`ደግሞም፥ቆይታችን፥ከሁለት፡ሣምንት፡በላይ፡የማያልፍ፡ከመሆኑም፡በላይ፤ለ፡እኔ፡እና፡አንቺ፡ባይተዋር፡ሊሆንብን፡የማይችል፡የኣውሮጳ፡ሐገር፡ስለሆነ፥ካልተመቸን፥ብድግ፡ብለን፡ጥለን፡
መመለስ፡ነዋ~ምን፡ችግር፡አለ`።`ኒንየትዬ`፤ነገሬ፡ሲጥማት፡ሁሌም፡እንደምታደገው፥ጠጋ፡ብላ፥ከንፈሬን፡በሥሱ፡ሳመችኝ።የሥዊስ፡አየር፡በረራውም፡ቀጠለ።
ስለ፡`ስዊትዘርላንድ`፡ሐገር፡የማውቀው፥የተወሰኑ፡ነገሮችን፡ብቻነው።የበረዶ፡ላይ፡መንሽራተቻ፡ስፖርት፡ምድር፡እንደሆነች፣በዓለም፡ተወዳጅ፡ቸኮላታ፡እንደምታመርት፣ከወፍ፡ጎጆዋ፡
ውስጥ፡ብቅ፡ብላ፥`ኩኮ~ኩኮ`፡ብላ፡የምትዘምር፥የላንቲካ፡አንሻንጉሊት፡እንደ፡አለች፣ብዙ፡ጎንብኝዎች፤ደርሰው፡ሲመለሱ፡የሚይዙት፥`የስዊስ~ቢላዋ`፡የተሰኘ፡ሴንጢ፣የቀይ፡መስቀል፡
ኣርማ`፥ጥቂቶቹ፡ናሙና፡ናቸው።በእርግጥም፥መጠቀስ፡የማያሻው፥ዓለም~አቀፉ፤`የተባባሩት~መንግሥታት፡ማኅበር፤ዋና፡ጽሕፈት፡ቤት፡ምድር፡መሆኑን፡እና፤እጅግ፡የበለጸገ፥
`ገለልተኛ`፡ሐገር፡እንደሆነ፣የመላይቱን፡ዓለም፡ባንኮች፡የሚያስተናግድ፡እና፡የሚያስተዳድር፡ምድር፡እንደሆነም፥በሰፊው፡የሚነገርለት፡ገጽታው፡ነው። ከምን፣ለምን፡`እንደተገለለ፡`፡
ግን፡አልገባኝም።
ኣውሮፓን፡እና፡መላይቱን፡ዓለማችንን፡የአናወጸው፥የሁለተኛው፡የዓለም፡ጦርነት፥ሲጋይ፣ሲጠኸይ፥ይህችን፡ሐገር፥ጨረፍታ፡እንኵን፡እንዳልነካት፡ሰምተናል።ከ፡እዚህ፡
በተረፈ፥በስማ፡በለው፥አንድ፡ሦስት፡አራት፡ዝነኛ፡ከያኒዎችዋን፡ሥም፡ሰምቼ፡ቢሆን፡ነው።
አጠገቤ፡የምታንቀላፋው፡ጕደኛዬ፥`ኒኒየት`፥የ፡`ስኮትሥ~ላንድ`፡ተወላጅ፡ብትሆንም፥ጥቂት፡አውሮፓ፡ሐገሮች፡ውስጥ፡በመኖርዋ፥`ስዊስዘርላንድን`፡ምድር፤በእየ፡ወቅቱ፡አጋጣሚ፡
እንደተላለፈችበት፡አጫውታኝ፡አለች።
`የጡረታ፡ዕድሜአቸውን፥በሰጥታ፡እና፡በተድላ፣ደስታ፡ማሳለፍ፡የሚሹ፥የኣውሮፓ፡መሣፍንት፣ዲታዎች፡እና፡ከበርቴዎች፡እንዲመች፡ሆኖ፤በሚገባ፡የተደራጀ፥የህግ፡እና፡ሥርዐት፡ምድር፡
ነው`፡የአለችኝ፡ይታወሰኛል።
የሦስት፡ሰዓት፡ገደማው፥ከ፡`ሎንዶን~ጄኔቫ`፡በረራችን፡እንደ፡አበቃለት፥አብራሪው፤በድምጽ፡ማጉሊያው፡በአበሰረን፡መሰረት፥ጽዱ፡እና፡ጥንቁቅ፡ሆና፡ከጠበቀችን፥`ዤኔቫ`፡
ከተማ፡አውሮፕላን፡ማረፍያ፡ጣብያ፡በሠላም፡ስናርፍ፥`ኒኒየትዬን`፡ቀሰቀስኵት። ዓይኖችዋን፡እየ፡አሻሸች፡ነቅታ፥በመስኮቱ፤ቁልቁል፡ትመለከት፡ጀመር።
ጋባዣችን፡ወይዘሮ፥`ሄለኒት~ይደረቡ`፥የአራት፡ሰዓት፡የመኪና፡መንገድ፡ተጉዛ፥`ኦበር~ዶርፈን`፡ከተሰኘው፥የሰሜን፡ጥጉ፥መኖርያ፡መንደርዋ፡ተነስታ፤ልትቀበለን፡እዚህ፡ድረስ፡
መምጣትዋ፤እእጅጉን፡አስደንቆኝ፡~
`ኒኒየትዬ`፥ይኸች፡ሴት፥ኪነቴን፡ምኑን፡ይአክል፡ብትወድደው፡ይሆን፥ይሄንን፡ሁሉ፡እርቀት፡ለፍታ፡መምጣትዋ`*፡ብዬ፡ባነክርላት፥የ፡ኣበሻ፤ሥነ፡ልቡናችን፡ነገር፤ግር፡እንደሚላት፡ሁሉ፥በ፡
`እኔ~እንጃ`፡ዝምታ፥ትከሻዋን፡ብቻ፤ሽቅብ፡መታ፡አደረገች።
ከ፡ወይዘሮ፡`ሄለኒት`፡ጋር፤በስልክ፡በተዋዋልነው፡መሰረት፥ከሰዓቱ፤ቀድማ፡ደርሳ፡ኖሮ፥አጠር፣ቆፍጠን፡የአለችው፤ሰልካካ፡ጠይም፡የሴት፡ወይዘሮ፥በፈገታ፡እየተቀበለችን፥
`እንኵን፡በደህና፥ከድንቂቱ፥የስዊስ፡ምድር፡ገባችሁ`፡በማለት፥ሁለታችንንም፥በባህላዊው፡ደምብ፥ጉንጫችንን፡አገላብጣ፡ሳመችን።አብሯት፡የአለውን፥የመኪናዋን፡ነጂ፥
ጠየም፣ረዘም፡የአለ፡ሰውዬ፥`ተዋወቁልኝ፥ባለ፡ውለታ፡ወዳጄ፡ነው፥`የተስፋው`፡ይሰኛል፡አለችን።
በዝና፡ስሚ፥ዦሮው~ጠገብ፡ፈገግታ፤በትኅትና፡ሠላምታ፡ሰጥቶኝ፥ወደ፡የምትጠብቀን፥`ረኖ`፡መኪና፡ገባን።
`~ቲጂ`፡በሰጠችኝ፡ገለጻ፡ብቻ፥እንደማልስትሕ፡እርግጠኛ፡ነበርኩኝ~ደግሞም፥ከፈርንጅ፡ጋር፡አብሮ፤የሚታይ፤ብዙም፡የኣበሻ፡ወንድ፡ስለማይኖርም፥ከእርቀት፡ለመነጸር፡አላዳገታችሁኝም
`፡አለች። ጀርመን፡ቍንቍ፡አቀላጥፋ፡ከምትናገረው፤ከ፡`ኒኒየትዬ`፡ጋር፡ወድያው፡ለመግባባት፡በመቻላቸው፤እጅጉን፡ደስ፡አለኝ።
የጽዳት፡እና፡ሥርዓቱን፡ስድረት፡ብቻ፡መታዘብ፥መዳፍን፡ከኣፍ፡ከሚያስጭነው፤መሐል፡ከተማ፡ሰንጥቀን፡ገብተን፥ለማረፍያ፡ከተዘጋጀልን፡ምግብ፡ቤት፡እየቀረብን፡ስአለን፡~`ምሤታችን፤
`ኣውራሪስ`፡ከተሰኘው፤የሐገር፡ባሕል፡ምግብ፡ቤት፡እንደሚሆን፡እና፥ባለንብረትዋም፥`ቤታኒ`፡የተሰኘች፤የሐገሩን፡ተወላጅ፡አግብታ፡የምትኖር፡ኢትዮጵያዊት፡ወይዘሮ፤የልብ፡ወዳጅዋ፡
እንደ፡ሆነች፡አሳወቀችን። አቀበት፡ላይ፡የተከፈተው፤በሐገር፡ባሕል፡የወግ፡ዕቃ፡ከ፡አጌጠው፡ምግብ፡ቤት፡በራፍ፡ላይ፡ወጥታ፤በፈገግታ፡የተቀበለችን፥ደርባባ፣ብስል፡ቀይ፡ወይዘሮ፥የተፈጥሮ
፡ቁንጅና፡እና፡የኑሮ፡ምቾት፤በአንድ፡አብረው፡የቸሩዋት፡ሴት፡መሆንዋ፤በጉልህ፡ይታያል።
ደርበብ፣በአለ፡አረማመድ፥እዚህ፡እዝያ፡እየ፡አለች፥ለሰራተኞችዋን፡ትዕዛዝ፡ሰጥታ፡ስታበቃ፤ወደ፡እኛው፤መለስ፡በማለት፡~`እንግዲህ፥የመስተንግዶው፤የምሣ፡ግብዣ~የእኔ፡ነው
`፡ስትል፥በእርጋታ፡አስታወቀችን።መቀመጫችንን፡ይዘን፡አረፍ፡እንደ፡አልን፥አጠገቤ፡የተቀመጠው፥መኪና፡ነጂአችን፡ጉብል፥`ኣያቴ፡በተለይ፥የአንተ፡ተረክዎች፡በራዲዪ፡በሚቀርቡበት፡
ሰዓት፥እቤታችን፡ውስጥ~አንድ፡ሰው፤ቃል፡ትንፍሽ፡እንዲል፡አይፈቅዱም፡ነበር፡`በማለት፡አሳቀኝ። ለወትሮ፥`ኒኒየትዬን`፡አበሻ፡መሀል፡ይዣት፡ስገባ፡የሚገጥመን፤የቍንቍ፡
ባይተዋርነት፡መገለል፡ባለመፈጠሩ፥እጅጉን፡ተመቸኝ። ከ፡አስተናግጅዋ፡`ቤታኒም`፣ከ`ሄለኒትም`፣ከሾፈሩም፡ጋር፤እንደ፡ደልብዋ፤በጀርመንኛ፡ቍንቍ፡መወያየት፡ችላለች።
ለክብር፡እንግዶች፡ተብሎ፥ጥግ፡ላይ፡ከተሞገሰው፡መሦበ፡ወርቅ፡ዙርያ፡ቀርበን፤ከመልካም፡ጭውውት፡ጋር፥ጥዑም፡ምሤታችንን፡አድርሰን፡እንደ፡አበቃን፥ባለቤትዋ፤ወይዘሮ፡
`ቤታኒ`፡~`እንግዶቻችን፥ጥቂት፡ከአረፉ፡በሗላ፤ከተማውን፡ትንሽ፥ዘወር፣ዘወር፡አድርጌ፡ባስጎበኛቸው፡ደስታዬ፡ነው`፡የሚል፡ግብዣ፡አቀረበች።
ወደ፡ማረፍያችን፡መንደር፥የመመለሻ፡ጉዞኣችን፡እንዳይረፍድ`፤በሚል`፥`እኔም፡ደስ፡ባለኝ፡ነበር፥ግን፡ሳይመሽ፡`ኦበር~ዶርፈን`፡ብንገባ፥በጉጉት፡ለሚጠብቁን፥ባለቤቴ፡እና፡ለልጆቼም፡
መልካም፡ነው~እንግዶቹም፥ኣየር፡በረራው፡ሳያደክማቸው፡አልቀረም፡እና፤ገብተው፡ቢያርፉ፡ደግ፡ይመስለኛል~~`ቤታኒዬ`~ለጥቂት፡ሣምንታት፡ስለሚቆዩ፥ለ፡አንቺም፡ወድያው፡እረፍት፡
ይሆንሻል፡ብቅ፡ብለሽ፡ብታይን፡እና፡እንደገና፡ብትገናኙ`፤በማለት፤የእግረ~መንገድ፡ግብዣ፡ስታቀርብላት፥ወይዘሮ፡`ቤታኒ`፤ግብዣውን፡ደስ፡እየ፡አላት፡በፍሱህ፡ገጽ፡ተቀበለችው።
~~~*~~~
(የ፡ምዕራፍ፡፪፡ማብቅያ)
(ከ፡~`ጃህእርሥዎ፡ሞትባይኖር፡ኪሩብ፡ዔል`)
2 Comments
Whatever happened to part III of the “ Semaye Woodwood” story?. All tales have an end!!…jamoki