለህ? በዚያ ላይ በማግስቱ ጠዋት ምን
    ሊከሰት እንደሚችል እስቲ አስብ። ከእንቅልፍህ አርፍደህ ብትነቃ የበለጠ ትወጣጠራለህ፤
    ከዚህም ሌላ ከቤት ተጣድፈህ ልትወጣ ወይም ትምህርት ቤት ዘግይተህ ልትደርስ ትችላለህ።
    —ምሳሌ 6:10, 11
    እኩዮችህ ምን ይላሉ? “ቴሌቪዥን ማየት፣ ጊታር መጫወትና ከጓደኞቼ ጋር መሆን በጣም
    ያስደስተኛል። እነዚህን ነገሮች ማድረግ በራሱ ስህተት ባይሆንም ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑት
    ነገሮች ጊዜ ስለሚያሳጡኝ በኋላ ላይ ነገሮችን በጥድፊያ ለማከናወን እገደዳለሁ።”—ጁልያን
    ምን ሊረዳህ ይችላል? የግድ ማድረግ ያለብህን ነገሮች ብቻ ሳይሆን ዘና የምትልባቸውን
    አንዳንድ እንቅስቃሴዎችም በፕሮግራምህ ውስጥ አካትት። ጁልያን “በኋላ ላይ አንድ
    የሚያስደስተኝ ነገር እንደማደርግ ካሰብኩ ከዚያ በፊት መሥራት የሚገባኝን ነገር ማከናወን
    ቀላል ይሆንልኛል” በማለት ተናግሯል። ሌላ አማራጭ፦ ልትደርስበት የምትፈልገው ግብ
    አውጣ፤ ከዚያም እዚያ ላይ ለመድረስ የሚረዱህ ሌሎች የአጭር ጊዜ ግቦች በማውጣት
    በፕሮግራምህ መሠረት እየሄድህ መሆንህን ተከታተል።
    ምን ማድረግ ትችላለህ? በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ልትደርስባቸው የምትችላቸውን
    አንድ ወይም ሁለት ግቦች ከታች ባለው ክፍት ቦታ ላይ ጻፍ።
    ․․․․․
    በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ልትደርስበት የምትፈልገውን ግብ ጻፍ። እዚህ ግብ ላይ
    ለመድረስ ከአሁን ጀምሮ ምን ማድረግ ትችላለህ? *
    ․․․․․
    ተፈታታኝ ሁኔታ #3፦ ንጹሕና የተደራጀህ መሆን
    እንቅፋት የሚሆንብህ ነገር። ‘ንጹሕና የተደራጁ መሆን ጊዜን በአግባቡ ከመጠቀም ጋር ምን
    ግንኙነት አለው?’ ብለህ ታስብ ይሆናል። ‘በዚያ ላይ ሁሉን ነገር በሥርዓት ማስቀመጥ ቀላል
    አይደለም። ክፍሌን ነገም ላስተካክለው እችላለሁ፤ ደግሞም ባይስተካከልስ! እኔ እንደሆን
    መዝረክረኩ ያን ያህል አይደብረኝም!’ ትል ይሆናል። በመሆኑም ክፍልህን ማስተካከል ያን ያህል
    አስፈላጊ እንዳልሆነ ሊሰማህ ይችላል። ይሁንና ይህ ትክክለኛ አመለካከት ነው?
    ይህን ማድረግ ያለብህ ለምንድን ነው? ሁሉንም ነገር በሥርዓት ማስቀመጥህና የተደራጀህ
    መሆንህ የምትፈልገውን ነገር በቀላሉ ለማግኘት ስለሚያስችልህ ጊዜ ይቆጥብልሃል።
    በተጨማሪም የተረጋጋህ እንድትሆን ስለሚረዳህ በጣም ይጠቅምሃል።—1 ቆሮንቶስ 14:40
    እኩዮችህ ምን ይላሉ? “ልብሶቼ ከተዝረከረኩ የምፈልጋቸውን ነገሮች ማግኘት በጣም
    አስቸጋሪ ይሆንብኛል።”—ማንዲ
    “በአንድ ወቅት የኪስ ቦርሳዬን የት እንዳደረግሁት አጥቼው ነበር። ሳምንቱን በሙሉ ብፈልገውም
    ላገኘው ስላልቻልኩ በጣም ተጨነቅኩ። በመጨረሻ ግን ክፍሌን ሳስተካክል አገኘሁት።”—
    ፍራንክ
    ምን ሊረዳህ ይችላል? በተቻለህ መጠን ዕቃዎችህን ወዲያውኑ በየቦታቸው ለመመለስ ጥረት
    አድርግ። ክፍልህ ተዝረክርኮ ለማጽዳት አስቸጋሪ እስኪሆን ከመጠበቅ ይልቅ ከሥር ከሥሩ
    አስተካክለው።
    ማድረግ የምትችለው ነገር። ምንጊዜም ንጹሕና የተደራጀህ ለመሆን ጥረት አድርግ። ሁሉንም
    ነገር በሥርዓት ለማስቀመጥ ስትጥር ውጥረትህ ይቀንስልሃል።
    ጊዜ ሁሉም ሰው በእኩል መጠን የተሰጠው ንብረት ነው ማለት ይችላል። ይህን ንብረት
    ካባከንከው ችግር ውስጥ ትገባለህ። በአግባቡ ከተጠቀምክበት ግን ጥሩ ውጤት ታገኛለህ።
    ምርጫው የአንተ ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...