‘እንካነት’
አፍ ለንባብ ወደ አደባባይ ከመምጣቱ በፊት፤ ደራሲው ለአምስት ወንድም ደራሲዎች የመፅሀፉን የተተየበ ኮፒ በመስጠት ሥግር እንዲሰሩበት ጋብዞ ነበር።
የደረሱኝን እነዚህን ሥግሮች በአፍ ሁለተኛ ዕትም ላይ እንደማቀርብ ተስፋ አደርጋለሁ። ‘እንካ’ ብዬ የምጠራውም ይህን ደራሲያኑን የመጋበዝ ድርጊት ነው።
አፍ የተባለውን ይሄን ልብ ወለድ ከዚህ ሰፋ አድርጌ በግሌ ሥግር ልሰራበት እችላለሁ። ዋናው ዓላማዬ እሱ ሳይሆን ሌሎች ደራሲዎች የተሳተፉበት ውስብስብ (complex) የሆነ ነገር መፍጠር ነው። ወደ ኋላ ላይ እንደ ምክኒያት የማነሳቸው ጥቂት ነጥቦችም አሉ።
አፍ ወደ አደባባይ ሲወረወር ለተስፋፋ እክብነት ራሱን ክፍት እያደረገ ነው። ማንም እክብ የተለያዩ ብልቶች አሉት። በተለምዶ አጭር ታሪክ አንድ አቅጣጫ ያለው፥ አንድ ነጥብ ላይ ያተኮረ ሞኖሎጂካል እንደሆነ ተቀባይነት ያገኘ ነው። እጅግ አትኩሮታም መሆን ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ ተቀምጦ በመነሳት መሃል የሚነበብ አድርገው ይወስኑታል።
ለእኔ ማንም ልብ ወለድ ስድራት (assemblage) መሆን አለበት። ልብ ወለድ ከማስተማሰል ውጪ ከምናየው ተጨባጭ አለም የተለየ ያለ ስድራት የሚነቃነቅ ፀረ ውስብስብ አይደለም። ራሱ እክብ ቢሆንም ለበለጠ እክባዊ ለውጥ ራሱን ይከፍታል። በዚህም ወደ ሌላ አይነት የስፋትና የጥራት ለውጥ ይሄዳል።
ማለት አፍ ይከራል። ደራሲው በመርበብት ቢፅፍም የስራው ጊዜያዊ ወሰን በፍጥነት እንዲፈርስ ይጋብዛል። ማሥገር ማለት በየአፍታው የሚለወጥ ተነቃናቂ ማንነትን መፍጠር ነው። የአፍ ከባቢ የደራሲነቱን ቦታ ሲወስድና በፍጥነት ሲያፅን የአንባቢና የደራሲነት ወሰን ይደባለቃል። አንባቢ አንባቢ-ደራሲ (አንደራ) ይሆናል።
ልብ ወለዶች ብዙ ጊዜ ከሚፃፉባቸው ዘመኖች ርቀው የሚሰሩ የስነ ምልክት ቁሶች ናቸው። እንደ ጋዜጣና መፅሄት የቅርቡን ጊዜ አይመዘግቡም። ሥግር ግን የአሁን ጊዜ ቀጠና ውስጥ የመግባት ፀባዩ አንደምርጫ ተቀምጦለታል። የማንበብና የመፃፍ ሂደቶች ተከታታይ ወይም በአንድ ሂደት ውስጥ ይገባሉ። አንባቢና ደራሲ በመሆን መሃል ያለው የጊዜ ርቀት ጠባብ ይሆናል። ሁለቱ አንድ መስክ ላይ ያርፋሉ። ተዋረድ ለማውጣት አይመችም። ቢወጣም በቅደም ተከተል ስለሚሻሻሩ አያምርም።
ሮላንድ ባርቴስና ጁሊያ ክርስቴቫ ስለ ደራሲው አለመኖር ወይም መሞት ሲነግሩን ‘መፃፍ ማለት የነበረውን እንደገና መፃፍ ነው’ ይሉናል። የባርቴስ ድርሳን ሳያቋርጥ ራሱን የሚሸምን ነው።
ሱዛን ፍሪድማን ደግሞ እንዲህ ትላለች፤
‘Barthes’s text is an infinite web seemingly spinning itself and demands the reintroduction of the spider–as author, as subject, as agent, as genndered bod, as producer of the text’
አለምን የማይለወጥ ደጋግሞ የሚከሰት የኩነቶች አዙሪት ነገር ያደርጉታል። ነገር ግን አንድ ጉዳይ በዑደት ተመልሶ ይመጣል ብንልም ሁልጊዜም አዲስ የተለየ ጉዳይ ለጥፎ ነው።
ሥግር አሰራር ደረቅ እውነታ፥ ቀዳሚ ትረካ፥ ደራሲው፥ ፅንሰ ሃሳቦቹና የማስተማሰያ ተረኮቹ እንዳሉ ያምናል። ቦታው ሙሉ ነው። ባክቲን ‘ደራሲው አልሞተም እንዲያውም ሁሉ ጉዳይ የተሰበሰበበት ማዕከል ነው’ ይላል። ጄራልድ ጄኔትም ‘The literally phenomena is not only the text but also its reader and all the reader’s possible reactions to the text’ ይላል።
ዛሬ የሚሰራው ትረካ በአለፉት ትረካዎች ላይ የተመሰረተ ብቻ ነው ብሎ ማመን ቢያንስ አገራችን ውስጥ አይሰራም። አባባሉ ፋንታስቲክ በመሆኑ እንደ ተረት ሊመስጠን ይችላል። ሁሉ intertext ነው ማለት ከመጀመርያው ሕፅናዊነትን መግደል ነው።
እንደኛ አዲስ ነገር የለም፥ ሁሉም የተባለ ነው ማለት በእውነትና በማስተማሰል መሃል የ100 ፐርሰንት ግቡቡነት እንዳለ ምስክር ነው። በሲግኒፋይድ (ተወካይ)ና በሲግኒፋየር (ወካይ) መሃል ያለው የማይደፈን ልዩነት ውሸት ይሆናል።
ኢማኑኤል ካንት ‘በአለምና በሃሳብ መሃል ሊደፈን የማይችል ጉድባ አለ’ ይላል። ቢያንስ በዚህ መልክ ሕፅናዊነት ሱሶርያን ነው። የማሥገር ድርጊት ደራሲው እንዳለ ያምናል። አዲስ ነገርም እንደሚፈጥር ወይም አንደሚል ያምናል።
የሕፅናዊነት ዓለም ምን ሊመስል ይችላል?
***
ክፍል 4