እንዴት አደራችሁ ጎበዛዝት? እኔ አላሁ አክበር ሳይል ከእንቅልፌ ነቅቼ እስኪነጋ ድረስ ዩቲዩብ ላይ የተለቀቀ የአማርኛ ፊልም ከፈትኩ። ጎበዝ! እኛ ኢትዮጵያውያን የፊልም ነገር ምንም አልተዋጣልንም። የፊልሙ ኢንደስትሪያችን (ኢንደስትሪ ከተባለ) ከቀን ወደቀን ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ነው። ድርሰቱ፣ ፕሮዳክሽኑ ምናምን ምንለው አይደለም ባጭሩ ፊልም ኢንደስትሪያችን ሞቷል! ወደድንም ጠላንም ቀብሩ ተራዝሞ ነው እንጂ ፊልማችን ሞቷል!
አሁን አሁን ተስፋ ቆርጬ ተውኩት እንጂ እስከቅርብ ግዜ ድረስ ያለመታከት ደህና ፊልም ፍለጋ የሲኒማ ቤት ደጅ እጠና ነበር። ሌላ ሌላውን ተዉትና የፊልሞቹ ታሪክ ከመመሳሰሉ የተነሳ አንዱን ድርሰት ተዋናይና ርእስ ቀይረው ድጋሜ ሚሰሩት ሁሉ ነው ሚመስለው። ባለሙያዎቻችን ደሞ በተለያየ መድረክ ላይ ለፊልሙ አለማደግ ምክኒያቱ የገንዘብና የተመልካች እጥረት እንደሆነ ሲያወሩ እሰማለሁ።
እንደኔ ግን የፊልም ኢንደስትሪያችን ትልቁ ችግር ማንም ሳይሆን አሁን የፊልሙን አለም ባልታጠበ እጁ እያምቦራጨቀው ያለው ራሱ ፊልም ሰሪ ነኝ ባዩ ባለሙያው ነው! ጎበዝ እነ 12 angry man እኮ በብላክ ኤንድ ኋይት በአንድ ክፍል ውስጥ በ 12 ተዋናይና በደከመ በጀት ተሰርተው እስከዛሬ እየተገረምን ደጋግመን ምናያቸው የቀረፃ ኳሊቲያቸው ማርኮን ሳይሆን ስቶሪያቸው ጠንካራ ስለሆነ ነው። አረ የሆሊውድን ዳታ ጎግል ብታደርጉ በ 2010 ብቻ በ 15 ሺ ዶላር በጀት ተሰርተው ከመቶ ሚሊየን ዶላር በላይ ያተረፉ ፊልሞችን ታገኛላችሁ።
ብራዘር … ርእሱን አይተን የፊልሙን መጀመሪያና መጨረሻ የምናውቀውን ሃሳብ የያዘ በመንደር ፉተታ የተሞላ ፊልም ይዘህ እየመጣህ የብቃትህን ጉድለት በፋይናንስና በተመልካች ማሳበብ ነውር አይደል እንዴ? ሲጀምር የኢትዮጵያ ተመልካች የታሪኩ ደካማነትና የተዋናዩን መንደሬነት እንጂ ፊልሙ በ low coast ተሰራ ካሜራው ጥራት ጎደለው ኤዲቲንጉ የወረደ ነው ብሎ አያውቅም!
ካሜራ ፊልም ይሆን ይመስል ለቀሽም ፊልሞቻቸው የካሜራ ቀረጥ ይነሳልን እያሉ በነጋዴ ሜንታሊቲ ስለፊልም እድገት የሚያወሩ የመንደር ፊልም ሰሪዎች እያሉ የኢትዮጵያ ፊልም ኢንደስትሪ መቼም በእግሩ ቁሞ አይሄድም! !
ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ያለ መቃሚያ ቤት ተፅፎ እዚያው ተዋናይ ካስት ተደርጎ እዚያው የሚያልቅ ፊልም እያዘጋጁ ተመልካች ጠፋ ብሎ ማለቃቀስ ተመልካቹን መናቅ ነው።
ሰውዬ የተሻለ ፊልም የመስራት አቅም ከሌለህ ከፊልሙ ጋር ምን ያጣብቅሃል ሌላ ስራ አትፈልግም እንዴ?
ቀድሞውኑም አንተ በተራ ፊልም አየሩን አጥነኸው ተመልካች ስላሸሸህ ነው የተሻሉ ሰዎች ወደፊልም ኢንደስትሪው ያልመጡት! አንተ “ያራዳ ልጅ ፣ የሰፈር ልጅ” እያልክ በሁለት ወር ባደረስከው የቁጩ ፊልም ነው እነ «የነገን አልወልድም» አይነት ምርጥ ፊልሞች ተውጠው የቀሩት። አንተ በቀሽም ተመልካችህ ልክ ከየስርቻው በለቃቀምከው ቀልድ ጠፍጥፈህ በሰራኸው ተራ ፊልም የፊልሙን አለም ከተመልካች እያፀዳኸው ነው። አንተ ጫት ቤት ካስት ባረግካትና ጭኗን ስለመፀወተችህ ብቻ ተዋናይ አድርገህ በሾምካት የትወናን ሀሁ በማታውቅ ተዋናይ እልፍ የትወና ብቃቱ ያላቸው ሴቶች ተገፍተው ከስራ ወጥተዋል። አንተ በጓደኝነትና ታዋቂ ስለሆነ ተመልካች ይስባል ብለህ በደነጎርከው ብዙ ከመታየቱ ብዛት ፊቱ የመነቸከ የጎተራ ኮንዶሚኒየም ሴሌብሪቲ በአቅም ከሆሊውድ ተዋናዮች የማያንሱ እልፍ ወርቃማ የኢትዮጵያ ተዋናዮች ቦታቸው ተይዞ ዳር ቆመዋል!
«ለፊልሙ አለም ብዬ ነው ምሰራው እንጂ ተጠቃሚ አይደለሁም» ምናምን የሚል ዋቴህን አፈርፍረህ ብላው! ፊልም አያፀድቅም። ካላዋጣህ ተወው! አንተ ዞር ስትል አቅም ያለውና ተመልካቹን አስገድዶ ከቤቱ የሚያመጣ ፊልም እንደሚሰራ እርግጠኛ የሆነ ሰው ይመጣል! አንተ በምርቃና የሰራኸው ፊልም ተመልካቹን ከሲኒማው እያባረረ እንዴት ብሎ ነው የተሻለ ሰው ወደኢንደስትሪው የሚመጣው? የትኛው አዋቂ ነው ካንተ ጋር ወረፋ ይዞ እየተጋፋ ፊልም ለማሳየት ሚመጣው? ባጭሩ ስማችሁን ከመጥራታችን በፊት እንደነእንትና አይነት ቁጩበሉዎች ተሸብለሉና እንደ አብርሃም ገዛኸኝ አይነት ትክክለኛ ባለሙያዎች ወደፊት ይውጡልን ነው ምለው!
ብራዘር … አታድክመኝ የፊልሙ ችግር አንተ ነህ! ፊልሙን ትተህ ሰርግ እየቀረፅክ ኑሮህን ደጉም። ፊልሙን ለባለሙያው ተው! መድረኩን አቅም ላለው ሰው ልቀቅ! በዚሁ ከቀጠልክ የቀረውን ትንሽ ተመልካች ታባርረውና የኢትዮጵያን ፊልም እንደዳይኖሰር ታሪክ የምታረግበት ቀን ሩቅ አይሆንም! ወደፊት ሲኒማ ቤት ለመሳሳም የሚገባ ካፕል ራሱ አይኖርም ስልህ 🙂
One Comment
ዝም ብዬ ስሰማህ ገለልተኛ ያልሆነ ሂስ ነው የሰጠኸው:እንትና ይውረድ እንትና ይስራ ከምትል ዓቅም ያለኝ የፊል ባለሙያ ነኝ የሚል አካል ለምን ስርቶ አያሳየንም:ግዜኮ የውድድር ነው:የተሻለ የሰራ የተሻለ ሰም ይኖሯል:ዳኛው ደግሞ ተመልካች ነው:አንተ የአገራችን ፊልሞ ኳሊቲያቸው የወረደ ነው ከማለት አልፍህ መሰንዘር የነበረብህ አይመስለኛም:አብርሃም ያልከው ሰውዬና “ነገን አልወለድም”ያልከውን ፍልም ያልከውን ያህል ሰምና ክብር ካላቸው የሚፈርደው አንተ ሳትወን ተመልካች ነው:ዝም ብለክ በባዶ ራስህን አስገመትክ ….