እና፥በእዚህ፡አስደናቂ፡ጎዞ፡ወቅት፡ነው፥ለተረት፡የማይመስል፣ለዕውን፡የሚያስፈራ፣ለግምት፡የቸገረ፡`ኣጋጣሚ`፡ከፊት፡ለፊታችን፡የተደቀነብን።የሆነው፡ስለ፡ሆነ፡እና፤መዝገብ፡የሙያ፡ግዴታዬ፡በመሆኑም፤አነሆኝ፤ገጠመኙን፡እንደሚከተለው፡ከትቤዋለሁ።ትርጉም፥የግል፣ዕምነትም፡የተጸውዖ፡ናቸው፡እና፥እንደመሰላችሁ፡ተረዱት።
ወደ፡ሠማይ፡የምናርግ፡ይመስል፥እየ፡አሻቀበ፣አያዳገተ፡የሚሄደውን፡ኾረብታማ፡ጠረጠር፥ቢሊሊል፡እንልበት፡ያዝን። የ፡ወይዘሮ፡`ዕሌኒት`፡ወግ፡እና፡ጭውውት፤ከቶም፡የሚጠገብ፡አልነበረም። `ኒኒየትየም`፡በእየ፡መሃሉ፡እየገባች፡የመሰላትን፥ማጣፈጫ፡ሃሳብ፡ጣል፡ታደርጋለች።
`ይገርምሃል፥ከጥንቶቹ፡ወርቃማ፡ከያኒዎች፡ጋር፥ግንኙነታችንን፡አላቍረጥንም።የእናቴም፤የድሮው፡ትውስታ፤ስለ፡አለ፥አንዴ፡ስልክ፡መደዋወል፡ከጀመርን፤ፈጽሞ፡ማብቅያ፡የለውም~እና፡በቀደም፡ምን፡ያጫውቱኛል፥`ያ፡አንቺ፡እጅግ፡የምታደንቂው፡ደራሲ፡እኮ፡ሞተ`ብለው፤ድንገት፡አያረዱኝ፡መሰለህ*። ስለ፡አንት፡ጽሑፍ፡ፍቺ፡እና፡ትርጉም፤በደምብ፡ያስተዋወቀኝ፡እርሱ፡ነበር`
የጠቀሰችልኝን፡ሥም፤በዝና፡እንኵን፡በአለመስማቴ፤ስገረም፥በሌላው፡በኩል፡ደግሞ፥ከሐገር፡ከወጣሁ፡በሗላ፡የተፈጠረውን፤በግጻዌ፡ተገኝቼ፡መከታተል፡በአለመቻሌ፥`ይሄስ፡ባልገረመህ*`~ብዬ፡አለፍኩት። `ዕሌኒት`ም፤የሞቀ፡ወግዋን፡ቀጠለች፡~
`አንዳድ፡አንዴ፡እማ~በህልሜ፡ሁሉ፡እየመጣ፥የቸገረኝን፡የኪነት፡ትብትብ፡ይፈታልኝ፡ነበር`፡እንደ፡አለኝ፡አስታውሳለሁ`፡አለች።
መኪና፡ነጂው፥በሚያዳምጠው፡ሁሉ፡ተመስጦ፡ውስጥ፡እንደገባ፡ያስታውቃል።
እንዲሁ፡እያልን፡ስንጕዝ፡ቆይተን፥ለኣራት፡ሰዓቱ፡መንገድ፤በመሃሉ፥ጥቂት፡እረፍት፡እንደሚያሻን፤አስቀድማ፡አሳውቃን፡ስለነበር፡~`እንግዲህ፥ይህቺ፥ከእርቀት፡የምትታያችሁ፥ትንስዬ፡መንደር፥ማረፍያችን፡ትሁን~`ዣርዳን~ሴክሬ`፡ይሏታል`፡አለች።
`ከመንደርዋ፡እንደገባን፥ከወደ፡አፋፍ፡የሚገኘውን፥ምግብ፡ቤት፡መርጠን፥መኪናችንን፤ከቅጥሩ፡አቁመን፡ወረድን። ተኾራምቶ፡የቆየው፡ተሳፍሪ፡ሁሉ፥እግር፡ማፍታታቱን፣ዙርያውን፡መቃኘቱን፡እንደ፡ጀመረ፥ወደ፡ለንደን፡ስልክ፡መደወል፡ንደሚገባኝ፡አስታውቄ፤አጠገቤ፡ከነበረው፡ኪዮስክ፡ስገባ፡~
`ይገርምሻል~ሁሌም፡እንደ፡እዚሁ፡ነው~ትንሽ፤ከከተማ፡ወጣ፡ከአለ፤የ፡`ሎንዶን`፡ጕደኞቹ፡ይናፍቁታል`፡ስትል፡እሰማታለሁ። ምነው፥`ኒኒየት`፡እንዳለችው፡ሆኖ፡በቀረ፡ነበር~ውድ፡አንባቢዬ፥እና፤ከፈተና፡በዳንኩኝ*። ምን፡ይሆናል~የሰው፡ምኞት፡ሌላ፣የሕይወት፡ተብየዋ፡ጉድ፤አካሄድ፡ሌላ*
ስልኩን፡የአነሳው፡ሰው፡~`ማን፡ልበል*`፤ሲል፤በሞጋች፡ድምጽ፡ቃና፡ጠየቀኝ
`አንተን፡ማን፡ልበል~እኔማ፡የምፈልገውን፡አውቃለሁ`፡ስል፡መለስኩኝ።
`እኔ፡ነኝ፡እኮ፡የደወልኩት`፡ብሎኝ፡አረፈ
`የት፡ብለህ፡ነው፡የደወልከው*`~ስል፡አፋጠጥኩት።
`ተመስገን~ረዳ፡እግዚ`፤ማለት፤እርስዎ፡ነዎት*`፡ሲል፡አከለበት።
በእዚሁ፡ቅጽበት፥ከአለሁበት፡ኪዎስክ፡ውጭ፥ወይዘሮ፡`ዕሌኒት`፡ስፅለፈለፍ፡እና፥ተደግፋ፤ከአግዳሚው፡ወምበር፡ላይ፡ሲያስቀምጧት፡ታየኝ።ከመጣበት፡ሳይታወቅ፥አጠገባቸው፡የቆመውን፡ሰው፡ግን፡አላውቀውም።ኣበሻ፡ለመሆኑ፡ግን፡አያጠራጥርም። የሐገርዋን፡ሰው፤በኣጋጣሚ፡አግኝታ፤የማይሆን፡ነገር፡አሰምትዋት፡ይሆናል፡በሚል፡ጥርጣሬ፥መንፈሱ፡በስልክ፡የተጠለፈውን፥የለንደን፡አናጋሪዬን፡`ይቅርታ፥አደብ፡ግዛ፡እና፥በሌላ፡ቀን፡ብንነጋገር፡ይሻላል`፡ብዬ፡ዘግቼ፤ወደ፡አርስዋ፡አመራሁ። እንግዳው፡ሰው፤ሲያየኝ፤ጎንበስ፡ብሎ፥የማሽፍ፡መሳይ፡እጅ፡እየነሳ፡~
`ምድራችን፥ታሪክ፡እና፡ድንቅ፡አያልቅባት፥ከአልጠፋ፡ስፍራ፤እዚህ፡`ሠማየ~ውድውድ`፡ስር፡አገናኘችን*`፡ሲል፥ፈጽሞ፡የተናወጸችው፡ዕሌኒት`፤ትንፋሽ፡እየ፡አጠራት፡~`ተ~ተ~መስገን~ረድዐ፡እግዚ`፡ማ~ማለት፡እኮ፡እርሱ፡ነው`፡አለችኝ።
የተውኔት፡መድረክ፡ላይ፡የሞኾስል፡ይመስል፤አሁንም፡እየተሽቆጠቆጠ፡~`በኪነትሕ፡ምናብ፥ገነትን፡ስታሳየኝ፡በመኖርህ፥እነሆ፥የመንግሥተ፡ሠማያትን፡ቁልፍ፤አንተ፡እጅ፡ነው፡ማለትን፡ስለሰማሁ፥ፍለጋ፡መጥቻለሁ*`፡ሲል፤በዚቀኛ፡ንጝግሩን፡ይራቀቅብኝ፡ቀጠለ።
ምናልባት፥መኪና፡ነጂአችን፤የተሻለ፡ማብራርያ፡ይሰጠኝ፡ይሆናል፡በሚል፤ጠጋ፡ስለው፥መኪናው፡ዙርያ፡እየተንቆራጠጠ፡~`አርፏል`፤ብለው፡የአረድዋት፥እሱን፡እኮ፡ነበር፥ድንጋጤው፡ልብዋን፡አጥወልውሏት፡ነው`፡አለኝ።
የስልኩ፡መዟዟር፡ሲደንቀኝ፤ይብሱን፡ይሄ፡ተአከለበት። `አቶ~ኣልኧዛር`፡ይሁኑ፤ወይም፤ተውኔት፡የሚወደዱ፥ከእንቅልፋቸው፡ድንገት፡የባነኑ፡ወገን፤መለየት፡ከአቅሜ፡በላይ፡እንደሆነ፡ስለገባኝ፥በሁኔታችን፡የተራበሸችውን፡`ኒኒየትዬን`ወደ፡ጎን፡ወስጄ፤ስለተፈጠረው፡ግራ፡መጋባት፡አብራራሁላት። እንደ፡ወትሮዋ፡ሁሉ፤በብልህ፡ኣንጎልዋ፥በፍጥነት፡ኣስባ፡ስታበቃ፡~`ከእዚሁ፡መንደር፤ወደ፡`ዤኒቭ`፡የሚሄድ፡አውቶቡስ፡አለ፥እሱን፡ተሳፍረን፥በግዜ፡ወደ፡ሐገራችን፡እንመልስ`፡ስትለኝ።
ድምጽ፡ሳላሰማ፤በቀጥታ፡ወደ፡መኪናው፡የጀርባ፡ኮፈን፡በመሄድ፡ሻንጣችንን፡አውጥቼ፤እጅዋን፡ይዤ፥ወደ፡ኣውቶቡስ፡ማቆምያው፡አመራን። ወይዘሮ፡`ዕሌኒ`፡እና፡ሁለቱ፡ኣበሾች፡ሲጨቃጨቁ፡ይሰማኛል። ድንጋጤው፡የአልበረደላት፥`ኒኒየት`፥`ምን፡እየተባባሉ፡ነው*`፤ስትል፡ጠየቀችኝ።
`በምን፡ቍንቍ፡እንደሆነ፡የሚያወሩት፡እኔ፡እንጃ~`፡አልኵት።
~~~*~~~
4 Comments
ምንም የመዘግየት ችግር ቢኖርበትም
ኢትዮጵያ በመሆኑ ብቻ በርቱ እደጎ
ፈጣሪ ሀገራችን ይጠብቃል
አሜን
አሜን
አሜን
ማንም ምንም ቢል ኢትዮጵያዊ ቋንቋ
ማሳደግ ግድ የሚለ ይመስለኛል ለብዞዎቾ
ተደራሽ ይሆን
ሰይፋ ሽታዬ ዋለልኝ
ማንም ምንም ቢል ኢትዮጵያዊ ቋንቋ
ማሳደግ ግድ የሚለ ይመስለኛል ለብዞዎቾ
ተደራሽ ይሆን
ሰይፋ ሽታዬ ዋለልኝ